ከወንጀሉም በላይ ....!
ጦርነት አማራጭ ሲጠፋ የሚገባበት አውዳሚና ጥቁር ጠባሳን ጥሎ የሚያልፍ ጉዳይ መሆኑ ፈፅሞ አከራካሪ አይሆንም። ጦርነት አንድን ፖለቲካዊ አላማና ግብ ለማሳካት በሁለት ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ ተዋጊ ኃይሎች መካከል ይደረግ እንጂ ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ የሚያስከትለው የጎንዮሽ ጉዳት/collateral damage ከተዋጊ ሀይሎቹ ባሻገር ፥ መጠኑና አይነቱ ቢለያይም ጦርነቱ በሚካሄድበት አካባቢ ያሉ ያልታጠቁ ሰላማዊ ዜጎችን ሰለባ እንደሚያደርግ የሚታመን ነው።
በጦርነት ውስጥ ጦርነቱ በፈጠረው አመቺ ሁኔታ የዘረፋ ፣ የእገታና የግድያ ወንጀሎች እንደሚበራከቱም በቀላሉ መገንዘብ ይቻላል። አለማቀፋዊ የጦር ስምምነቶች ለሲቪሎች ጥበቃና ከለላ እንዲደረግ ብሎም ተዋጊ አካላትም ይህን ህግ እንዲያከብሩ የሚያስገድዱ ቢሆንም ፣ የሚደርሱትን የጦር ወንጀሎች መቆጣጠር ወይም መግታት ግን ሲቻላቸው አይስተዋልም።
እዚህ ጋር በሁለት ተዋጊዎች መካከል በሚደረግ ጦርነት ውስጥ ፣ አንደኛው አካል የሌላኛውን ስም ለማጉደፍና ከህብረተሰቡ ለመነጠል ሲል ሆነ ብሎ የተለያዩ ወንጀሎችን በመፈፀም አለያም በማስፈፀም ይህ ካልሆነም ጦርነቱን እንደመልካም አጋጣሚ ተጠቅመው ባልታጠቁ ሰላማዊ ዜጎች ላይ የተደራጀ ወንጀል የሚፈፅሙ ጥገኛ ሀይሎችን ተግባር ባለቤቱን በመቀየር ፥ የፖለቲካ ቁማር ለመጫወት የሚደረግ አፀያፊ ተግባር ደግሞ በእጅጉ ያሳዝናል።
ወንጀል በማንኛውም አካል ይፈፀም መወገዝና ተጠያቂነትን ማስከተል ያለበት እኩይ ተግባር ነው። ሆኖም ወንጀልን የፖለቲካ ቁማር መቆመሪያ ማድረግ ግን የጭካኔ ሁሉ ጭካኔ ነው። ለተጎጅዎች ትክክለኛ ፍትህ እንዳይሰፍን የሚያደርግ ሀላፊነት የጎደለው ተግባርም ነው።
በአማራ ክልል የእገታና የዘረፋ ወንጀሎች ከጊዜ ወደጊዜ እየተበራከቱ መምጣታቸው አሳሳቢ ሆኖ ከመምጣቱም ባሻገር እነዚህ ወንጀሎችን ከመቆጣጠርና ትክክለኛ ፍትህ እንዲሰፍን ከመስራት ይልቅ '' ፅንፈኛው ኃይል ፣ ጃውሳው ፣ ፋኖው ፣ .....'' የሚል የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ በመክፈት የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት መትጋት ከወንጀሉም በላይ አሳዛኝ የሆነ ርካሽ ተግባር ነው።
ለአብነት በውጊያ በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች የሚገኙ ባንኮችን መደበኛ ስራቸውን እንዲቀጥሉና ህብረተሰቡን እንዲያገለግሉ የሚጠብቅ ኃይል '' ህፃን አግቶ ገንዘብ ተቀበለ ወይም ገደለ'' የሚል ፕሮፓጋንዳ ቢሰራበት ውሃ የሚያነሳ ይሆናልን ? '' ቢፈልግ የሚታገልለትን ህዝብ አግቶ ገንዘብ ከመቀበል ትህነግ ሲያደርገው እንደነበረው የየባንኮቹን ረብጣ ገንዘብ እየወሰደ ለአላማው ማስፈፀሚያ አያደርግም ነበር ወይ ?'' የሚል ተጠይቅ አያስነሳምንስ ? ይህ አይነቱ ተራ ፕሮፓጋንዳ ለተጎጂዎች ፍትህ ከማስፈን ይልቅ በቁስላቸው ላይ እንጨት መስደድ አይሆንምን ?
እኔ ግን እላለሁ ፣ ፋኖም በስሙ የሚነግዱና አመቸን ብለው ዘረፋና ውንብድና የሚፈፅሙ አካላትን አምርሮ ይታገል ፣ ውስጡንም ለመሰል ስም ማጠልሸት አመቺ ሁኔታ የሚፈጥሩ ስንጥቆችን ይድፈን ፣ ብሎም ለሚሰነዘርበት የፕሮፓጋንዳ ዘመቻም በቂና የህብረተሰቡን ብዥታ የሚያጠራ መረጃን በወቅቱ ተደራሽ ያድርግ።
የዜጎችን ሰላምና ደህንነት የማስጠበቅ ተቀዳሚ ሀላፊነት ያለበት ''መንግስት ነኝ'' ባዩ አካልም ርካሽ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚያደርገውን ተራ ፕሮፓጋንዳ አቁሞ ፣ ከራሱ የፀጥታ መዋቅር ጀምሮ በህብረተሰቡ ውስጥ ሁኔታዎችን እንደመልካም አጋጣሚ ተጠቅመው መሰል ውንብድናና እገታ የሚፈፅሙ ሀይሎችን መቆጣጠርና ማስቆም ብሎም ለተጎጂዎች ትክክለኛ ፍትህ እንዲሰጥ የማድረግ ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል እላለሁ!
'' በጎንደር ከተማ 14 የመንግስት የፀጥታ አካላትና አመራሮች ከላይ ከጠቀስኩት ወንጀል ጋር በተያያዘ ከስራ ተሰናብተው በቁጥጥር ስር ዋሉ!'' የሚለው መረጃም ትክክል ከሆነ ጥሩ ጅምር ነው! ሻወር የሚጀምረው ከራስ ነውና ...!
ፍትህ በግፍ ለተገደለችው ህፃን ኖላዊ! 😭😭😭