የሚሊሻ አባላት ትጥቅ ለማስፈታት የመጡ ከ12 በላይ የሚሆኑ በክልሉ የሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላትን በቁጥጥር ሥር አውለው ለመንግሥት ያስረክባሉ። በዚህ የተበሳጩ የታጠቀ ቡድኑ አባላት በአብተጋሆ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑ ሰዎችን፣ ሴቶች እና ሕፃናትን ጨምሮ፣ 23 ሲቪል ሰዎችን አፍነው ወደ ቴዎድሮስ ከተማ በመውሰድ የተወሰኑት ሲመለሱ ሌሎችን ገድለዋል። በዚህ ግጭት ምክንያት በሚሊሻ አባላት እና በአካባቢው በሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን አባላት መካከል ሰኔ 29 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ የተቀሰቀሰው ግጭት ተባብሶ ሐምሌ 3 ቀን 2016 ዓ.ም. ወደ ማኅበረሰብ ግጭት ተሸጋግሮ ባይካዎ እና አጋም ውሃ ቀበሌዎች ከሁለቱም ብሔር ተወላጆች ብዛታቸው ያልታወቀ ሰዎች ሕይወት አልፏል። ከሟቾች መካከልም ግጭቱን ማምለጥ ያልቻሉ አረጋውያን፣ ሴቶች እና ሕፃናት የሚገኙበት መሆኑን እና በዚሁ ግጭት ቤቶች እና የሰብል ማሳ መቃጠላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።
#ሼር
#ሼር