✝️ይተካል እግዚአብሔር✝️
ይተካል እግዚአብሔር አገልጋይ ለቤቱ
ከዛሬው የሚልቅ የማይዝል ጉልበቱ
አይሰስትምና ፀጋን በማካፈል
ብርቱ ውን ያስነሳል ከትውልዱ መሃል (፪)
ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ
✝️ለባለ ማህተቦች✝️ሼር ያድርጉ↗️
✨✨✨✨✨✨✨
✝️#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ✝️
✨✨✨✨✨✨✨
ይተካል እግዚአብሔር አገልጋይ ለቤቱ
ከዛሬው የሚልቅ የማይዝል ጉልበቱ
አይሰስትምና ፀጋን በማካፈል
ብርቱ ውን ያስነሳል ከትውልዱ መሃል (፪)
የሙሴ በረከት ደርሶዋል ለኢያሱ
አምላክ በቃ ብሎ ሊጣራው ወደርሱ
ኢያሱን አቆመው በበረታ ጸጋ
የነገስታት ንጉሥ አልፋና ኦሜጋ (፪)
መጎናጸፊያውን ለኤልሳ ትቶለት
ኤሊያስ ቢኤድም ቢነጠቅ በእሳት
እጥፍ ድርብ ጸጋ ከሁሉ የሚልቅ
አምላክ ስለ ሰጠው ፈጽሞዋል ድንቃድንቅ (፪)
እኔ ብቻ በቀር ማነው ያለው ሌላ
ትጉን አገልግሎት ዝናሩ ያላላ
እንዲ አትበሉ እግዚአብሔር ዘገየ
ይሾማል ለቤቱ ጠላት ዓይኑ እያየ (፪)
ቀድሰን ዘምረን ወንጌሉን መስክረን
ወደ ሰማዩ ቤት ደሞ እኔዳለን
እግዚአብሔር ያስነሳል ዳግም እንደገና
ዘመኑ የዋጀ እጅጉን የጸና (፪)
ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ
✝️ለባለ ማህተቦች✝️ሼር ያድርጉ↗️
✨✨✨✨✨✨✨
✝️#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ✝️
✨✨✨✨✨✨✨