▓▓▓▓▓▓▓ ግጥM ▓▓▓▓▓▓▓
"ሂጂ ፈቅጃለሁ"
የውስጤን ላይ ሸማ አንቺው ጀምረሽው
በሰፊው ልቤ ላይ ባጭር ከቀጨሽው
……………………ደርቢው አልልም
ድሮም አጭር ነገር ከሰው ላይ አያምርም!!
እውነቴን ነው ውዴ
ለሰው ልጆች ሁሉ
ያልተመለሰልን ብዙ ጥያቄ አለ
አንቺም ካልተመቸሽ
የልቤ ላይ ሸማ ላንቺ ካልተባለ
መሄድ ትችያለሽ!
አልከለክልሽም !
ለኔ የሞተብሽ ስሜትሽ ካየለ
ግን ማወቅ ያለብሽ?
ገፍቶ በመሄድ ላይ ብዙ መውደቅ አለ
እውነቴን ነው ውዴ
በዚች ዓለም ስኖር መገፋት ቢኖርም
በፍቅር መረገጥ ሽንፈት አይወክልም
ደሞ ይሄን ስልሽ
እንዲገባሽ እንጂ እንድትመጪ አደለም!
ሂጂ ፈቅጃለሁ
በኳታኙ እግርሽ እንዳሻሽ ሁኝበት
ድሮም መሄድ እንጂ መምጣት አታውቂበት
ስለዚህ ፍቅሬ
ጥለሽኝ ብትሄጅም
መነሳቴ አይቀርም መቃብር ፈልፍየ
በፍቅር ዓለም ውስጥ
ከሞት በኃላ ነው 'ሚኖረው ትንሳኤ ።
✍ Abu
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 😘
አዘጋጅ፦ ፍቅሬን በግጥM
➳➳ ከወደዱት ለሌሎች ሼር ያድርጉ !! ➢➢
Join us 👉👇 https://t.me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA
"ሂጂ ፈቅጃለሁ"
የውስጤን ላይ ሸማ አንቺው ጀምረሽው
በሰፊው ልቤ ላይ ባጭር ከቀጨሽው
……………………ደርቢው አልልም
ድሮም አጭር ነገር ከሰው ላይ አያምርም!!
እውነቴን ነው ውዴ
ለሰው ልጆች ሁሉ
ያልተመለሰልን ብዙ ጥያቄ አለ
አንቺም ካልተመቸሽ
የልቤ ላይ ሸማ ላንቺ ካልተባለ
መሄድ ትችያለሽ!
አልከለክልሽም !
ለኔ የሞተብሽ ስሜትሽ ካየለ
ግን ማወቅ ያለብሽ?
ገፍቶ በመሄድ ላይ ብዙ መውደቅ አለ
እውነቴን ነው ውዴ
በዚች ዓለም ስኖር መገፋት ቢኖርም
በፍቅር መረገጥ ሽንፈት አይወክልም
ደሞ ይሄን ስልሽ
እንዲገባሽ እንጂ እንድትመጪ አደለም!
ሂጂ ፈቅጃለሁ
በኳታኙ እግርሽ እንዳሻሽ ሁኝበት
ድሮም መሄድ እንጂ መምጣት አታውቂበት
ስለዚህ ፍቅሬ
ጥለሽኝ ብትሄጅም
መነሳቴ አይቀርም መቃብር ፈልፍየ
በፍቅር ዓለም ውስጥ
ከሞት በኃላ ነው 'ሚኖረው ትንሳኤ ።
✍ Abu
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 😘
አዘጋጅ፦ ፍቅሬን በግጥM
➳➳ ከወደዱት ለሌሎች ሼር ያድርጉ !! ➢➢
Join us 👉👇 https://t.me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA