Репост из: Ethio student online
ኢትዮ ቴሌኮም በቢሾፍቱ የ5ጂ ኢንተርኔት ኔትዎርክ አገልግሎት አስጀመረ‼️
በቢሾፍቱ ከተማ የቱሪዝም ዘርፉን ወደላቀ ደረጃ ለማሻገር ያስችላል የተባለው የ5ጂ አገልግሎቱን የቢሾፍቱ ከተማና የኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ አመራሮች በይፋ አስጀምረዋል።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህወት ታምሩ የ5ጂ አገልግሎት በቢሾፍቱ ከተማ መጀመሩ ከተማዋ በቱሪዝም፣ በንግድና በሌሎችም ዘርፎች ከፍተኛ ዕድገት ለማምጣት የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል።
በከተማዋ የ5ጂ አገልግሎት መጀመር ስማርት ቢሾፍቱን ለመገንባት አስተዋጽኦው ከፍተኛ መሆኑንም ተናግረዋል።
የቢሾፍቱ ከተማ ከንቲባ አቶ አለማየሁ አሰፋ፥ በዓለም አቀፍ ደረጃ የመጨረሻው ፈጣን የሆነውን የ5ጂ አገልግሎት በከተማዋ መጀመር የቢሮ ስራዎችን ለማቀላጠፍ፣ ለተገልጋዩ ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት፣ ስማርት ሲቲን ለመገንባት፣ የቢሾፍቱን የቱሪስት መስህብነት አቅም ለማሳደግና በርካታ አገልግሎቶችን ለማከናወን የሚረዳ መሆኑን ገልፀዋል።
130 ዓመታት ለህዝቡ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው ኢትዮ ቴሌኮም ዓለማችን የደረሰችበትን የ5ጂ ኔትዎርክ አገልግሎት በቀጣይ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ለማስጀመር እየሰራ መሆኑ ተገልጿል።
ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️
https://t.me/+D9SY4VrC-i8wYTc0