TGStat
TGStat
Введите текст для поиска
Расширенный поиск каналов
Язык сайта
Russian
English
Uzbek
Вход на сайт
Каталог
Каталог каналов и чатов
Поиск каналов
Добавить канал/чат
Рейтинги
Рейтинг каналов
Рейтинг чатов
Рейтинг публикаций
Рейтинги брендов и персон
Аналитика
Поиск по публикациям
Мониторинг Telegram
✞ የመዝሙር ግጥሞች ✞
14 Dec 2024, 13:40
Открыть в Telegram
Поделиться
Пожаловаться
✥ ታትመሻል ✥ — ✟ ጋሜል- ዘ ኦርቶዶክስ ✟
06:44
ታትመሻል
ታትመሻል በሰው ልቦና
የደካሞች ምርኩዝ ነሽና
ላመስግንሽ በአዲስ ዝማሬ
እመቤቴ ገና ነው ፍቅሬ
የተፅናናንብሽ የድሆች ማረፊያ
ነፋስ ውቅያኖሱን ወጀቡን መቅዘፊያ
ወርሰናል ስምሽን ከወርቁ መዝገብ ላይ
ወለድሽልን ድንግል የሕይወትን ፀሐይ
ፅዮን ብለናል ነሽ መማፀኛችን
ሞትን አናይም ካለሽ እናታችን /2/
ቀስተ ደመናዬ ሁነሽ ምልክቴ
አለሁ እስከዛሬ ባንቺው በእመቤቴ
ልጅሽን አምኜ ምን ይጎልብኛል
ያስጨነቀኝ ሁሉ ይታዘዝልኛል
ተከቧል ተራራው በብሩህ ደመና
የአብ ልጅ ክርስቶስ ባንቺ ወርዷልና
ይባቤ ምስጋና አፋችን ይመላ
መቅደስ አላየሁም ድንግል ካንቺ ሌላ
የከሳሼን ጉልበት ፅናቱን ሰብረሻል
የአዳም ልጅ ከሲኦል ከሞት ወጥቶብሻል
ጣፈጣት ለነፍሴ የማህጸንሽ ፍሬ
ስጠራሽ እኖራለሁ በያሬድ ዝማሬ
1.5k
0
38
9
×