✞ አርሴማ ቅድስት ወሰማዕት ✞
አርሴማ ቅድስት ፪ ወሰማዕት
ወሰማዕት ፭ አርሴማ ቅድስት ኧኸ ፫
ከምድር ሙሽርነት ይበልጣል የሰማይ
በማለት ወሰነች ሰይፍ ስለቱን ሳታይ
የሰማዕትነቷ ፅኑ መከራዋ
ተቀበለችበት የክብርን ፅዋ
አዝ=======
የዚህችን ዓለም ጣዕም ፍፁም ያልበገራት
የንጉስ ግልምጫ ከእግዚአብሔር ያልለያት
አምላኯን መረጠች መክሊቷን አትርፋ
አክሊል ተቀዳጀች ለእምነት ተሰልፋ
አዝ=======
የማይታየውን ለመውረስ ተብሎ
በሚታየው ዓለም ይበዛል ተጋድሎ
የሰማዕታት ዋጋ ይኸው ነው ውጤቱ
በዚህ ምድር ሳይሆን በሰማይ ነው ቤቱ
አዝ=======
ውበት ከንቱ ነው ደም ግባት ሀሰት
እንዲህ ብላ ፀናች አርሴማ ቅድስት
ያመነችው ጌታ በሰጣት ቃልኪዳን
ልዩ እናት ሆናለች ትውልዱን በማዳን
አርሴማ ቅድስት ፪ ወሰማዕት
ወሰማዕት ፭ አርሴማ ቅድስት ኧኸ ፫
ከምድር ሙሽርነት ይበልጣል የሰማይ
በማለት ወሰነች ሰይፍ ስለቱን ሳታይ
የሰማዕትነቷ ፅኑ መከራዋ
ተቀበለችበት የክብርን ፅዋ
አዝ=======
የዚህችን ዓለም ጣዕም ፍፁም ያልበገራት
የንጉስ ግልምጫ ከእግዚአብሔር ያልለያት
አምላኯን መረጠች መክሊቷን አትርፋ
አክሊል ተቀዳጀች ለእምነት ተሰልፋ
አዝ=======
የማይታየውን ለመውረስ ተብሎ
በሚታየው ዓለም ይበዛል ተጋድሎ
የሰማዕታት ዋጋ ይኸው ነው ውጤቱ
በዚህ ምድር ሳይሆን በሰማይ ነው ቤቱ
አዝ=======
ውበት ከንቱ ነው ደም ግባት ሀሰት
እንዲህ ብላ ፀናች አርሴማ ቅድስት
ያመነችው ጌታ በሰጣት ቃልኪዳን
ልዩ እናት ሆናለች ትውልዱን በማዳን