✞ ከሀጢያተኛው ድንኳን ✞
ከሀጥያተኛው ድንኳን ቅዱሱ ቆመሀል
ልጄ የት ነው ብለህ እኔን ፈልገሀል
አንተ ስላለኸኝ ቀሏል መከራዬ
ለኔ ያደረከው ብዙ ነው ጌታዬ (2x)
እንኳንስ አርገኸኝ ጌታዬ ሙሉ ሰው
እንዲሁም ይህን ነበር ልቤ ሚናፍቀው
የዘመናት ሸክም ቀረ ጉስቁልና
የጠፋውን ድሪም አግኝተሀልና
አዝ=====
ባገኸኝ ጊዜ ሸፍናኝ በለሷ
ከፊትህ ያነበብኩት ፍጹሞ አይረሳ
ከዚህ የበለጠ ታይለህ ምትለኝ
ዓይንህ ይናገራል እንደማትረሳኝ
አዝ=====
ምን አለኝ ብለህ ነው ደጄን የምትመታ
እኔ ደካማ ነኝ አንተ ቅዱስ ጌታ
ከእንግዲ አላርስም ምንጣፌን በእንባ
መንጦላይቴን ከፍተህ በምህረት ግባ
አዝ=====
እኔኮ አውቅሀለው ሁሉን ስታፈቅር
የአናብስቱን ጉድጓድ የሞት አዋጅ ስትሽር
እንዲህ እያለ ነው የሚቀኘው ውስጥ
ኢየሱስ ክርስቶስ ምግብና መጠጤ