🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
ልብ አንጠልጣይ የ ፍቅር ታሪክ በመልካም ልቦች የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ💟
⭐️ክፍል 🟰7️⃣
አንድ ቀን ቆላ ውዬ እየተመለስኩ እናቷን አገኘኋት ና እስቲ አንተ ያቺ ዘረ ቢስ ልጅ እናንተጋ ናት አሉ ያቺ እመቤት ተብዬዋ ሴተኛ አዳሪ የማንንም ዲቃላ እየሰበሰበች ታኖራለች አደል ላንተ አልበቃ ብሎ ጭራሽ እሷንም ቀላቀለች ቆይ ግዴለም ዋጋችሁን ነው ምሰጣችሁ ብላ ዛተችብኝ።
መልስ ለመመለስ እራሱ አቃተኝ አውጥተሽ የጣልሻትን ልጅ መኖሪያ በሰጠቻት እንደዚህ መሳደብሽ ልክ ነው እናት አደለሽ እንዴ አንጀትሽ ከምንድነው የተሰራው አልኳት።
አይ እንግዲ እኔ እንደሷ አይነት ልጅ አልወለድኩም እናቷን ፍርድ ቤት ለፍርድ ቤት ምታንከራትት ልጅ ልጅ ትባላለች እንዴ ይቺ ሴጣን እግዚአብሔር ስንቱን ሲወስድ ለሷ ቦታ አጥቶ ነው እስካሁን ያልገደላት አለችኝ።
አነጋገሯ አስገረመኝ ለኔ እናት ስገረም ጭራሽ የባሰም አለ እንዴ ብዬ አልፊያት ሄድኩ ቤት ስገባ መደብ ላይ ጭብጥ ብላ ተኝታ አየኋት ውስጤ ልውስ አለ አቃተኝ።
አጨዳ በቀን 5 ብር ነበር ምውለው ማሳው ታጭዶ እስኪያልቅ ድረስ 50 ብር ሞላልኝ 20 ብር ለእመቤት ሰጠኋት በዛ ሰአት 20 ብር በጣም ብዙ ብር ነበር የቀረኝን ብር ይዤ ወደገበያ ወጣሁና ለልጅቷ ሜትር 12 ብር ነበር
2 ሜትር በ24 ብር ቀሚስ አሰፋሁላት ስታየው አበደች በደስታ ዘለለች ፍርድ ቤት ይሄንን የተቀዳደ ልብስ ለብሰሽ ስትሄጂ ይኑቅሻል ሀሳብሽንም አይሰሙሽም ቢያንስ ግን የተቀደደ ልብስ ካለበሽ ምን እንደምታወሪ ይሰሙሻል ያዝኑልሻል አልኳት አመሰገነችኝ ስትስቅ የፊቷ ብርሀን ያንፀባርቃል ።
ከዛን ቀን ቡሀላ ፍርድ ቤት ከእናቷጋ ልትካሰስ ስትወጣ እኔ እስከፍርድ ቤት ማውጣት ጀመርኩ ።
በዛ ምክንያት እናቷ ጥምድ አድርጋ ያዘችኝ በየጊዜው አንተንና እሷን አንድ ቀን አስደፋችኋለሁ እያለች ትዝትብኝ ጀመር።
ቀስ በቀስ እኔ እየወደድኳት መጣሁ ለምን እኔ አላገባሽም ቤት ባይኖረንም አንድ ቀን ይኖረን ይሆናል ብዬ ጠየኳት እንቢ አለችኝ
ቆይታ ስታስበው ግን ቢያንስ ብቸኝነቷን መርሳት ፈልጋ ነበርና እሺ አለችኝ።
ከዛ ለእመቤት ነገርናት እዛው ግቢዋ ውስጥ እቃ ምናምን ምታስቀምጥበት በር የሌለው ቤት ነበር እና እሷ ውስጥ መኖር ትችላላችሁ አለችን።
እሺ ብለን ባዶ እጃችንን እሷ ውስጥ ገባን እንጨት ሰብስቤ መጣሁና ለበሩ እንደመዝጊያ ሚሆነን ማታ ማታ ምናቆመው ጠዋት ጠዋት ደሞ አንስተን ወደጎን አድርገን ምናስቀምጠው በር ሰራሁለትና እመቤት ቡና አፍልታ አስገባችን የዛን ቀን አብረን አደርን ጎዳና ላይ ስታድር ብዙ ወንዶች ሊደፍሯት እና ትንሽ ትንሽ ገንዘብ እየሰጡ አብረዋት እንድታድር ይጠይቋት እንደነበር በምግብ ሁላ ካልደለልንሽ እንደሚሏት እሰማ ነበር ቢሆንም ግን እሷ እንቢ ባይ ነበረችና ከነ ክብረ ንፅህናዋ አገኘኋት።
የሀገሬው ሰው እንደተጋባን ሲሰማ መሳቂያ መሳለቂያ ቡና መጠጫ አደረጉን ለራሱ ሰው ቤት እየለመነ ጎኑን እያሳረፈ ጭራሽ ሌላ ዲቃላ ይጨምራል እንዴ እያሉ ያወሩብን ጀመር አጎቴ ይሄን ሲሰማ ተበሳጨ እንዴት ለራስህ ሳትሆን ሌላ ሸክም ትጨምራለህ ልጅ ይመጣል በምናችሁ ልታሳድጉት ነው አለኝ።
ችግር የለም እሱን አልኩት።
ምግብ ምንሰራበት እቃ እንኳን ስለሌለን ምንበላው ምንጠጣው እመቤትጋ ነው።
በዛ መሀል ባለቤቴ እንደዛ እየተንከራተተች ከናቷጋና ከእንጀራ ካባቷጋ እየተካሰሰች እያወቀ ሚፈርድላት ዳኛው አብረሽኝ እደሪና ነገውኑ ላንቺ ላስፈርድልሽ አላት ሚስቴ ሞቼ እገኛለሁ ብላ እንቢ አለች።
ከዛ በቃኝ ሳትል የበላዩጋ ሄዳ ከሰሰችው ፈጣሪ ከሷጋ ነበርና ተሳካላት።
አባቷ ሲሞት ያለውን መሬት እንዳለ በሷ ስም አስደርጎት ነበር እድሜዋ ስላልደረሰ እናቷ መሬቱን የማስተዳደር መብት ስለተሰጣት ለካ በዛ ልክ ምታሳድዳትና ምትጠላት ስታድግ መሬቱን ከምትቀማኝ ቶሎ ሞታ በተገላገልኩ ብላ ኖሯል ።
ያው ግን ፈጣሪ ከሷጋ ሆነና 4 የእርሻ መሬት 1 የጌሾ እርሻ እና አባቷ በህይወት እያለ ከቤታቸው ጀርባ በቆሎ እየዘራ ሚጠቀምበትን መሬት ሰጧት እናቷ እዛ መሬት ላይ ከረገጠች እንደምትታሰር አስጠነቀቋት ።
ከዛን ቡሀላ ከእመቤት ቤት ወጣንና በቆሎ ሚዘራበት የነበረው እርሻ ላይ በጨርቅ ጋርደን ቤት ሰራን አጎንብሰን እንገባለን አጎንብሰን እንወጣለን ።
ከእመቤት ቤት ጉልቻ ከአጎቴ ቤት ድስት ና ምጣድ ተሰጠን ግን እኛ ምንሰራው ሁላ አልነበረንም።
በዛ ሁላ መሀል ለካ እኛ ሳናውቅ ሚስቴ እርጉዝ ነበረች ።
🔻ክፍል ስምንት ነገ ማታ3️⃣🟰3️⃣0️⃣ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
💔 @MELKAM_LBOCH13 💔
💔 @MELKAM_LBOCH13 💔
➖የዩቲዩ ገፃችን➖
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333

💗 ጥቁር ልብ 💗