🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
ልብ አንጠልጣይ የ ፍቅር ታሪክ በመልካም ልቦች የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ💟
⭐️ክፍል 🟰3️⃣
የዛን ምሽት ሳናወራ አደርን ጠዋት እንደተነሳሁ ከሱጋም ከኔጋም ደለትኩት ቴሌግራም ውስጥ ከሁለቱ የሴት ጓደኞቼና ከዴቭ ውጪ ማንንም አላወራም ።
ስልኬን ሁላ ሁለቱ የክላሴ ልጆችና ቤተሰቦቼ ከዛ ውጪ ዴቭ ብቻ ነው የሚያቀው መደዋወል መፃፃፍ social media መከታተል የሚባሉት ነገር ላይ ብዙም ጎበዝ አደለሁም።
ከክላስ ተማሪዎቼ ውስጥም ቢሆን ማንም ደፍሮ ሊያናግረኝ የሚሞክር የለም።
ማታ ላይ ከዴቭጋ በደንብ ለመግባባት ይረዳን ዘንድ የተወሰነ ነገር እናወራለን 4 ሰአት ሲል ሰአቴን ጠብቄ እተኛለሁ።
የሰአት አጠቃቀሜ እንዴት ነበር መሰላችሁ ጠዋት ትምህርት ቤት እሄዳለሁ።
ከትምህርት እንደተመለስኩ ልብሴን ቀያይሬ መክሰሴን በልቼ ከናቴጋ አወራለሁ።
12 ሰአት ሲሆን ክፍሌ እገባና እስከ 2 ሰአት የቤት ስራዎቼንና ጥናቴን እጨራርስና 2 ሰአት ላይ እራት ለመብላት ወደሚጠብቁኝ ቤተሰቦቼ ሄጄ እራቴን እበላለሁ።
አባቴ ቀኑን ሙሉ ስራ ስለሚውል ከእራት ቡሀላ ነው ከሱጋ የማውራት እድል የማገኘው ።
እሱን እንደጨረሰኩ ወደክፍሌ ገብቼ tv እያየሁ 4 ሰአት ሲሆን እተኛለሁ።
ብቻ life እንደዛ ነበር እላችኋለሁ።
ያው በነጋታው ቅዳሜ ስለነበር እቤት ዋልኩኝ።
እሁድ ለምን እንደሆነ ባይገባኝም ዴቭ እቤት መጥቶ ነበር በጣም ትልቅ ጥያቄ ሆነብኝ አባቴ አደለም ቀርቶ የውጭ ሰው ዘመዶቻችን እንኳን ሲመጡ ደስ አይለውም ዘመድ እኛ ቤት መጥቶ ሲጫወት በአል ሲያከብር አይቸ አላቅም እኔና እናቴም ብንሆነ የቤቱ እስረኞች ስለሆንን ቤታችን ውስጥ ገባ ወጣ የሚበዛበት አይነት ቤተሰቦች አደለንም።
ታዲያ የዴቭ ቤት መምጣት ግርምትን የፈጠረብኝ ለዛ ነበር።
እናቴን እንዴት መጣ ብዬ ጠየኳት እኔጃ ልጄ ብቻ ግን ጥሩ ልጅ ይመስላል ልብሶቹም ብራንድ ናቸው እራሱን በጣም ይጠብቃል ተቀጥሮ ሚሰራ ሹፌር አይመስልም አለችኝ እሷም።
ጥያቄዬን በጥያቄ ስትመልስልኝ ዝም አልኩኝ።
ከዴቭ በጣም ከሚገዛኝ ነገሩ ዝምታውን እወድለታለሁ ፊቱ ላይ የሚታየው እርጋታ ቀልብን ይገዛል ብቻ ብዙም ሳያወራ አባቴ ያወራውን ሲያዳምጥ ወደማታ አካባቢ ላይ ካባቴጋ ተያይዘው ወጡ።
ሰኞ ውጤት ለማየት ትንሽ ጓጉቼ ስለነበር ቀስቃሽ ሳያስፈልገኝ በጠዋት ተነስቼ ለባበስኩ ቀድሜ ጨራርሼ ዴቭ እስኪመጣ መጠበቅ ጀመርኩ።
ሲመጣ ተነስቼ ወጣሁ። ትምህርት ቤት እስክንደርስ ካለወትሮው በጣም እያሳቀኝ ነበር።
ክላስ ስገባ እያሱ ቀድሞ ገብቶ ቁጭ ብሉ ደብተሩን እያገላበጠ ነበር።
ስገባ ቀና ብሎ አይቶኝ ፊቱን ቋጠረብኝ።
ዝም ብዬ ሄጄ ቦታዬ ላይ ተቀመጥኩ።
ሁሉም አስተማሪ ፈተናዎቻችንን የሚሰጡበት ቀን ነበርና የገባው ሁሉ ውጤት እየተናገረ ይሰጡን ጀመር በሚገርም ሁኔታ ሁሉንም ፈተናዎች ከፍተኛ ውጤት ያመጣው እሱ ነበር አይገርምም ለመጀመሪያ ጊዜ ክላስ ውስጥ የሚበልጠኝ ተማሪ ተገኘ።
መናደድ ሲገባኝ እኔ ግን ደስ አለኝ እንዴት ስለበለጠኝ ደስ እንዳለኝ አላውቅም ግን ውጤቶቹን ሳያቸው ደስ ይላል የበለጠኝም አንድ ትምህርት ብቻ ነው ያውም በአንድ ነጥብ።
🔻ክፍል አራት ነገ ማታ3️⃣🟰3️⃣0️⃣ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
💔 @MELKAM_LBOCH13 💔
💔 @MELKAM_LBOCH13 💔
➖የዩቲዩ ገፃችን➖
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333
https://www.youtube.com/@Kezerareaction33
💗 ኤልዳና 💗