🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
ልብ አንጠልጣይ የ ፍቅር ታሪክ በመልካም ልቦች የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ💟
⭐️ክፍል 🟰3️⃣2️⃣
ሳንገናኝ አንድ ሳምንት ቆየን በቃ የመጨረሻ የመከፋት ስሜት ውስጥ ገብቼ ነበር።
ከሳምንት ቡሀላ ዴቭ መጥቶ ይዞኝ ወጣና ከእዩጋ አገናኘኝ ችግራችሁን ተነጋግራችሁ ፍቱ እያንዳንዷ ክፍተት ፍቅራችሁን ታደበዝዛለች አለኝ።
እኔ ካፌ ክፉ ቃል ማውጣት ስላልፈለኩ ዝም አልኩኝ እዩ ማውራት ጀመረ።
ቆይ የምር እኔን በቃል ጠርጥረሽኝ ነው አንቺን በሷ ምተካሽ መስሎሽ ነው አለኝ።
ዝምም አልኩት:
ኤልዱ እኔ ካስፈለገ በምወዳት እናቴ እምልልሻለሁ አንቺን በማንም አልተካሽም አንቺ ህይወቴ ውስጥ ያለሽው ትልቋ መሰሬቴ ነሽ ለኔ ብቻ ሳይሆን ለናቴም ደስታ ነሽ ግን በቃ ቃልን ግዴታ ማውራት ስለነበረብኝ ነው ያወራኋት ብሎ ስልኩን ከፍቶ ፎቶ አሳየኝ ቃል እራሷን ለማጥፋት ሙከራ አድርጋ እንደነበር የሚያሳይ ፎቶ አሳየኝና እኔ አላወራሽም ብያት ፊት ነስቻት ነበር እሷ ግን እራሷን ልታጠፋ ሞከረች ድጋሜ ማላወራት ምርቃት ምዘጋት ከሆነ እራሷን እንደምታጠፋ እያለቀሰች ስትለምነኝ እኔም ሀገሩን ስለማታቀው ከቤተሰብ መነጠል ብቸኝነት ስለሚፈጥርባት ነገሮች ሲደራረቡ ሆድ ከሚብሳት ብዬ ነው የቀረብኳት አንቺ እንደምታስቢው በሌላ ነገር አደለም ደሞ በጣም ታማሚ ሆናለች እዛ ከሄድን ቡሀላ በየጊዜው ነው እራሷን ምትስተው ስለምታሳዝነኝ ነው አለኝ።
እኔ ውስጤን በምንም ቃላት ማስተካከል አልቻልኩም ክፍት እንዳለኝ ስለነበር በድጋሜ ዝምታን መረጥኩ እሱ የሆነውን ያልሆነውን ወሬ እየፈጠረ ሊያስቀኝ ሊያዝናናኝ ሲሞክር አልቻልኩም ያ በከፋኝ ሰአት ከጎንደር አዲስ አበባ ለኔ ብሎ መምጣቱን አሰብኩና ታረኩት።
አብረን እናምሽ በቃ ዴቭ ቤት እንሂድና እዛ እንደር እስክሄድ አብረን እንሁን አለኝ እሺ ብዬ ተያይዘን ከዴቭጋ ሶስታችንም ሄድን ዴቭ አድርሶን ሊሄድ ሲል እዩ አብሮን እንዲያድር ሌሊቱን ሙሉ ስንፍታታ ማደር እንደምችል ነገረውና ወደ ውስጥ ገባን ዴቭ ወጥቶ መጠጥ ይዞ መጣ መሬት ላይ ክብ ሰርተን ከተቀመጥን ቡሀላ ጨዋታ እየተጫወትን አንዴ ሚስጥር መናገር አንዴ መታዘዝ (ተነስቶ መጨፍር: መዝፈን: ) ብቻ እንዲሁ ሆዳችን እስኪቆስል ስንስቅ አመሸን ዴቭ ተነሳና ሶፋ ላይ ተኛ እኔና እዩ ቁጭ ብለን አሰብከው ግን ወደፊት እኔና አንተ የራሳችን ቤት ኖሮን አብረን ውለን አብረን አድረን በቃ ሳንለያይ ሁሌ እየተያየን በፍቅር ብዙ አመት ስንኖር አልኩት እዩ ፈገግ ብሎ አቅፎ እየሳመኝ ትንሽ ግዜ ብቻ ነው የቀረን ታገሽ አለኝ።
ሁለታችንም እንቅልፋችን ስላልመጣ መተኛት አልቻልንም ዴብን መበጥበጥ ጀመርን ትራስ እየወረወርን አላስተኛ አልነው ፊቱን አዙሮ ተኝቶ እረፉ ሊለን ሲዞር አይኑ ቀልቷል ደንግጬ ትኩር ብዬ ሳየው አታይም እንዴ እንቅልፌ በጣም ስለመጣኮ አይኔ ሁላ ቀለ አለ ነገሩ ባይዋጥልኝም ዝም አልኩ።
ጠዋት አብረን ቁርስ በላንና እዩ እናትጋ ሄድን ተአምራዊ ሴት ማለት እሷ ናት በቃ በየቀኑ ታስገርመኛለች ዴቭን ደሞ እንዴት እንደምተወደው:
ሱቋ ስንሄድ ለመጣው ሰው ሁላ ፊቷ ፍክት እንዳለ ነው እጇ ስስት አያቅም ትጎጃለሽኮ ለምን እንደዚህ ትመዝኛለሽ ስትባል ከብዛት አገኘዋለሁ ትላለች።
በቅርቡ የከተማዋ ባለሀብት አንቺ ነሽ እያልኳት ተጨዋወትንና እኔና ዴቭ እናቴጋ ሄድን እዩ እናቱን እያገዛት እዛው ቀረ።
ሌላ ሳምንታቶች ተቆጠሩ እኔና እናቱ እዩ ከመሄዱ በፊት ተለቅ ያለ ቆንጆ ቤት ተከራይተን ሰርፕራይዝ ለማድረግ አሰብንና እዛው ከስራ ቦታዋ ጀርባ ባለ አንድ መኝታ ቤት አገኘንና ያጠራቀመችውን ገንዘብ እንዳለ እቃ ላይ አዋለችው እኔም ያቅሜን አገዝኳት ቀኑን ሙሉ እዩ ሱቅ ውስጥ ሲሸጥ ዋለ እኛ ደሞ ቤት ስንቀይር ዋልን ማታ ላይ አስተካክለን ለመጨረስ ስላልቻልን እዩን ከሱቅ ቀጥታ ይዤው ዴቭ ወደተከራየው ቤት ሄድኩና እዛው አደርን ጠዋት እሱን ሱቅ አድርሰን እኔ ወደ አዲሱ ቤት አመራሁ እናቱ ቀድማኝ ደርሳ እያዘገጃጀች ነበር አጋዦች ጠርተን ቤቱን አሰማመርነው መኝታ ቤቱንም ሳሎኑንም ፏፏ አደረግንና ቤቱን ቄጤማ ጎዝጉዘን ቡና አቀራርበን ስንጨርስ እዩን ከሱቅ ይዤው ለመምጣት ሄድኩኝ ማታ ሁለት ሰአት ላይ ሱቃችንን ዘግተን አንድ ምኔድበት ቦታ አለን ብዬ ይዠው ሄድኩ።
እናቱን ውስጥ ቁጭ ብላ ሲያያት ግራ ገብቶት ወደ ውስጥ ገባ ሲገባ የራሱ ሽልማቶችና ፎቶዎቹ ውስጥ ተሰቃቅለው ሲያያቸው ግራ ገብቶት ነበር ነገሩን ስንነግረው በደስታ አለቀሰ እንባውን ማቆም እስኪያቅተው ድረስ እያቀፈን ደስታውን ገለፀለን ቡና ጠጥተን እስቅንጨርስ ማመን አቅቶት አስሬ ግን ከምራችሁ ነዋ እያለ ሲጠይቀን ነበር።
ቡናው ሲያልቅ ዛሬ የቤት መመረቂያ ሁላችንም እዚሁ ነው ምናድረው ተባለ እዩ እጄን ያዘኝና አየር ወስደን እንምጣ ብሎ በዛ በማታ ይዞኝ ወደ ውጭ ወጣ ጥብቅ አድርጎ አቅፎኝ ስለሁሉም ነገር አመሰግናለሁ የወደፊት ህልሜን በሙሉ ቀድመሽ እያሳየሽኝ ነው አንቺ ለኔ በረከቴ ነሽ ህይወቴ ውስጥ ከገባሽ ቀን አንስቶ በየቀኑ ጥሩ ነገሮች ወደኔ ይመጣሉ ከምስጋና በላይ ላንቺ ምንም ላደርግልሽ አልችልም የእናቴ ምርቃት ነው አንቺን የሰጠኝ ብሎ አለቀሰ አብረው እያለቀስኩ እንባውን ጠረኩለት ትንሽ እስክንረጋጋ ሁለታችንም ጨረቃዋ ላይ አፍጥጠን ውጭ ቁጭ አልንና ተመልሰን ገባን።
ነገሮች አሪፍ እየሄዱ ነው አሁን ጥሩ ላይ ነኝ ብዬ ሳስብ የእዩ መሄጃ ቀን ደረሰና ተመልሶ ወደግቢ ሄደ።
በዛን ሰአት ላይ ከእናቴጋ ቁጭ ብዬ አወራሁ ለምን ካባቴጋ አትፋችም ከዚህ በላይ ምን እስከሚመጣብሽ ነው ምትጠብቂው ሴት ልጅ ለውሳኔ ከዘገየች ዋጋ ትከፍላለች አልኳት።
እናቴ ፈገግ ብላ አየችኝና ልጄ እየበሰልሽ ነው ግን እኔ አባትሽን መፍታት አልችልም
ለምን??!
ምክንያቴን መናገር አልፈልግም ግን ልጄ አሁን ሳይሽ እያደግሽልኝ እየደረሽልኝ ጓደኛ እየሆንሽኝ ስለሆነ ካንቺ መደበቅ አልችልም እኔና አባትሽ ባለትዳሮች ሆነን ለብዙ አመታቶች ብንቆይም ይሄ ሁላ የምታይው ሀብት ላይ እኔ ምንም ድርሻ የለኝም እኔ አባትሽን ከፈታሁት ባዶ እጃችንን ነው ምንቀረው አለችኝ።
እ እማ ምንድነው ምታወሪው ሚስቱኮ ነሽ ሙሉ መብት አለሽ እንጂ አልኳት።
አይ የለኝም ከመጋባታችን በፊት በዚህ ተስማምቼ ነው የገባሁት አለችኝ ።
ቤተሰቦቼ በላዬ ላይ ፊልም ሲሰሩ መኖራቸው አስገረመኝ እውነት እናቴ ለገንዘብ ብላ እራሷን ሸጣ እየኖረች ነው ወይስ ለኔ መስዋት እየከፈለች ለነገሩኮ እኔ የመጣሁት ቡሀላ ከመጀመሪያው ምን አስባ ነው ያገባችው::
በቃ አንዴ መጥፎ ነገር ወደኛ መምጣት ከጀመረ ማቆሚያ የለውም ያለሁበት ሁኔታ አስገረመኝ ችግርን ስለማላቀው አካብጄው ነው ወይስ ነገሩ የምር ከብዶ አላቅም ብቻ ግን ሲከፋኝ መሸሸጊያዬ ወይ ዴቭ ነው አለበለዚያ የእዩ እናትጋ ሄዶ ቁጭ ማለት ከሁለቱ ውጭ አማራጭ የለኝም ።
እንደለመድኩት ሄድኩና እንደከፋኝና የተፈጠረውን በሙሉ ነገርኳት አባትሽን አውሪው እናትሽን ነፃ አውጫት አለችኝ።
💗 ኤልዳና 💗