ፅጌሬዳ
ክፍል 14
አቶ ሳሙኤል ደነገጡ ማሂ ምታደርገው ጠፍቷት መርበትበት ጀመረች እናቴ አንገቷን ደፍታ እያለቀሰች ዝም አለች።
እኔ የባሰ እንባዬ መጣ አባቴ ከስንት ጊዜ ቡሀላ አይኔን ስታየው እንደዚህ ትሆናለህ አልኩኝ።
ዝም በል ድራሽህ ይጥፋ ከሰው በላይ አንቀባርሬ ባሳድግህ አዋረደክኝ ቤተሰቤን በተንከው ክብሬን አሳጣኸኝ እንዳንተ አይነቱን ከመውለድ ምነው መሀን ሆኜ በቀረሁ አለ በተሳሰረ አፉ።
አቶ ሳሙኤልና እህቴ አባቴን እየጎተቱ ይዘውት ወጡ ።
ወይኔ ወንዱ እያለ አባቴ እንደሴት ማልቀስ ጀመረ።
በስማም አባቴ በሰው ፊት ስሜቱን አያሳይም ነበር ዛሬ ሰክሮ እንደዚህ እየተዘላገደ እንደሴት ቁጭ ብሎ ሲያለቅስ ሳየው ሀሞቴ ፍስስ አለ::
ቀጥታ በዛ በምሽት ከቤት ወጣሁ ወዴት እንደምሄድ አላቅም።
እንባዬን በሁለት እጄ ከፊቴ ላይ እየጠረኩ በፍጥነት መራመድ ጀመርኩ ማሂ ከኋላይ እየጠራችኝ ትከተለኛለች እኔ ዝም ብዬ ወደፊት ሄዳለሁ ከኋላዬ ተንደርድራ መጣችና ያዘችኝ የት ልትሄድ ነው አለችኝ እየተቆጣች ።
በቃ አባቴን እንዲህ ሆኖ ከማየው እንደለመድኩት ጎዳና ላይ ባድር ይሻለኛል ጎዳናው ለኔ አዲስ አደለም ተመለሽና ወደቤት ግቢ ብያት አልፊያት ሄድኩ ።
ማሂ በድጋሜ ቆጣ አለችና ቆይ እዚህ ድረስ መተን ከዛ ሁሉ ችግር መከራ አልፈህ አሁን ወዴት ነው ምትሸሸው እንደለመደከው ጥለሀቸው ልትሄድ ነው እናትህን ስታይ እንኳን ምንም አይሰማህም እንዴ ቆይ ምን ያህል ጨካኝ ብትሆን ነው አለች።
በቃ ነገረኩሽኮ አባቴን እንዲህ ሆኖ ከማየው ሞቴን እመርጣለሁ አበቃ።
ተከተለችኝና በቃ እሺ መኪና ውስጥ እንደር በፈጠረኽ በቃ እሺ በለኝ አለች እሺ አልኳት ።
ማልልኝ ቤት ደርሼ ልምጣ አለችኝ ማልኩላት ቤት ገብታ የመኪና ቁልፍና ስልኳን ይዛ ወጣች።
መኪና ውስጥ ገባን ሁለታችንም ከኋላ ቁጭ አለን ማልቀስ ጀመርኩ በቃ በደንብ አልቅስና የውስጥህ ጠባሳ ይቅለልህ አለችኝ።
የዛኔ ባሰብኝ ማሂ አሰብሽው ያንን አባቴን የገደለኩትኮ እኔ ነኝ የሰፈሩ ሰው ቀና ብሎ ለማየት እንኳንኮ አይደፍረውም እእእ ዛሬ እሱ በየአረቄ ቤቱ በየመጠጥ ቤቱ እየሰከረ ሲለፈልፍ ሰው ሲንቀው እናቴ በኔ መጥፋት አልቅሳ ሳትጨርስ አባቴ እንዲህ ሲሆንባት ውስጧ ምን ያህል እንደቆሰለ አሰብሽው እእእ
ቆይ እኔ አሁን ሰው ነኝ ምንም ሳላፍር ደሞ መጥቼ አይናቸውን አያለሁ እእእ ቆይ ወዴት ሄጄ ተንፍሼው ይውጣልኝ።
ማሂ አብራኝ ታለቅሳለች ጨነቃት ቆይ እኔ ምን ላድርግልህ እሺ እእእ በቃ በናትህ ተረጋጋ እኔ እየጨነቀኝ ነው ብላ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች ።
አሳዘነችኝ ተቃቅፈን አነባነው በዛው ማሂ እንቅልፍ ወሰዳት ሌሊት ስለተነሳች ከብዷት ነበር።
እኔ እንዲሁ እንዳፈጠጥኩ ነጋልኝ እንቅልፍ ባይኔ ከዞረ ቀናቶች ተቆጠሩ.......
ማሂን ቀሰቀስኳት ተነሳችና ከመኪና ወርዳ ተናፈሰች ና ቤተክርስቲያን ደርሰን እንምጣና ወደቤት እኔዳለን አለችኝ እሺ አልኳት።
ቤተክርስቲያን ደርሰን ከመጣን ቡሀላ ወደቤት ተመለስን።
አባቴ ተኝቶ ነበር።
የማሂ አባት ሶፋ ላይ በጀርባቸው ደገፍ ብለው ቁጭ ብለዋል እናቴ ወደቤተክርስቲያን ሄዳለች አሉን።
እህቴ ቁርስ ለማዘጋጀት እየተሯሯጠች ነበር።
የማሂ አባት ምነው ልጄ ከስንት አመት ቡሀላ አይናቸውን ብታየው አስችሎህ ውጭ አደረክ እእእ
አንገቴን እንደደፋሁ ዝም አልኳቸው ና ቁጭ በል አሉኝና ጠጋ አሉልኝ።
እየውልህ ልጄ አባትህ ምንም ቢያደርግ እንዳትናደድበት ልክ ነው።
ለአባት ልጁ ሲደሰት አሪፍ ደረጃ ሲደርስ እንደማየት የሚያስደስተው ነገር የለም ይኼን ሁሉ ግቢ ቤት ትተህ አንዲት ሴትን ተከትለህ ስትኮበልል ይሁን እሺ ብሎ መቀበል ነበረበት እንዴ እእ አንተ ብትሆን ይሄን ነበር ምታደርገው??
እኔ አባት ነኝ ስሜቱን አቀዋለሁ ያማል ልጅን በትልቅ ቦታ ለማየት እየጠበከው ተስፋህን ሲያጨልመው ስሜቱ ከባድ ነው አሁን ሲነሳ እግሩ ላይ ውደቅና ይቅርታ ጠይቀው ልጄ እሱ ነው ለሁለታችሁም የሚበጀው::እሺ አልኳቸው አባቴ እንደተኛ ሳይነሳ እናቴ ከቤተክርስቲያን ተመልሳ መጣች ስታየኝ እንባ ቀደማት መጥታ አቀፈችኝና ሳም እያደረገችኝ እውነት እውነት አልመስልሽ አለኝኮ የኔ ልጅ ና ቁጭ በል ጎረመስክልኝ የኔ ልጅ።
የኔ ልጅ አልመስል አልከኝ በድጋሜ አቅፋ ሳም ታደርገኛለች።
የናት አንጀት ሆኖባት እንጂ እኔ አሁን ይቅርታ ሚያስደርግ ስራ ሰርቼ ነው ለራሴ ገረመኝ።
ትንሽ ቆይቶ አባቴ ተነሳ ወደ ሳሎን ሳይወጣ እህቴን ጠራትና የሆነ ነገር አላት።
እህቴ ወደኔ ጠጋ ብላ ሂድ ግባና አናግረው እሱ እዚህ እስኪመጣ አጠብቅ አቶ ሳሙኤል እርሶም ከወንድሜጋ አብረው ይግቡ አስታራቂ ይሀሸናሉ አለች የውሸት ፈገግ ለማለት እየሞከረች።
እሺ ልጄ ተነስ በቃ እንቋጨው ይሄን ነገር አሉኝ።
ወደመኝታ ክፍሉ ገባን አባቴ አልጋ ላይ ቁጭ ብሎ አሰያለቀሰ አንገቱን ደፍቶ እያለቀሰ ነበር እኛን ሲያየን ምንም እንዳልተፈጠረ ለመሆን ሞከረ ተርበተበተ እኔ እሮጬ ጉልበቱ ላይ ጥምጥም አልኩበት አባቴ ስላሳፈርኩህ ይቅር በለኝ ከሰው በታች ስላደረኩህ ይቅር በለኝ አስተምረኸኝ እንዳልተማረ ስለሆንኩ ይቅር በለኝ አባቴ ክብርህን እንድታጣ ስላደረኩህ ይቅር በለኝ አልኩት ሳግ እየተናነቀኝ አባቴ ዝም ብሎ ከኔ እኩል ማልቀሱን ተያያዘው ቀና ብዬ ሳየው አሳዘነኝ።
ከፊቱ ላይ እንባውን እየጠረኩለት ይቅርታ አድርግልኝ ልብህን ስለሰበርኩት እርግጠኛ ሁንብኝ እንጂ እክስሀለሁ አባቴ ክብርህን በእጥፉ ነው ምመልስልህ ብቻ አንተ ይቅርታ አድርግልኝና የህሊና እረፍት ላግኝ አልኩት ።
ይቀጥላል ..
✎ክፍል 15 ነገ ማታ 2:30 ይቀጥላል♥️ ቶሎ እንዲ🀄️ጥል LIKE♥️ እና Share አድርጉ።
ይ🀄️ላ🀄️ሉን
https://t.me/+4dGFaH_mUnExZjg8
https://t.me/+4dGFaH_mUnExZjg8
💝የዩቲዩ ገፃችን💝
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333