ፅጌሬዳ
ክፍል 38
ልጄ ቆየሁባችሁ እንዴ ቁርስ ሳትበሉ አለች።
አረ እማ አልቆየሽም ገናኮ ሰአት እኛ በጠዋት ተነስተን ነው አልኳት።
ሌሊት ተነስቼ ሰራርቼላችሁ እስክትነሱ የሄድኩት ኑ በቃ አባትህን ልቀስቅሰውና እንምጣ ብላ ወደ አባቴጋ ገባች።
እኔ ቀጥ ብዬ ቆምኩ ወደማሂጋ ተመልሼ ነይ ቁርስ እንብላ ለማለት ድፍረቱን አጣሁ።
ቀጥ ብዬ ሳሎን ገብቼ እራሴን ለቁርስ አዘጋጅቼ ቁጭ አልኩኝ ።
እናቴ መጣችና ነገርካት ለማሂ አባትህ እየታጠበ ነው ና አግዘኝ እስኪመጡ እናቀራርብ አለችኝ።
ተነስቼ እናቴን ማገዝ ጀመርኩ አባቴ መጥቶ ቁጭ አለ አቀራርበን ስንጨርስ እናቴ ቆም አለችና ማሂ ምን ሆና ነው እስካሁን ያልመጣችው አልነገርካትም እንዴ አለችኝ።
እኔጃ እማ ሂጂና እያት እስኪ አልኳት
ሄዳ ደግፋ ይዛት መጣች።
አይኗን ማየት ሞት መስሎ ተሰማኝ ያኔስ ሰክራ ነው አሁን ምን ይባላል አልኩኝ።
እሷ መጥታ ቁጭ ካለችበት ፊት ለፊት ላለመሆን ቦታ ቀየርኩ ።
አጎንብሼ ቀና ሳልል መብላት ጀመርኩ አባቴ የኔ ልጅ ዛሬ እንዴት ነው ለውጥ አለሽ አደል አላት።
አዎ ደና ነኝ ዛሬ ደሞ በጣም ደና ነኝ በህልሜ እራሱ ጥሩ ነገር ነው ያየሁት በጠዋቱም ደስ የሚል ነገር ተፈጥሯል አደል እንዴ ናታኔም አለችኝ።
የጎረስኩት ምግብ ትን አለኝ።
እናቴ ደንግጣ እኔን ልጄ እኔ አፈር ልብላልህ እንካ ውሀ ጠጣ አለችኝ።
አባቴ ከተቀመጠበት ከመቼው ተነስቶ አጠገቤ እንደቆመ ፈጣሪ ይወቀው ከናቴ ውሀውን ተቀብሎ አጠጣኝና ደና ነህ ደና ነህ አሉኝ ሁሉም።
ደና ነኝ ቁጭ በሉ አልኳቸውና ቁጭ አሉ።
ማሂን ቀና ብዬ ሳያት ጠቀሰችኝ።
ሁኔታዋ አስገረመኝ ይቺ ልጅ ይሄን ጋጠወጥነት ከየት ነው ያመጣችው ቆይ ያማታል እንዴ አልኩኝ ለራሴ።
ምግቡን በልተን እስክንጨርስ ቀና ሳልል አንገቴን እንደደፋሁ ቁርስ በቃኝ ብዬ ተነሳሁ ማሂም እኔም በቅቶኛል እባክህ እንድነሳ ታግዘኛለህ አለች።
እናቴ እንዴ ማሂ አንቺማ ብይ በግራሽ ስለምትበይኮ የልብሽ አይደርስም አለቻት።
አይ በቃኝ እናቴ አመሰግናለሁ አለቻትና እባክህ አግዘኝ እንድነሳ ትንሽ ቲቪ ባይ ጥሩ ነው አለች።
እሺ ብዬ እጇን ያዝኩት ስነካት ሰውነቴ ልክ አልነበረም በውስጤ ምን ሆኜ ነው ቆይ እንደጅል የሚያደርገኝ በቃ አንዴ ተፈጠረ አደል እንዴ እላለሁ።
ወስጄ ሶፋ ላይ አስቀመጥኳትና እኔ እናቴን በማነሳሳት ማገዝ ጀመርኩ።
ማሂ ፈገግ እያለች በገባሁ በወጣሁ ቁጥር በነገር እየነቆረች ታበሳጨኛለች።
እናቴ አጠገቧ ቡናዋን አቀራረበችና ልጄ በቃ ዛሬ ፏፏ ላድርግሻ ደስ እንዳለሽ እንዲውል በዛ ላይ አሁን አባትሽ ይመጣል አለቻት።
አጠገቧ ቡናዋን እያፈላች የልብ የልቧን ታወራታለች እናቴ ማሂን ልክ እንደልጇ የተቀበለቻት ነገር ግርም ይለኛል ገና ስለሷ ምንም ሳታውቅ እንዳየቻት ነበር የወደደቻት ማሂም ብትሆን ቀለል አድርጋ ነው ምትቀርባት ስታወራት እንደናት እንዳሳደገቻት ነገር ነው አወራሯ።
በመሀል እኔ ብድግ አልኩና መኝታ ቤት ገባሁና እየተናነቀ ያስቸገረኝን ሳቄን ለቀቁት ።
ሽንት ቤት ገብቼ መስታወት ፊት ጅንን ብዬ ቆምኩና እራሴን አስተዋልኩት ።
በመስታወት ውስጥ የማየው ሰው ሌላ እስኪመስለኝ ድረስ ነበር የሚሰማኝ ስሜት ይሄ ነው ማለት አይቻልም ብቻዬን ፈገግ እልና መልሼ ደሞ ይሄኮ ኖርማል ነው ኮራ በል እንጂ እላለሁ መልሼ ደሞ ቆይ ካሁን ቡሀላ ማሂ ፍቅረኛዬ ሆነች ማለት ነው ወይስ እንዴት ልንቀጥል ነው እራሴን ጠየኩት ይሄን ግንኙነት ለመጀመር እርግጠኛ ነህ አምነህበት ነው ፊደልን እስከዘላለሙ ከልብህ አውጥተህ በማህሌት ለመተካት ዝግጁ ነህ ወይስ ጊዜያዊ ስሜት ነው???
ጭንቅላቴ ውስጥ ምንም ትክክለኛ መልስ አጣሁ።
ቆሜ እንዳፈጠጥኩ እናቴ ጠራችኝና ምን እየሰራህ ነው ና እንጂ ቡናችንን እንጠጣ በዛው ጠፋህኮ አለችኝ።
እሺ እናቴ ብዬ ያፈላችውን ቡና ላባቴ አድርሼ ለራሴም ወስጄ ቁጭ አልኩኝ።
ማሂ አጠገቧ ስለሆነች እራሷ ሰጠቻት ቡናችንን ስንጨርስ ።
አቶ ሳሙኤል ሲመጡ መልሰን ስለምናፈላ ብላ መልሳ አቀራረበችው።
እናቴ ምሳ ማዘጋጀት ልጀምር ብላ ወደኪችን ገባች ።
ተከተልኳትና ገናኮ ነው አሁን ጀምረሽ ለምን ትሰሪያለሽ ከማሂጋ ቁጭ ብለሽ አታወሪም እንዴ አልኳት።
አይ ልጄ አቶ ሳሙኤል ስንት ሰአት እንደሚደርስ አላወኩም ቆንጆ ነገር አዘጋጅቼ ልጠብቀው አለችኝ።
እሺ ብዬ ተመልሼ ወደ ሳሎን ቁጭ አልኩኝ የማየው ሁላ ግራ ገባኝ ።
አባቴ ከማሂጋ ጨዋታ አንስቶ ማውራት ጀመረ በተቻለ መጠን treet ለማድረግ እየሞከረ ነበር።
ሲጨንቀኝ ከቤት ወጣሁና እህቴ ቤት ሄድኩኝ።
ያገር ልብስ እያጠበች ነበር።
ላግዝሽ እንዴ ብዬ ከሷጋ ማጠብ ጀመርኩ ቀና ብላ አይኔን አየችኝና ምን ሆነሀል አለችኝ??
ምን ሆንኩ አልኳት ።
በመጀመሪያ እንዴት በዚህ ሰአት ማሂን ትተህ እኔጋ መጣህ ሲቀጥል ከመቼ ጀምሮ ነው አንተ እኔን ልብስ ማጠብ ማገዝ የጀመርከው ብላ በጥያቄ አጣደፈችኝ።
ሳቄ እየተናነቀኝም እየተኮሳተርኩም ዝም ብዬ ካየኋት ቡሀላ
ማሂን ሳምኳት ማለቴ ሳመችኝ በቃ ተሳሳምን ዛሬ ጠዋት አልኳት።
ጮኸች ደንግጬ ወደኋላ ወደቀኝ ወደግራ ማየት ጀመርኩ ።
ወንዴሜ እኔ አላምንም ጓደኛሞች ሆናችሁ ማለት ነው እእ እንደምትወድህና እንደምትወዳት ተነጋገራችሁ ወይኔ ጉዴ እንዴት ደስ ይላል አለችኝ እየተፍለቀለቀች።
አረ እንደሱ አደለም እህቴ በቃ መሳሳም ብቻ ነው እንጂ እንደምንዋደድ አልተነጋገርንም ግን እኔ ጥሩ ስሜት ላይ አደለሁም ሲጨንቀኝ ነው ወዳንቺ የመጣሁት አልኳት።
ምኑ ነው የጨነቀህ ይሄኮ እጅግ ደስ የሚል ነገር ነው ወንድሜ የተሻለ ነገን አታስብም እንዴ ለምንድነው በትላንትህ ውስጥ ታስረህ ምትኖረው ደሞኮ ግልፅ ነው እንደምትዋደዱ
እውነት ለመናገር መጀመሪያ ሳያችሁኮ ፍቅረኛህ መስላኝ እንዴት ደስ እንዳለኝ ነበር ነገሩ እየቆየ ሲገለጥልኝ ግን ውሳጥችሁ መዋደድ አለ ግን ገልጣችሁ እንዳላወራችሁት ያስታውቅባችሁ ነበር።
ወንድሜ ፈጣሪኮ ምናልባት ሊክስህ ቁስልህን ሊጠግንልህ ማህሌትን ልኮልህ ይሆናል ፈጣሪ የሰህን ፍቅር ደሞ ባትገፋ ነው ሚሻልህ ቆይ ማሂ ምን ይወጣላታል ሁሉን የታደለችኮ ናት ቆይ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ ውስጥህ ያለው ትክክለኛ ስሜት ምንድነው ???
ይቀጥላል...
✎ክፍል 39 ነገ ማታ 2:30 ይቀጥላል♥️ ቶሎ እንዲ🀄️ጥል LIKE♥️ እና Share አድርጉ።
ይ🀄️ላ🀄️ሉን
https://t.me/+4dGFaH_mUnExZjg8
https://t.me/+4dGFaH_mUnExZjg8
💝የዩቲዩ ገፃችን💝
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333