ቤተል አደባባይ ላይ ተሽከርካሪዎች በግድ እንዲቆሙ እየተደረጉ ሰዎች እየታገቱ መሆኑ ታወቀ
ከቅርብ ወራት ወዲህ ቤተል አደባባይ ላይ በተለይ ዘመናዊ የሚባሉ መኪናዎችን የሚያሽከረክሩ ሰዎች በሁለት ሌሎች መኪናዎች መንገድ ተዘግቶባቸው በጠራራ ፀሀይ እየታገቱ እንደሆነ ምንጮቻችን ጠቁመዋል።
እነዚህ ግለሰቦች በዚህ መልኩ ታግተው ከተወሰዱ በኋላ እስከ 5 ሚልዮን ብር እየተጠየቀባቸው እንደሆነ ለመሠረት ሚድያ የሚደርሰው ጥቆማ ያሳያል።
አንድ የጉዳዩ ሰለባ የሆኑ ግለሰብ ድርጊቱን ለማንም እንዳይናገሩ ማስፈራርያ ስለሚደርሳቸው እንጂ በዚህ መልኩ በርካታ ዜጎች ታፍነው እየተወሰዱ ገንዘብ ከፍለው እየተለቀቁ እንደሆነ ተናግረዋል።
ሁለት ሚልየን ብር ከፍለው እንደወጡ የሚናገሩት ግለሰቡ ያገቷቸው ሰዎች የፀጥታ አካላት እንደሆኑ እንደደረሱበት ጨምረው ተናግረዋል።
"ህዝብን ይጠብቃሉ ተብለው የሚመደቡ አካላት ህዝብ ላይ እንዲህ በደል ሲያደርሱ ማየት እጅግ ያሳዝናል" ያሉን ግለሰቡ በዚህ ምክንያት ከሀገር ለመውጣት እንደተገደዱ ተናግረዋል።
በተያያዘ ዜና ከውጭ ሀገራት ወደ ሀገር ቤት ለዘመድ ጥየቃ፣ ለመዝናናት እና ለስራ የሚሄዱ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የእገታ ሰለባ እየሆኑ እንደሆነ ታውቋል።
ሰዎች ከውጭ እንደመጡ ሲታወቅ በክትትል ኢላማ ውስጥ እንዲገቡ እንደሚደረጉ የተጠቆመ ሲሆን በተለይ ሀብትና ንብረት እንዳላቸው የሚታወቁ የዲያስፖራ ኮሚኒቲ አባላት እገታ እንደተፈፀመባቸው የደረሰን መረጃ ይጠቁማል።
አንዳንዶች ካረፉበት ሆቴል እና አፓርትመንት ጭምር "ትፈለጋለህ" በሚል ምክንያት እንደሚወሰዱ እና በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ ግን የገንዘብ ድርድር እንደሚጀመር ታውቋል።
በዚህም እስከ 2 ሚልየን ብር ከፍለው የተለቀቁ የዲያስፖራ ኮሚኒቲ አባላት እንዳሉ እና ይህም በኤምባሲዎች እና በፖሊስ ተቋማት በኩል ጭምር እንደሚታወቅ ጨምሮ ተገልጿል።
በክፍላተ ሀገራት ይፈፀሙ የነበሩ የእገታ ወንጀሎች አሁን አሁን በጠራራ ፀሀይ በመሀል አዲስ አበባ እየተፈፀመ መሆኑ በብዙዎች የሚታወቅ ቢሆንም መረጃው እንዳይወጣ በሚፈፀም ማስፈራራት ወደ ሚድያ እንደማይወጣ ታውቋል።
(MeseretMedia)
@Addis_Reporter