እስከ 30,000 ብር የሚጠይቁት ህገወጥ የፍተሻ ጣቢያዎች ሊዘጉ ነዉ ተባለ
የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የትራንስፖርት እንቅስቃሴን ለማቀላጠፍና የኢኮኖሚ እድገትን ለማሳደግ በሚደረገው እንቅስቃሴ በመላ አገሪቱ በርካታ ሕገ-ወጥ የፍተሻ ጣቢያዎች እንደሚዘጉ አስታውቋል።
ሚኒስትሩ ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) አንዳንድ ሲሉ የጠሯቸው ቀበሌዎችና ከተሞች ያልተፈቀዱ የፍተሻ ጣቢያዎችን በመክፈት ከ10 እስከ 30,000 ብር የሚደርስ ክፍያ ሲጠይቁ እንደነበር ገልጸዋል።
እነዚህ የፍተሻ ጣቢያዎች ብዙውን ጊዜ በአካባቢዎች መካከል በሚደረግ ፉክክር መንፈስ የሚቆሙ፣ አላስፈላጊና ለኢኮኖሚው ጎጂ እንደሆኑ ተመላክቷል።
ሚኒስትሩ እነዚህ የመንገድ መዝጊያዎች አላስፈላጊ ወጪዎችንና መዘግየቶችን ከማስከተላቸውም በላይ የሀገሪቱን ኢኮኖሚያዊ እድገት እንደሚያደናቅፉ አስረድተዋል።
በሁሉም መንገድ ላይ እውቅና የሌላቸው የፍተሻ ጣቢያዎች መኖራቸውን አምነው የተቀበሉት ሚኒስቴሩ የጉምሩክ ፣ የፀጥታ ፍተሻ ፣ የድንበር (ለገቢ/ወጪ) እና ዋና ዋና የጭነት ተርሚናል የፍተሻ ጣቢያዎች ( ኬላ) ብቻ የተፈቀዱ መሆናቸውን ግልጽ አድርገዋል ።
@Addis_Reporter @Addis_Reporter