በሚሊዮኖች የምትጎበኘው ደብረ ምጥማቅ ጻድቃኔ ማርያም
በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በሞጃና ወደራ ወረዳ የምትገኘው የጻድቃኔ ማርያም መካነ ቅዱሳን ገዳም በሰላ ድንጋይ ከተማ አቅራቢያ ትገኛለች። ቦታው ከክልሉ ርእሰ ከተማ ባሕር ዳር 767 ኪሎ ሜትር፣ ከአዲስ አበባ 202 ኪሎ ሜትር እና ከዞኑ ርእሰ ከተማ ደብረ ብርሃን 72 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል።
ይህ ቅዱስ ሥፍራ በአፄ ዘርዓያዕቆብ እንደተቆረቆረ ሊቃውንቱ ይናገራሉ ። ጽላቷ ወደቦታው ስትመጣ ንጉሠ ነገሥቱ በእልልታና በደስታ ተቀብለው በዘመኑ ለነበሩት ካህናትና ዲያቆናት አስረከቧቸው፡፡
ቀጥሎም አጼ ዘርዓ ያዕቆብ ጅባት ከተባለው ከተማ ወደ እንጦጦ አምጥተው ለብዙ ጊዜ አስቀምጠዋታል፡፡ እንደገናም ከእንጦጦ አንስተው ወደ ደብረ ብርሃን አመጧት።
ከዚያም አሁን ወዳለችበት አካባቢ ወደ ሰላ ድንጋይ ሞሊያ በተባለው ከፍተኛ ቦታ ለብዙ ዓመታት መቆየቷን የገዳሟ መረጃ ይጠቁማል።
https://ameco.et/tourism/953/