ሮበርት ሌዋንዶውስኪ 7.2🇵🇱
ሮበርት ትላንት ያሳየው አቋም የላሊጋው ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ የሆነና ከኋላ በቅርብ ርቀት እንደ ኪልያን ምባፔ አይነት አደገኛ ተጫዋች እየተከተለው ያለ አጥቂ የሚያሳየውን አቋም አይደለም ያሳየው። አንዳንድ የጎል ማስቆጠር እድሎችን ሲያባክን ነበር።
ራፊንሃ 8.3🇧🇷
ራፊንሃ ሰሞኑን ጎል ከማስቆጠር ቢቦዝንም ነገር ግን ጥሩ ከመጫወት እና ቡድኑን ከመርዳት አልቦዘነም። ለሁለተኛው ጎል መቆጠር አመቻችቶ ያቀበለው ራፋ በመከላከሉም ረገድ አስደናቂ ነበር።
ዳኒ ኦልሞ 8.2🇪🇸
መቼስ የዳኒ ብቃት የሚያጠራጥር አይደለም። እሱ አቋሙ ላይ ከሆነ ዓለም ላይ ካሉ ምርጥ 10 መካከል ነው(ምናልባትም ምርጡ) ይህንንም በዩሮ 2024 ማሳየት ችሏል። ችግሩ ግን ጉዳት እና ከጉዳት ጋር ተያይዘው የሚመጡ እንደ አቋም መውረድ አይነት ችግሮች ናቸው። ትላንትናም ዳኒ ከጉዳት ነጻ ከሆነ ምን ያህል አደገኛ እንደሆነ ማሳየት ችሏል።
ፌራን ቶሬስ 7.5🇪🇸
ሜዳው ውስጥ ወደ 13 ደቂቃ ገደማ የተጫወተው ፌራን አስደናቂ ግብ ማስቆጠር ችሏል። ሮበርትን ተክቶ በቋሚነት የሚሰለፍበት ጊዜ አሁን ይሆን?
ፍሬንኪ 6.8 🇳🇱
ብዙም ደቂቃ አልተጫወተም ግን ከገባ በኋላ ቡድኑ ይበልጥ ተረጋግቶ እንዲጫወት ማድረግ ችሏል።
@BARCAFANSETHIOPIA

ክለባችን በ2025 ሌላ ጥንካሬውን እያሳየ ይገኛል እሱም የመከላከል አቅም ነው። ይህም ከሼዝኒ መምጣት ጋር እና ከተከላካዮቻችን ጥሩ አቋም ላይ ከመሆናቸው ጋር የሚገናኝ!
በአጠቃላይ ክለባችን ትላንት ጥሩ የሚባል አጨዋወትን አስመልክቶን (በተለይ ከኦልሞ መግባት በኋላ) ጨዋታውን አሸንፎ መውጣት ችሏል። ሬቲንጉን ያቀረብኩላቹ ADDY🥇 ነበርኩ በቀጣይ ማክሰኞ በአትሌቲው ጨዋታ እንገናኛለን። መልካም ምሽትን ተመኘሁ!
@BARCAFANSETHIOPIA
@BARCAFANSETHIOPIA