Репост из: እንማር
✅ ወርሃ የካቲት እለተ ቅዳሜ 2009 አመሻሽ ላይ ፍፁም ፀጥታ በሰፈነበት ምሽት የምናዘወትርበት መናፈሻ ዉስጥ ቁጭ ብለናል፡፡
እሷም እግሯን ዘርግታመሬት ላይ ኮቷን አንጥፋ እኔም ጭንቅላቴን እግሯ ላይ አስደግፌ የለበስኩትን ሹራብ አንጥፌ በጀርባዬ ተኝቻለሁ ፡፡ አይኖቼን ከእሷ ላይ መንቀል አልቻልኩም፡፡
አንደ ሁል ጊዜዬ ዛሬም አይኗን አሻቅቤ በ ስስት መመልከት ጀምራለሁ፡፡ እሷም እጆቿን ደረቴ ላይ ለጥፋ በምወድላት ፈገግታዋ ታጅባቁልቁል ትመለከተኛል፡፡
✅ ትንሽ ቆየች እና ጣቶቿን ወደ ከዋክብቱ እየጠቆመች “እነዚህ ሁሉ ከዋክብትና ጨረቃ ባይኖሩ ምን
የሚፈጠር ይመስልሀል?” አለችኝ፡፡ ምንም ሳላቅማማ “ድፍንያለ
ጨለማ ይሆናል” ብዬ መለስኩላት….....
,
,
✅ እሷም በ እረጅሙ ከተነፈሰች በሗላ “ውዴ ድፍን ያለ ጨለማ
ቢሆን እንኳ አንተን ከመመልከት አያግደኝም…በዚች ምድር ሳለሁ
ልቋቋመው የማልችለው አጋጣሚ ቢኖር አንተን ካጣሁ ነዉ "
በብላ ፀጉሬን
በጣቶቿ እያሻሸች አዘቅዝቃ አየችኝ ፡፡ እኔም በፍፁም መገረም
እና ደስታ ዉስጥ ሆኜ
“ቆይ… እኔን ብታጪ ምን ትሆኛለሽ?” አልኳት፡፡
✅ ወዲያው እግሮቿን ቀጥ አደረገች እና እጆቿን ደረቴ ላይ ጣል አድርጋ አይኖቿን ጨፍና “አንተን ካጣሁ በህይወት መኖር
አልችልም” አለችኝ ፡፡
ቀን ቀንን ወልዶ ዘመን ተለዉጦ ያ ፍፁም ነዉ ያልኩት ፍቅሯም
ተቀይሮ ይኸው አንተን ካጣሁ እሞታለሁ ያለችኝ ልጅ ሌላ ሰው አግባታ መኖር ከጀመረች አመታት አለፉ።
✅✅@Enmare1988