ወደ አሜሪካን ጎት ታለንት ( American Got Talent) ከሚመጡ ተወዳዳሪዎች መሃል Jane Marczewiski (በቅጽል ስሟ Nightbird) የምትባለውን ብዙዎች አይረሷትም፡፡ ተወዳዳሪዋ ወደ መድረክ በመጣች ጊዜ የዕለቱ ተረኛ ጠያቂ ሀዋርድ "እንዴት ነሽ!?" አላት:: በጣም ደስተኛ ነኝ:: እዚህ በመሆኔ በጣም ደስ ብሎኛል አለች"
ሀዋርድ ቀጠለና "ምንድንው የምታቀርቢልን!?" አላት:: እሷም "It is Ok” የሚል የራሴን ስራ ነው" አለች:: ሁላቸውም ባንድ አፍ እሺ ቀጥይ አሉ:: ሀዋርድ ቀጠለና "ግን ሁሉ ደህና ነው ስለምንድነው?" ሲላት ከካንሰር ጋር ስትታገል የኖረችውን የሕይወት ውጣውረድ ነገረቻቸው:: የሁሉም ፊት ጨለማ የእሷ ፊት ግን የደስታ ጨረር ከመርጨት አላቆመም:: ኮምጨጭ አለችና "አረ ሁሉ ደህና ነው:: እኔ ሰላም ነኝ" አለቻቸው::
ከዚያም ሳይመን "አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ? አሁን እንዴት ነሽ!?" አላት:: እሷም "የመጨረሻውን ምርመራ ሳደርግ በሳንባዬ፣ ጣፊያዬና ጉበቴ ላይ ካንሰር እንዳለ ተነግሮኛል ስትል ሳይመን በድንጋጤ ተመለከታት ፡፡ ቀጠለና ሀዋርድ "ስለዚህ ደህና አይደለሽም ማለት ነዋ" አላት:: "በርግጥ በሁሉም መልኩ አይደለም" ስትል ሀዋርድ ተገርሞ "ማንም ምን አይነት ሁኔታ ውስጥ እንዳለሽ እስከማያውቅ ድረስ ለሌሎች የደስታ ጨረር የሚረጭ አስገራሚ ፈገግታ አለሽ" አላት ተገርሞ!!
Nightbird የሕይወት ታሪኳን አሳማኝ በሆነ መልኩ በዜማ ካቀረበች በሗላ የዳኞች ውሳኔ የሚሰጥበት ሰአት ደረሰ:: ሁሉም ሳግ እየተናነቃቸው በስሜት የተሞሉ አዎንታዊ አስተያየቶችን ሰጡ:: ተራው ሲደርስ ተጠባቂው ሳይመን ሌሎች ዳኞች በሰጡት አስተያየት ሙሉ በሙሉ እንደሚስማማ ገልፆ ተጨማሪ ስሜቱን እንዴት መግለጥ እንዳለበት ግራ ገብቶት ሲያመነታ ሳለ መኻል ላይ አቋርጣ በከፍተኛ ፈገግታ በመሞላት፡
"ደስተኛ ልትሆን ለመወሰን ሕይወት ከዚህ በፊት ከነበረው ከባድነት ቀላል እስኪሆን መጠበቅ የለብህም" የሚል እጅግ አስገራሚ አስተያየት ሰነዘረች::
ያ ንግግር ብዙዎችን ያስገረመ ቢሆንም ሳይመንን ለደቂቃዎች አፍዝዞ እንባ ከሁለቱ ዓይኖቹ ፈሰሱ::
ከፊቱ ያለውን ተጎንጭቶ ሳግና እንባውን አወራረደ:: በመቀጠልም አስተያየቱን ሰነዘረ:- "በዚህ ዓመት ታላላቅ ችሎታ ያለቸውን ሰዎች አይቻለሁ:: ሆኖም ላንቺ 'yes’ አልሰጥም" ሲል ከዳኞች እስከ ታደሚ በቅሬታ አጉተመተሙ:: ሳይመን አልጨረሰም ነበር:: "የሚሰጥሽ ከ'yes’ የተሻለ ነገር ነው" አለና እጆቹ ወደ Golden Buzzer ሄደ:: አደራሹ በከፍተኛ ደስታ ሲያስተጋባ Nightbird የወርቁ ብናኝ ላይ በደስታ እንባ ተደፋች!!
በአንድ ጽሑፏ ሕመሟን በተመለከት "ፈጣሪ አብዛኛውን ጊዜ ወሳጅ ሳይሆን ሰጪ ነው:: ከመውሰድ ይልቅ ይጨምራል" ትላለች:: “ጨለማዬን አልወሰደውም ግን ብርሃን ጨመረልኝ:: ብቸኝነቴን አልፈወሰደውም ግን እርሱ ይበልጥ ቀረበኝ" ትላለች:: በሕመሟ ተስፋዋ ይጨምራል እንጂ ተስፋ ቢስ አይደለችም:: በመሆኑም "በህመሜ ተስፋ የማደርገው የፈጣሪን ቅርበት በዚያ ስላወቅሁ ነው" ትልም ነበር፡፡በመጨረሸም እንዲህ ነበር ያለቸው፦
"ለመኖር ሁለት ፐርሰንት ዕድል ብቻ እንዳለኝ በሀኪሞች ተነግሮኛል:: ነገር ግን ሁለት ፐርሰንት ማለት ዜሮ ማለት አይደለም:: ሁለት ፐርሰንት ማለት የሆነ ነገር እንደሆነ ሰዎች ሁሉ እንዲያውቁ እፈልጋለሁ!!"
https://t.me/shewitdorkahttps://t.me/shewitdorkahttps://t.me/shewitdorka