ይሄም አለ‼
በውስጥ የደረሰኝ ጥቆማ ነው‼
የፌደራል ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒሰቴር በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት በሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞኖች ጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶች ማገገሚያና የተሃድሶ ማዕከል ለመገንባት በ50 ሚሊዮን ብር በ2015 ዓ.ም ደሴ ከተማ አስዳደር ላይ የመሠረት ድንጋይ አስቀመጠ።
ለግንባታው ማስጀመሪያ የሚሆንም በመጀመሪያ ዙር በአማራ ክልላዊ መንግሥት የሴቶች ፣ሕፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አማካይነት ለዚህ ዓላማ ተብሎ በተከፈተ አካውንት 30 ሚሊዮን ብር ገቢ ተደረገ።
ሆኖም ምክንያቱ ባልታወቀ ምክንያት አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ገንዘቡን መልሱልኝ አለ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር።ክልሉም 30 ሚሊዮን ብሩን መለሰ።
በቅርቡ ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሱፐርቪዥን ቡድን ወደ ደሴ ከተማ አስተዳደር የመስክ ምልከታ ለማድረግ ይሄዳሉ።
በዚህ ወቅት ከተማ አስተዳደሩ ቃላችሁን አጠብቁም ለምን መጣችሁ የሚል ጥያቄ ያነሳል፣ ባህርዳርም ተመሳሳይ ጥያቄ ይቀርብለታል የሱፐርቪዥን ቡድኑ ቡድኑ ተመልሶ ግኝቱን ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያቀርባል።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሌላ ቡድን አዋቅሮ አባላቱ በአውሮፕላን ወደ ኮምቦልቻ ሁለት መኪና(ፕራዶና ላንድ ክሩዘር) እንዲከተላቸው አድርገው ይሄዳሉ።
በመጨረሻም የፋኖ ታጣቂ አስሮን መኪናዎችን ወስዶ እኛን ለቅቀን የሚል ሪፖርታቸውን ይዘው ከካዛንቺስ ከች አሉ።
የ50 ሚሊዮን ብር ፕሮጀክት ደሴ ከተማ የመሠረት ድንጋይ አስቀምጠው ኋላም ቃላቸው አጥፈው ገንዘቡን ወደሌላ እነሱ ወሚፈልጉት ቦታ የወሰዱት እነዚሁ ሰዎች ወደ ቢሮ ሲሄዱ እንኳንስ መኪና ሻንጣ የጠፋባቸው አይመስሉም ነበር ሲሉ ወዳጆቼ መረጃውን አጋርተውኛል።የተቋሙ ኃላፊዎችም ስለሁኔታው ማጣራት ወይም መጠየቅ አልቻሉም።ለመሆኑ መኪኖቹ የት ገቡ?!!
ጥቆማው "የመሠረት ድንጋይ ከደሴ ነቅለው የተለቀቀ በጀት አስመልሰው የራሳቸውን ፍላጎት ለማሟላት ይልንን የፈፀሙ ሰዎች እንኳንስ መኪና የተቋሙንም ህንፃ ሰነድ ቢያገኙት አይምሩም"በሚል ተቋጭቷል።
@ET_SEBER_ZENA