መፈንቅለ መንግሥት የማድረግ ዕቅድ‼️
በደብረፂዮን የሚመራው የህወሓት ጀነራሎች ለአምሰት ቀናት ያካሄዱትን ዝግ ስብሰባ ጨርሰው ዛሬ የአቋም መግለጫ አውጥተዋል‼️
የህወሓት ጀነራሎች ዛሬ ባወጡት መግለጫ ፤ "14ኛውን የህወሓት ጉባኤ ያደረገው የነ ደብረፅዮን ቡድን በወሰነው ውሳኔ መሠረት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደርን አስተካክሎ የማዋቀሩ ስራ ባስቸኳይ እንዲተገበር ወስነናል" ብለዋል።
መግለጫው ፥ በጌታቸው ረዳ የሚመራ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳድር አብዝቶ የሚኮንን እና መቀየር አለበት የሚል አቋም ያለው ነው።
በመግለጫው በቅርቡ በነ ደብረፂኦን የሚመራው የህወሓት ቡድን የራሱን አስተዳደር ማዋቀሩን በመደገፍ ከነደብረፂኦን ጋር እንደሚቆሙ አሳውቀዋል። ይህ ማለት የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳን ከፕሬዝዳንትነት ይነሳል ማለት ነው።
የትግራይ ሰራዊት በአንድ እዝ ስር ይግባ ይላል መግለጫው፣ ስለዚህ ጌታቸው ህግ የሚያስከብርበት ሰራዊት አይኖረውም ማለት ነው።
አዲስ ሰራዊት ማዋቀርን ሰራዊቱ በጥብቅ ከልክሎ ይህን በሚተላለፍ ማንኛውም አካል ላይ እርምጃ እወስዳለው ብሏል።
ከመግለጫው መረዳት እንደሚቻለው መፈንቅለ መንግሥት የማድረግ እቅድ እንዳለ በግልጽ ያሳያል።
የፌዴራል መንግሥቱ ምላሽ ይጠበቃል።
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት 👉
@Akiyas21bot @ET_SEBER_ZENA@ET_SEBER_ZENA