ፆታን መሰረት ያደረገ ጥቃትን አዘጋገብ በተመለከተ ስልጠና ተሰጠ
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከፍትህ ለሁሉም ኢትዮጵያ (Justice for All) ጋር በመተባበር ፆታን መሰረት ያደረገ ጥቃት (Sexual and Gender-Based Violence (SGBV)) አዘጋገብ ዙሪያ ለመገናኛ ብዙኃን ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ስልጠና ሰጥቷል።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛው ተስፋዬ፣ በስልጠናው መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ከፆታ ጋር የተያያዘ ጥቃት በቂ ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ አለመሆኑን በማንሳት በዚህ ዙሪያ ስልጠና መሰጠቱ ጠቃሚ መሆኑን ተናግረዋል።
መገናኛ ብዙኃን የስርዓተ ፆታ እኩልነትን በማስረጽና ፆታን መሰረት ያደረገ ጥቃት የመከላከል ሚና እንዲሁም ከስርዓተ ፆታ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች አዘጋገብ ምን ምን መርሆዎችን መከተል አለባቸው የሚሉ ነጥቦች በስልጠናው ተካተዋል።
በመገናኛ ብዙኃን እና በማስታወቂያ ይዘቶች ላይ የህግ ጥሰት፣ የሙያ ስነ-ምግባር ግድፈት፣ የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ ሲመለከቱ በ9192 ነፃ የስልክ መስመር ደውለው ማሳወቅዎን አይርሱ፡፡
#ብቁ_መገናኛ_ብዙኃን_ለማህበረሰባዊ_ንቃት
#የጥላቻ_ንግግርና_ሐሰተኛ_መረጃን_በጋራ_እንከላከል
የማህበራዊ ትስስር ገፆቻችንን ይጎብኙ፦
ድረ ገጽ
www.ema.gov.etፌስቡክ
https://www.facebook.com/ethiopian.media.authority/ኤክስ (X)
https://twitter.com/ethmediaauth?lang=enሊንክዲን
https://www.linkedin.com/in/ethiopian-media-authority-711169219?utm_source=share&utm_campaign=share_via&utm_content=profile&utm_medium=android_app