ከሚስቱ ይልቅ ለድመቱ ትኩረት ሰጥቷል የተባለው ባል ክስ ተመሰረተበት....
ባልየው ባህሪውን እንዲያስተካክል በሚስቱ ቢነገረውም አልተስተካከለም ተብሏል
ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ይዛ የሄደችው ሚስትም ፍትህ ይሰጠኝ ብላለች
ከሚስቱ ይልቅ ለድመቱ ትኩረት ሰጥቷል የተንባለው ባል ክስ ተመሰረተበት
ድመትን ጨምሮ ብዙ የቤት እንስሳት ከሰዎች ጋር በአንድ ቤት ውስጥ መኖር የተለመደ ሆኗል፡፡
አብራቸው እንድትኖር የተፈቀደላት አንድ ድመት ግን ለትዳር መፍረስ መነሻ ሆናለች ተብሏል፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፡፡ ሕንዳዊኑ ለዓመታት ጎጆ ቀልሰው በትዳር ተጣምረው እየኖሩ ነበር፡፡
አብራቸው እንድትኖር እና እናሳድጋት ያሏት ይህች ድመት ለፍቅራቸው መበላሸት መነሻ የሆነች ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ ባልየው ድመቷ እንድትለየው አለመፈለጉ ነው፡፡
ባሏ ከእሷ ይልቅ ለድመቷ ትኩረት ማድረጉ ያበሳጫት ሚስትም ከዚች ድመት ጋር ያለህን ግንኑነት ቀንስ ስትል ስሞታ ታቀርባለች፡፡
ከድመቷ ጋር ማንም አይለየኝም ያለው ባልም የሚስቱን አስተያየት ከመቀበል ይልቅ ተቃውሞ ያሰማል፡፡
በዚህ ምክንያት ወደ አለመግባባት የገቡት ባልና ሚስቶች አላስፈላጊ ቃላት እስከመለዋወጥ እንደደረሱ ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል፡፡
ጉዳዩ ያላማራት ሚስትም ፍትህ ይሰጠኝ ስትል ወደ ፍርድ አምርታለችም ተብሏል፡፡
ሚስትየዋ ለፍርድ ቤት በጻፈችው ማመልከቻ ላይ ባሌ ከእኔ ይልቅ ድመታችንን አብዝቶ ይንከባከባል ስትል ከሳለች፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ድመቷ ለእኔ ጥሩ እይታ የላትም ልቀርባት ስሞክርም በጥፍሮቿ ጉዳት ታደርስብኛለች፣ ባሌ ይህንን ችግር እንዲፈታ ብጠይቀውም ትኩረት አልሰጠም ማለቷ ተገልጿል፡፡
ክስ የቀረበለት ፍርድ ቤቱም በጉዳዩ ዙሪያ እልባት ለመስጠት ተቸግሯል የተባለ ሲሆን ምን አይነት ውሳኔ እንደሚያሳልፍ በጉጉት እየተጠበቀ ይገኛል፡፡[አል አይን]
@Ethionews433 @Ethionews433