ዲላ ዩኒቨርስቲ፣ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች በሒጃብ ምክንያት ከትምህርት ታግደዋል ተብሎ የተሠራጨው መረጃ "መሠረተ ቢስ" ነው ሲል በፌስቡክ ገጹ ባስተላለፈው መልዕክት አስተባብሏል።
ዩኒቨርስቲው "ብዝኀነትን" አክብሮ የሚሠራ የትምህርት ተቋም መኾኑን ገልጧል።
ኾኖም ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ካለፈው ሰኞ ጀምሮ ሒጃብ በመልበሳቸው ምክንያት ወደ ዩንቨርስቲው ቅጥር ግቢ እንዳይገቡ ታግደው በመስጂዶች ለማደር እንደተገደዱ መናገራቸውን ዶይቸቨለ ዘግቧል።
ሰኞ'ለት 44 ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ከስግደት ሲመለሱ፣ የግቢው ጸጥታ አካላት ሒጃባችኹን ካላወለቃችኹ አትገቡም እንዳሏቸው ተማሪዎቹ መግለጣቸውንም ዘገባው ጠቅሷል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ከማል ሐሩን፣ ምክር ቤቱ በጉዳዩ ላይ ከትምህርት ሚንስቴር ሃላፊዎች ጋር በመነጋገር ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ ለማስገኘት እንዲቻል አንድ የጋራ መድረክ ለማካሄድ ቀጠሮ እንደተያዘ ተናግረዋል ተብሏል። #DW
@Ethiopian_Digital_Library