የ USAID መቋረጥ ምን ያመጣብናል?
ሙሉ ለሙሉ አይተውንም እንጂ ከተረጂነት መንፈስ እንወጣ ነበር:: ሀገራችን ላይ ከ3 ሜትር ጀምሮ ውኃ አለ:: ግን በውኃ ጥም እንደኛ የሚሰቃይ የለም:: ማዕድናት እንደኛ ያለበት ሀገር መጥቀስ ይከብዳል:: አዲስ አበባ ውስጥ ሳይቀር ብዙ ማዕድናት አሉ:: የጫካውን ... (ሌላ ነገር ውስጥ አታስገቡን):: ሶማሌ ክልል ያለው የእርሻ መሬት አፍሪካን መቀለብ ይችላል:: ከጥልቅ ዳሎል እሳት እስከ ራስ ደጀን በረዶ ዐለም ያለው የአየር ንብረት ሁሉ አለን:: የአዲስ አበባ አየር በሹካ ተጠቅልሎ በማንካ የሚጎረስ የሚመስል እኮ ነው:: ሁሉንም ነገር ተሰጥቶን ሁሉንም ነገር ያጣን የነጣን ሆነን ነው::
ኑሮአችን አኗኗራችን ቀርቶ ሕግ ሁላ የሚወጣው በምቀኝነት ነው:: በስንት ልፋት, እንቅልፍ ማጣት እና ጥበብ የሆነ ሥራ ከሠራህ "በየት በኩል አምልጦን ከበረ?" ብለው ይከቡሃል:: ሳትወድ በግድ የማልመጡን መንገድ ትለማመዳለህ:: ብዙ ከሠራህ ብዙ የምትቀጣበት ሲስተም ውስጥ ነን:: አሜሪካ ዕርዳታ ብትቀንስ የለማኝ ነገር ወደ ቻይናና ራሽያ እንጠጋለን::
እንደው በምታምኑበት ይዣችሗለሁ:- ድንጋይ ለመፍለጥ, መሬት ለማረስ የትኛው የውጭ እርዳታ ያስፈልጋል? ብር ቸግሮን? በፍጹም:: ብር እኮ በነጻ የሚፈጠር ጸጋ ነው:: መንግሥት በማንኛውም ሰከንድ ያሻውን ያህል ብር መፍጠር ይችላል:: የውጭ ዕርዳታ የሚጠቅመን የውጭ ምንዛሪ ስለሆነ ከውጭ ለሚገባ ምርት እና ለዕዳ ክፍያ ነው::
ያው የፈረደባትን ቻይናን ምሳሌ ላድርግና 1959-1961 ጫማ ያስበላ ረሃብ ውስጥ የገባችው ቀደም ብላ የውጭ እርዳታ አስቁማ ወደ ኢንደስትሪ ገብታ ነው:: በኢንደስትሪው ምክንያት ብረት ተወደደና ገበሬው ማረሻውን ሁላ በኪሎ ሸጠ:: ግብርና ቀነሰ:: ረሃብ መጣ:: ሕዝቡ ለአመጽ ወጣ:: መንግሥት ወጥሮ ያዘ:: የግብርናና የኢንደስትሪ ባንክ አቋቁሞ, ታክስ ቆርጦ ጥሎ ዘመቻ ገባበት:: ታክስ መንግሥትን አስንፎ ሙሰኛን ይቀፈቅፋል::
የኢንደስትሪ ባንኳ ከዓለም 2ኛ ሲሆን የግብርና ባንኳ ከዓለም 4ኛ ነው::
ከስምንት ዓመታት በላይ በዕርዳታ ድርጅት ውስጥ ሠርቻለሁ:: የዕርዳታ ድርጅቶች የስለላ ሰንሰለቶች ናቸው:: እኛ በሁለቱም እግራችን ማጥ ውስጥ ስለገባን ቶሎ መውጣት ያዳግተን ይሆናል:: ግን መውጣት የግድ ይለናል::
Abdulkadir Hajj Nureddin
@Ethiopian_Digital_Library