መርፌ ቁልፍ
የምታዩት ስዕል እኔ ተወልጄ ባደግሁበት ሰቆጣ መርፌ ቁልፍ እንለዋለን። መርፌ ቁልፍ በገጠር ብዙ አገልግሎት አለው። ብዙ ገጠሬዎች ቢጠቀሙበትም ባይጠቀሙበትም እንደመጠባበቂያ ከኪሳቸው የማይለዩት መሣሪያ ነው። አንዳንድ ሰዎችም መያዣ ሊያበጁለት ይችላሉ። ዋነኛ ስራው ደረት እንዳይገለጥ እንደ አዝራር ለመጠቀም።
በድንገት ቢቀደድ እስኪሰፋ ድረስ ለማያያዝም ይጠቅማል። መርፌ ቁልፍ እሾህ ቢወጋ ወይም የእንጨት ስንጥር በአካል ላይ ቢገባ ለማውጣት ያገለግላል። እግር ወይም እጅ ቆስሎ ምግል ሲይዝም ጫፉ በእሳት ተጠብሶ ይቀዘቅዝና ለማምገል ይጠቅማል። ሞያሌ ወይም ሙጀሌ የሚወጣውም በመርፌ ቁልፍ ነው።
አንዳን ኮረዶች በተሠራ ጸጉራቸው ላይ እንደጌጥ ሲጠቀሙበት የነበሩ ሲሆን ለአገልግሎት ሲፈልጉት አውጥተው ይጠቀሙበትና ተመልሰው ጸጉራቸው ላይ ያደርጉት ነበር።
በነገራችን ላይ በ1950/60ዎቹ አምስት መርፌ ቁልፍ አምስት ሳንቲም፣ 12 ደግሞ በአስር ሳንቲም ይሸጥ ነበር። መርፌም በአምስት ሳንቲም 25፣ በአስር ሳንቲም ደግሞ 50 ይሸጥ ነበር።
መርፌ ቁልፍን የፈጠረው ዋልተር ሃንት የተባለ አሜሪካዊ ሲሆን የፈጠረውም እኤአ 1849 ነው። መርፌ ቁልፉን የፈጠረውም የነበረውን የ15 ዶላር ዕዳ በፍጥነት ለመክፈል ነበር። ሀንት መርፌ ቁልፉን ከሠራ በኋላ ዕዳውን በፍጥነት የከፈለ ቢሆንም የወደፊት ተፈላጊነቱን ሊያጤን አልቻለም። ስለሆነም ጠቃሚነቱን የተገነዘበ ባለሀብት የባለቤትነት መብቶቱን በ 400 ዶላር ገዝቶታል። ቅርጹም ከተፈጠረቀት ጊዜ እስካሁን ሳይለውጥ ቆይቷል።
ምስኪን ሀንት! የተረፈው ስሙ እንጂ ጥቅሙ ሳይሆን ቀረ።
@Ethiopian_Digital_Library