የባንክ ኢንዱስትሪውን ዘግይተው ከተቀላቀሉ መካከል አንዱ የሆነዉ አሃዱ ባንክ በተጠናቀቀው 2016 በጀት ዓመት ከታክስ በፊት 120 ሚሊዮን ብር ገደማ ትርፍ ማግኘቱን ገልጿል።
ባንኩ ስራ በጀመረበት የመጀመሪያ አመት ማለትም 2015 የስራ አፈፃፀሙ 267.7 ሚሊዮን ብር ኪሳራ ያስመዘገበ ቢሆንም በተያዘው በጀት ዓመት ግን ወደ ትርፍ መሸጋገር መቻሉን ነዉ በሪፖርቱ ያስታወቀው ።
በሁለት ዓመቱ የስራ ቆይታዉ ትርፍ ማስመዝገብ የቻለዉ አሃዱ ባንክ አጠቃላይ ሃብቱ 6.4 ቢሊዮን ብር መድረሱን እና 1.4 ቢሊዮን ብር ደግሞ የተፈረመ ካፒታል መሆኑን ጠቅሷል።
እኤአ በ 2021 የተቋቋመው ባንኩ አጠቃላይ ተቀማጭ ሂሳብ 4.66 ቢሊዮን ብር መድረሱን ገልጿል። በተጠቀሰው የስራ ዘመን 80 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚሆን የዉጭ ምንዛሪ መሰብሰብ መቻሉን ነዉ ያስታወቀው ።
Source: capitalethiopia
@Ethiopianbusinessdaily