ብሔራዊ የንግድ ፖርታል ማስፋፊያ ተጠናቀቀ፣ ሶስት ከተሞች ተካተቱ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የንግድ ፖርታል (NBP) ማስፋፊያ ፕሮጀክት መጠናቀቁን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ። በአዲሱ ማስፋፊያ የአዳማ፣ የባህር ዳር እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች የተካተቱ ሲሆን፣ ይህም የግንባታ ፈቃድ መስጠትን ጨምሮ የመንግስት አገልግሎቶችን በመስመር ላይ እንዲሰጡ አስችሏቸዋል።
ይህ ፖርታል በርካታ የመንግስት አገልግሎቶችን በመስመር ላይ ለማግኘት የሚያስችል መድረክ ሲሆን፣ የመንግስት የኤሌክትሮኒክስ አገልግሎቶች (ኢ-አገልግሎቶች) እና ይህን አገልግሎት የሚሰጡ የመንግስት ኤጀንሲዎች በአንድ ማዕከል እንዲሰባሰቡ ታስቦ የተሰራ ነው።
ፖርታሉ በመጀመሪያ የተገነባው እ.ኤ.አ በ2019 በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር (ሚንት) ሲሆን፣ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ብቻ አገልግሎት ይሰጥ እንደነበር ተገልጿል።
በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የታየውን መሻሻል ተከትሎ፣ ሚንት በአውሮፓ ህብረት ድጋፍ ፕሮጀክቱን ወደ ሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች ለማስፋት መቻሉን ካፒታል ሰምቷል።
የካቲት 27 ቀን 2017 ዓ.ም. ይፋ የተደረገዉ የዚህ ፖርታል ዋና ዓላማ የኢትዮጵያን የንግድ ምቹ ሁኔታ ማሻሻልና የመንግስት አገልግሎቶችን በዲጂታል ማቅረብ እንደሆነ ተጠቁሟል።
Source: capitalethiopia
@Ethiopianbusinessdaily