Phineas Gage: በአንድ ፋብሪካ ውስጥ ተቀጥሮ ይሰራ በነበረበት ወቅት አንድ ከባድ አደጋ ይገጥመዋል:: ከየት መጣ የማይባል ብረት ራስ ቅሉን በስቶት ይገባል:: ታዲያ ከዚህ አሰቃቂ አደጋ በተአምር ቢተርፍም፤ ከአደጋው ማግስት ሚስተር ጌጅ የበፊት ማንነቱ ይከዳዋል.. ያልነበረውን ባህርይ መላበስ ይጀምራል:: ያ የተረጋጋው፣ ስራ ወዳዱ፣ ቤተሰቡን አክባሪው ጌጅ ባህርይው ተቀየረ:: ይህም የሆነው ባህርይውን የሚቃኘው የአንጎሉ ክፍል(frontal cortex) በመጎዳቱ ነበር::
ደግሞ ሌላ ታሪክ
የቦክስ፣ የራግቢ እና መሰል ትግል የሚበዛባቸው ስፖርቶች ላይ የሚሳተፉ ሰዎች በጊዜ ሂደት ባህሪያቸው ሲቀየር: ብሎም የማገናዘብ ችሎታቸው/Cognitive ability ( ማለትም ትውስታ: ቅልጥፍና፣ የቋንቋ ችሎታ፣ ማህበራዊ አረዳድ..) ላይ እክል ሲገጥማቸው ይስተዋላል:: ይህም ከባድ ያልሆኑ ግን ድግግሞሽ ባላቸው ጭንቅላት ላይ በሚያርፉ ጡጫዎች ምክንያት የሚመጣ ነው:: ይህ ችግር Chronic Traumatic Encephalopathy (Punch drunk syndrome የሚሉትም አሉ) ተብሎ ይጠራል::
ጡጫው ሃይለኛ እና ጠንከር ያለ ሁኖ እና ወዲያውኑ አንጎል ላይ ከፍተኛ ጉዳት ካደረሰ Dementia (የመርሳት ችግርን) ሊያመጣ ይችላል:: የ Parkinson አይነት ህመምም የሚያጋጥማቸው አሉ:: ለዚህም Mohammed Ali ን መጥቀስ ይቻላል::
ከላይ ከጠቀስናቸው በተጨማሪ : አዙሪት(Post traumatic Seizure) ፣ የድብርት እና የባይፖላር አይነት ህመም፣ ድህረ አደጋ ጭንቀት(Post traumatic stress)፣ የሳይኮሲስ ችግሮች(ለሌላ የማይሰሙ/የማይታዩ ነገሮች ይሰማናል/ይታየናል ማለት፣ መጠራጠር..) : እና የመሳሰሉትን ጭንቅላት ላይ የሚደርስ አደጋን ተከትለው ሊከሰቱ የሚችሉ የአዕምሮ ህመሞች ናቸው::
ስለዚህም እነዚህን መሰል ምልክቶች ከታዩ የአዕምሮ ህክምና ባለሞያን ማማከር እና አስፈላጊውን ህክምና ማድረግ ይገባል::
አሻም አሻም!
ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው- የአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስት
ለበለጠ መረጃ የሚከተሉትን ገጾች ይወዳጁ
https://t.me/DrEstif
https://www.facebook.com/DrEstif
@HakimEthio