ለሽንት ደጋግሞ መነሳት (Nocturia)
ሌሊት ከእንቅልፍ ለሽንት መነሳት ብዙ ግዜ የሚታይ ችግርሲሆን በተለይ ደግሞ እድሜ ሲገፋ ይባባሳል፡፡ ከ50 አመት በኋላ ከ50% በላይ ያሉ ሰዎች ዘንድ ይታያል፡፡
በህክምናው ከሁለት ግዜ በላይ ከእንቅልፍዎ ሽንት ከቀሰቀሰዎ እንደ ችግር የሚታይ ነው፡፡ ይህ ችግር የእንቅልፍን ሁኔታ ከመረበሹም በላይ ለልዩ ልዩ የጤና ችግሮች ያጋልጣል፡፡
የሌሊት ሽንት መደጋገም መንስኤዎች
• ከመሸ በኋላ ፈሳሽ ማብዛት፡ በምሽት ውሃ በተለይምሻይ፣ ቡና ወይም አልኮል መጠጦች ለሽንት መብዛትአስተዋጽኦ ያደርጋሉ፡፡
• እድሜ መግፋት፡ ከፊኛ ሽንት የመያዝ አቅም መዳከምእንዲሁም የስኳር በሽታ፣ የኩላሊት እና የልብ ችግሮችከእድሜ መግፋት ጋር ተያይዘው መከሰት ለችግሩ ያጋልጣሉ፡፡ ለተለያዩ የጤና ችግሮች የሚሰጡ የሽንት መጠንን የሚጨምሩ መድሃኒቶችም አጋላጭ ናቸው፡፡
• የፕሮስቴት እጢ መፋፋት ወይንም የፕሮስቴት ካንሰር፡ በእድሜ የገፉ አባቶች ከፕሮስቴት መጠን መጨመር ጋር ተያይዞ ችግሩ ሊታይ ይችላል፡፡
• እርግዝና እና ማረጥ፡ በሴቶች ዘንድ ደግሞ እርግዝና ወይም በእድሜ መግፋት ለችግሩ ሊያጋልጡ ይችላሉ፡፡
• የሽንት መስመር ኢንፌክሽን፡ ሽንት ደጋግሞ መምጣት የሽንት መስመር ኢንፌክሽን አንዱ መገለጫ ምልክትነው፡፡
ከእንቅልፍ ደጋግሞ ለሽንት መነሳት የሚያስከትላቸው የጤና ችግሮች
• ያልተስተካከለ እንቅልፍ በቀን የመታከት ስሜት፣ መነጫነጭ፣ ለስራም ሆነ ለሌላ ጉዳይ ትኩረት ማጣትችግሮች ያስከትላል፡፡ ይህም ማህበራዊ ግንኙታችንና የስራ ብቃታችን ላይ እክል ይፈጥራል፡፡
• ድብታና ጭንቀት ለመሳሰሉ የአይምሮ ጤና ችግሮችሊያጋልጥ ይችላል
• በሌሊት ከእንቅልፍ ጋር እየታገሉ ወደ መጸዳጃ ቤትመመላለስ መውደቅ ወይም መጋጨት ሊያስከትልይችላል፡፡ ይህ አንዳንድ ግዜ የከፋ ጉዳት ያመጣል፡፡
• ሌሊት ደጋግሞ መነሳት ለረጅም ግዜ ከዘለቀ በሽታ የመቋቋም አቅምን ያዳክማል፡፡
• ለስትሮክና ለልብ ጤና ችግር የመጋለጥ እድልን ይጨምራል፡፡
እንዴት ልንከላከለው እንችላለን?
• ከእንቅልፍ ሰአት በፊት ፈሳሽ መቀነስ
• ከመተኛትዎ በፊት ወደ ሽንት ቤት መሄድ ልማድ ማድረግ
• ቡና፣ ሻይ እና አልኮል አለመውሰድ፤ ሻይ ወይም ቡና ካስፈለገዎ ወደ ጠዋት መውሰድ
• ተያያዥ የጤና ችግሮችን በአግባቡ መታከም፤ የልብ፣ የስኳር፣ የኩላሊት እና የፕሮስቴት ችግሮች ከተገኙ አስፈላጊውን ህክምና ማግኘት
• የሽንት መጠን የሚጨምሩ መድሃኒቶችን ጠዋት ወይንም ከመኝታ 6 ሰአት አስቀድሞ መውሰድ
• ከሰአት በኋላ ለተወሰኑ ደቂቃዎች መተኛት የሰውነት ፈሳሽ አንዲሰራጭ እና በቀን የመሽናት እድልን ይጨምራል፡፡
• ቀን ላይ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ እግርዎትን ከሰውነትዎ ከፍ አድርገው ይቀመጡ ወይንም ይተኙ፡፡ ይህ ቀን ላይፈሳሽ በታችኛው የሰውነት ክፍልዎት ላይ እንዳይከማችይረዳል፡፡
• ከሁለት ግዜ በላይ ከእንቅልፍዎ የሚነሱ ከሆነ፣ ሽንት ላይ ተጨማሪ ምልክቶች ካሉ፣ የሽንት መቅላት ካለ፣ እና የአኗኗር ዘይቤዎን ካቃወሰው ሃኪም ማማከር ያስፈልጋል፡፡
ኢትዮስካንዲክ ስፔሻሊቲ ክሊኒክ
አድራሻ - ኮተቤ ወረዳ 13 ወሰን ግሮሰሪ አካባቢ ዋናው መንገድ ላይ
ዌብሳይት 👉 https://ethioscandicclinics.com/
ቴሌግራም ግሩፕ 👉 https://t.me/+Ojdt9sH5WG41N2E0
ቲክቶክ 👉 https://www.tiktok.com/@ethioscanclinic
ፌስቡክ 👉 https://web.facebook.com/ethioscandicclinic
#addisababa #addisababaethiopia #health #HealthTips #ጤና #ሆስፒታል #የጤናምክር #ፕሮስቴት #ህከምና #prostateproblems #የሽንትችግር
@HakimEthio