አደጋ የደረሰበትን ህፃን መከታተል የሚያስፈልጉ ነገሮቸ
አያድርገውና ልጆች ላይ በተለያየ አጋጣሚ ማለትም ሲጫወቱም ሆነ በለተለት እንቅስቃሴያቸው ላይ የመውደቅ የግጭት ወይም የቃጠሎ አደጋ ከደረሰባቸው እና ተያይዞ እነዚህን ነገሮች በልጆቻቹ ላይ ካስተዋላቹ በጊዜ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ የልጅዎን ሀኪም ማማከር ያስፈልጎታል።
👉 ከአደጋው ጋር በተያያዘ ራስን መሳት ካለ ወይም አደጋው ሲከሰት ልጁ ካላለቀሰ
👉 ከአደጋው በኋላ በተደጋጋሚ የሚያስመልሰው ከሆነ
👉 ከአደጋው በኋላ የራስ መሳት እና ተያይዞ የአጠቃላይ ሰውነት መንዘፍዘፍ ካለ
👉 ከአደጋው በኋላ ግራ የመጋባት ስሜት ፣ ለመናገር መቸገር እና ያለወትሮው እንቅልፍ መተኛት የሚያበዛ ከሆነ
👉 የተጎዳው ክፍል የሚደማ ከሆነ እና በንፁ ጨርቅ ለ10 ደቂቃ ተይዞም መድማቱን ማቆም ካልተቻለ
👉 የተጎዳው እጁ ወይም እግሩ ማበጥ እና ከጤናማ ቅርፁ ውጪ መጣመም ካለው እንዲሁም ለማንቀሳቀስ ካልቻለ
👉 የተጎዳው የሰውነት ክፍሉ ቁስል ከቆዳው ያለፈ ጥልቀት ካለው
👉 የትንፋሽ መቆራረጥ ወይም የትንፋሽ ማጠር ካለው
👉 የአንገት ህመም ካለ እና አንገት ለማንቀሳቀስ ከተቸገረ
👉 ሀይለኛ የሆድ ህመም ካለው
👉 የቃጠሎ አደጋ ከሆነ ደግሞ
✔️ እድሜው ከ1 አመት በታች ከሆነ እና ማንኛውም ቃጠሎ ከተከሰተ
✔️ የተቃጠለው አካባቢ ውሀ መቋጠር ካለው
✔️ የኬሚካል ወይም የኤሌትሪክ ቃጠሎ ከሆነ
✔️ የፊት፣ የእጅ ፣የእግር ፣የብልት እና የመገጣጠሚያ አካባቢ ቃጠሎ
✔️ ቃጠሎው ሲለካ ከልጁ የእጅ መዳፍ መጠን በላይ የሆነ
✔️ በእሳት ቃጠሎ ጭስ የመታፈን ከነበረው እና
✔️ የአሳት ቃጠሎ ቁስሉ በ2 ሳምንት ውስጥ ካልዳነ
በጊዜ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ ልጅዎን ማስመርመር እና ተገቢውን ህክምና እንዲያገኝ ማድረግ ያስፈልጋል።
ማጣቀሻ - Pediatrics ATLS guideline
ዶ/ር ዮናታን ከተማ: በቅዱስ ጳውሎስ ስፒሻይዝድ ሆስፒታል የህፃናት ቀዶ ህክምና ሬዚደንት ሐኪም
ለበለጠ መረጃ YouTube - https://youtube.com/@kedmialetenawo?si=dkMsvvTm5D7S4kmb መጎብኘት ይችላሉ።
ሰላምና ጤና በያላችሁበት ይሁን።
@HakimEthio