Репост из: የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ
ዕውቀት እና የዕውቀት ባለቤቶች ደረጃ
ክፍል አንድ
ምስጋና ለአለማት ጌታ ለአላህ ይገባው፤ ፍጻሜው ለጥንቅቆቹ ነው ፤ ሶላትና ሰላምታ ከፍጡራን ሁሉ ምርጥ በሆነው በወህዩ ታማኝ በሆነው አገልጋዩና መልክተኛው በሆኑት ነብያችን መሪያችን ሙሐመድ ብን ዓብዲላህ ﷺ ላይ እንዲሁም በቤተሰቦቻቸው በባልደረቦቻቸው እና እስከፍርዱ ቀን በእርሳቸው መንገድ ላይ በተጓዙት ሁሉ ይስፈን፡፡
ከዚህ በኋላ፡
የእውቀት ትሩፋት ከሁሉም ዘንድ የታወቀ ነው፤ ሰዎች ከሚፈለጉት እና ከሚንቀሳቀሱበት ነገር ሁሉ በላጩ የሸሪዓዊ እውቀት ነው፡፡
እውቀት ለበርካታ ነገሮች ስያሜ ሆኖ ሲያገልግል ይስተዋላል፤ ነገር ግን ከኢስላም ኡለሞች ዘንድ ፡ “ኢልም በመባል የታወቀው ሸሪኣዊ የሆነውን እውቀት ነው፡፡” ፤ እርሱም የአላህ ኪታብና የረሱል ﷺ ሱና ነው፡፡
ሸሪዓዊ እውቀት ማለት የሚከተሉትን ነገሮች ያካትታል፡ ስለአላህ ፣ ስለስሞቹ ፣ ስለመገለጫዎቹ ማወቅ ፤ ባሮች ያለባቸውን ሀቅ ማወቅ ፤ ለእነርሱ የደነገገውን ህግና ስርዓት ሁሉ ማወቅ …
ወደርሱ የሚያቃርቡ የአምልኮ ዓይነቶችን እስከ ዝርዝራቸው ማወቅ ፤ ሰዎች የወዲያኛው አለም ግባቸውና ፍጻሜው ምንድን ነው? የሚለውን ሁሉ ጠንቅቆ ማወቅ፡፡
ከእውቀቶች ሁሉ በላጩ ፣ ልንጓጓለት የሚገባው የሸሪዓ እውቀት ነው፤ ምክንያቱም በእርሱ ነው አላህ የሚታወቀው ፣ በእርሱ ነው የሚመለከው፡፡
አላህ የፈቀደው ፣ የከለከለው ፣ የሚወደው የሚጠላው ሁሉ የሚታወቀው በሸሪዓ እውቀት ነው፡፡
በዚህ አለም ሂዎት ጉዟችን ፣ ፍጻሜያችን የሚታወቀው በዚህ እውቀት ነው፤
የሰው ልጅ በዚህ የሸሪዓ እውቀት ላይ ተመስርቶ አሏህን በብቸኛነት ከተገዛ መዳረሻው የዘላለም ደስታ የሚጎናጸፍበት ጀነት ይሆናል። ይህ ሳይሆን ከቀረ - አሏህ ይጠብቀንና - ዘላለም ውርደትና ቅጣትን የሚቀምስባት ጀሐነም ይገባል።
በዚህ ላይ የእውቀት ባለቤቶች ማህበረሰቡን አንቅተዋል ፤ እውቀት በዚህ ትርጉም የታጠረ መሆኑን ግልጽ አድርገዋል፤
የጦሃውያ ሸርህ ባለቤት የሆኑት ቃዲ ብን አቢል ኢዝ የመጀመሪያ ማብራሪያው ላይ በዚህ ላይ ሰዎችን ካነቁ አሊሞች መካከል ናቸው፡፡ ከእርሳቸው ውጭም ኢብን አልቀይም ፣ ሸይኹል ኢስላም ብን ተይሚያህ እና ሌሎችም ዓሊሞች እንዲሁ በዚህ ጉዳይ ሰዎችን አንቅተዋል፡፡
ሸሪዓዊ እውቀት ግልጽ ነው : ከበላጮቹ፣ ከታላቆቹ እና በጣም ልቅና ካላቸው እውቀቶች መካከል ከአላህ ከስሞቹ ፣ ከመገለጫዎቹ ጋር ተያያዥ የሆነው እውቀት ነው ፤ እርሱም የአቂዳ እውቀት ነው፡፡ አላህ - ﷻ - በአካሉ ፣ በስሞቹ፣ በመገለጫዎቹ ፣በተግባራቶቹ ከፍተኛ የሆነ መገለጫ አለው፡፡
ከዚህ በመቀጠል ከሰዎች ሀቅ እና ከሸሪዓ ህግጋቶች ጋር ተያያዥነት ያለው እውቀት ነው፤ ከዚያም በዚህ ነገር ላይ አጋዥ የሆኑ እውቀቶች በተለይም የቁርዓን ፣የሐዲስ፣ የአረበኛ ችሎታችንን ለማጎልበት የሚያግዙ ኡሉሙል ቁርአን ፣ ሙስጦለሁል ሐዲስ ፣ ነህዉ ፣ ሶርፍ .. እና የመሳሰሉ እውቀቶቾን መማር አስፈላጊ ነው።
ከዚህም ውጭ ያሉ የሸሪዓ እውቀታችንን የበለጠበ የሚያግዙ እና እውቀትን የበለጠ ሙሉ የሚያደርጉ የትምህርት አይነቶችን መማር አስፈላጊ ነው፡፡
ከዚህ ጋር ተያያዥነት ያለው የነብዩን ﷺ ታሪክ ማወቅ ፣ ኢስላማዊ ታሪኮች ፣ የሀዲስ ሰዎችን የሂዎት ታሪክ እና የኢስላም መሪዎችን ታሪክ የምናውቅበት እውቀት ነው፡፡ ከእነዚህ እውቀቶች ጋር ተያያዥነት ያለው ሁሉ ተፈላጊ አውቀት ነው፡፡
https://t.me/alateriqilhaq
كن على بصيرة