ፆመን ውለን ስናበቃ ያለ አጅር ባዶዋችን እንዳንገባ እንጠንቀቅ!!
———
በዚህን ጊዜ አላህ ያዘነለት ሰው ሲቀር የብዙ ሰዎችን ተግባርና ምላስ ስናይ ፆም ማለት:- በቃ ከምግብና ከሚጠጡ ነገሮች መታቀብ ብቻ ይመስላቸዋል። ይህ ከባድ የሆነ አደጋ ነው!። አቢ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል አለ:-
عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ، عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ : " مَنْ لَمْ يَدَعْ قَوْلَ الزُّورِ وَالْعَمَلَ بِهِ وَالْجَهْلَ، فَلَيْسَ لِلَّهِ حَاجَةٌ أَنْ يَدَعَ طَعَامَهُ وَشَرَابَهُ ".
صحيح البخاري وغيره
“(ፆመኛ ሆኖ) በውሸት መናገርን ያልተወ፣ በውዳቂ ነገር መስራትን ያልተወ ሰው፣ በአላዋቂነትና በሞኛሞኝነት በሰዎችም ሆነ በራሱ ላይ ድንበር ማለፍን (ቂላቂል መሆንን) ካልተወ ምግብና የሚጠጣ ነገር በመተው ለአላህ ግድ የለውም።” [ቡኻሪና ሌሎችም ዘግበውታል።]
ኢብኑ'ል ቀይም (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:-
«ፆመኛ ማለት አካሎቹ ከሀጢአት የጸዱ፤ ምላሱን ከአሉባልታ፣ ከውሸት እና ከአጸያፊ ንግግር የጠበቀ፤ ሆዱን ከምግብ ፣ ከመጠጥ እና ብልቱን (በቀን ክፍለ ጊዜ) ከግብረ ስጋ ግንኙነት የጠበቀ ነው።
ፆመኛ ከተናገረ፣ ፆሙን በማይጎዳ መልኩ ይናገራል፣ ስራ ከሰራ ፆሙን በማያበላሽበት መልኩ ይሰራል። ፆመኛ ጠቃሚና ቁምነገር ያለው ንግግር እና ስራ ሲሰራ ምሳሌው ልክ ከሽቶ ተሸካሚ ሰው ጋር ተቀምጦ መልካም ሽታ እንደሚያገኝ ሰው ነው!!። ከፆመኛ ጋር የተቀመጠም ሰው መልካም ነገርን እንጂ ሌላ አያገኝም። ከተለያዩ መጥፎ ነገሮች እንደ ቅጥፈት፣ ውሸት፣ ጥመት እና በደል ከመሰሉ ነገሮች ሁሉ ሰላም ይሆናል። ይህ ነው ትክክለኛና ህጋዊ ፆም ማለት። ከምግብና መጠጥ ብቻ መታቀብ ፆም አይባልም።
ፆም ማለት አካላትን ከሀጢአት፣ ሆድን ከምግብና ከሚጠጣ ነገር በመታቀብ መፆም ነው። ምግብና የሚጠጣ ነገር ፆምን እንደሚያበላሽ ሁሉ ሀጢአትም የፆምን ምንዳ ያበላሻል፣ ውጤቱንም ያበላሻል። በዚህም ምክንያት ልክ ፆም እንዳልፆመ ተደርጎ ይታሰባል።» [አልዋቢሉ አስ-ሶይብ 31-32]
✍🏻 ኢብን ሽፋ: (t.me/ibnshifa)
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa