ግንኙነት ያልተፈፀመበት ኒካሕ
~
አንድ ሰው አንዲትን ሴት ኒካሕ አድርጎ ካገባ በኋላ ነገር ግን በመሃላቸው ግንኙነት ሳይፈፀም ከፈታት ፤ ለምሳሌ የተለያየ ሃገር እየኖሩ ኒካሕ ከታሰረ በኋላ ሳይገናኙ ፍቺ ቢፈፅም ዒዳ የለባትም። ምክንያቱም አላህ እንዲህ ብሏልና፦
يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آَمَنُوا إِذَا نَكَحْتُمُ الْمُؤْمِنَاتِ ثُمَّ طَلَّقْتُمُوهُنَّ مِنْ قَبْلِ أَنْ تَمَسُّوهُنَّ فَمَا لَكُمْ عَلَيْهِنَّ مِنْ عِدَّةٍ تَعْتَدُّونَهَا فَمَتِّعُوهُنَّ وَسَرِّحُوهُنَّ سَرَاحًا جَمِيلًا
{እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ምእምናትን ባገባችሁና ከዚያም ሳትነኳቸው በፊት በፈታችኋቸው ጊዜ ለእናንተ በእነርሱ ላይ የምትቆጥሯት ዒዳ ምንም የላችሁም፡፡ አጣቅሟቸውም፤ (ጉርሻ ስጧቸው)፡፡ መልካም ማሰናበትንም አሰናብቷቸው፡፡} [አል አሕዛብ፡ 49]
* ይሄ ጉዳይ የዑለማእ ኢጅማዕ ያለበት ነው።
ማሳሰቢያ፦
* ዳግም ማግባት ከፈለገ መስፈርቱን ያሟላ አዲስ ኒካሕ ማሰር እንጂ እንዲሁ መልሻለሁ ብሎ መመለስ አይችልም።
* ለመመለስ ሌላ አግብታ መፈታቷ ሸርጥ አይደለም። ሌላ አግብታ የተፈታች ባይሆንም ማግባት ይችላል። ነገር ግን የባለፈው ፍቺ አንድ ተብሎ ይቆጠራል። ስለዚህ ሁለት ኒካሕ ነው የሚቀረው ማለት ነው።
.
በፍቺ ሳይሆን በሞት ከተለየ ግን የዒዳው ብይን ይለያል። ማለትም ኒካሕ ታስሮ ግንኙነት ሳይፈፀም በፊት ባል ከሞተ አራት ወር ከ 10 ቀን ዒዳ ትቆጥራለች። ከንብረቱም ትወርሳለች። ሙሉ መህሯንም ትወስዳለች። የመህሯ መጠን ቀድሞ ያልተወሰነ ከሆነ የአምሳያዎቿ መህር ታሰቦ ይሰጣታል።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor