Репост из: EFDA የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን
መንግስት ጤናማ ባልሆኑ ምግቦች ምክንያት የሚከሰቱ በሽታዎችን ለመቀነስ ብሎም ለማጥፋት የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ ጥረቶችን በማካሄድ ላይ መሆኑ ተገለፀ፡፡
ታህሣሥ 3/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ በኢንዱስትሪ የሚመረቱ ትራንስ ፋቲ አሲድ ያለባቸውን ምግቦች ለመመርመር የሚያስችል አገር አቀፍ የላቦራቶሪ አቅም ለመፈተሽ የተካሄደውን ጥናት ይፋ ለማድረግ የተዘጋጀውን አውደጥናት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሄራን ገርባ ሲከፍቱ እንደተናገሩት በአገር ውስጥም ይሁን ከውጭ ወደ አገር የሚገቡ በኢንዱስትሪ የተመረቱ ምግቦች የትራንስ ፋቲ አሲ መጠናቸውን ለመለካት የሚያስችል አገር አቀፍ የላቦራቶሪ አቅም ፍተሻ ጥናት ማካሄድ በቀጣይ በዘርፉ ላይ ለሚደረገው ቁጥጥር አቅም የሚፈጥር ነው፡፡
በኢንዱስትሪ የሚመረቱ ምግቦች ውስጥ ያለውን የትራንስ ፋቲ አሲድ መጠን የመቀንስ ብሎም የማጥፋት ስራ የምግብ ደህንነት ለማረጋገጥ ከሚሠሩ ስራዎች መካከል አንዱ መሆኑን የጠቀሱት ዋና ዳይሬክተሯ መንግስት የህብረተሰብ ጤና ለመጠበቅ የምግብና የምግብ ስር-ዓተ ፖሊሲ ከማውጣት ጀምሮ የአምስት ዓመት የምግብ ደህንነት ፍኖተ ካርታ አውጥቶ ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡
በጥናቱ የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን፣የሕብረተሰብ ጤና አጠባበቅ ኢንስቲትዩትና የኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት፣ አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ስነ-ምግብ ማዕከል እንዲሁም የኬሚስትሪ ላቦራቶሪዎች፣ ፣ጅማ ዩንቨርስቲ፣ አሮማያ ዩኒቨርስቲ እንዲሁም ብሌስ አግሮ ላቦታሮሪ ና ጄጄ ላቦ ላቦራቶሪዎች በጥናቱ ተዳሰዋል፡፡
በቀጣይ ሁሉም ላቦራቶሪዎች ወደ ተፈለገው የላቦራቶሪ ምርመራ ስራ መግባት እንዲችሉ ያሉባቸውን ክፍተት በመሸፈንና የጋራ የትብብርና የቅንጅት ስራ በማጠናከር አጋር ድርጅቶች እገዛ መጨመር ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ተግባር እንደሆነ ተመልክቷል፡፡