Фильтр публикаций


በኢትዮጵያ #ተደራራቢ የግብር ጫና እየተፈጠረ ነው። መንግስት ከግብር ገቢ ውጪ የገቢ እቅዱን ማሳካት የሚችልበት አማራጭ የለውም?

የሚከተለውን ትንታኔ እንመልከት.....https://youtu.be/Cyyc2ZYb3iA


እቁብ ለመጀመሪያ ወሳጅ ወለድ የማይከፈልበት #ብድር ሲሆን መጨረሻ ለሚወስደው ወለድ ያልታሰበበት #ቁጠባ ይሆናል!

በሀገራችን እቁብ ከትንሽ እስከ ትልቅ የተለመደ ባህላዊ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ መሰረት ያለው አደረጃጀት ነው!

እቁብ ሰዎች የሚገቡበት ምክንያት የተለያየ ቢሆንም ገንዘብን እቤት ከማስቀመጥ፤ ገንዘብን በባንክ ከማስቀመጥ፤ ገንዘብ ከባንክ ከመበደር፤ ገንዘብ ከሰው ወይም በአራጣ ከመበደር አንፃር ስንለካው እድልም ስጋትም አለበት!

እቁብ ሁሉንም እኩል ተጠቃሚ አያደርግም!

እቁብ ወለድ የለውም! በመጀመሪያ እና በመጨረሻ ባለ እጣ መካከል ያለው ልዩነት በኢኮኖሚክስ #Depreciation ይባላል!https://youtu.be/bWgZRsKZ8oE


የብድር አዋጭነት ከሃገር ውስጥ እና ከውጪ ከሚገቡ ባንኮች!

የውጪ ሀገር ባንኮች (ዓለምአቀፍ ባንኮች) ወደ ኢትዮጵያ የፋይናንስ ገበያ ሊገቡ መሆኑ ይታወቃል!

ለብድር ፈላጊዎች ምርጫቸው ሁለት ሆኗል! ስለዚህ ብድር ከሃገር ውስጥ ባንኮች እና ከውጪ ከሚገቡ ባንኮች መካከል የሚኖሩ እድሎች እና ልዩነቶች!

ተበዳሪዎች ሁለቴ ማሰብ ያለባቸው መሰረታዊ ነጥቦች ምንድን ሊሆኑ እንደሚገቡ እንመልከት!https://youtu.be/ZJ1vIK6fDG0


#ዓለም_ባንክ፣ የኢትዮጵያን የፋይናንስ ዘርፍ ለማጠናከር የሚውል የ700 ሚሊዮን ዶላር ብድር አጽድቋል።

ከብድሩ 90 በመቶው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ሒሳብ ለማስተካከልና ባንኩን መልሶ ለማዋቀር እንደሚውል ዓለም ባንክ ገልጿል።

ከፊሉ ብድር ለብሄራዊ ባንክና የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ማጠናከሪያና መዋቅራዊ ማሻሻያ እንደሚሰጥ ባንኩ ጠቅሷል።

ብድሩ በአራት ዓመታት ጊዜ ውስጥ የባንኮቹ አፈጻጸም፣ የደንቦችና የመዋቅሮች ማሻሻያ ሂደት እየታየ የሚለቀቅ ነው።

የብድሩ ዓላማ፣ የአገሪቱን የፋይናንስ ዘርፍ ጠንካራና አስተማማኝ ለማድረግና ተደራሽነቱን ለማስፋት ያለመ እንደሆነም ባንኩ ባሰራጨው አጭር መግለጫ አንስቷል።

በመግለጫው...

"We are proud to support Ethiopia in its journey to transform and strengthen its financial sector. This project reflects our commitment to promoting economic stability and inclusive growth in the country. By boosting the capacity of key financial institutions, we aim to build a more resilient and accessible financial system that truly meets the needs of all Ethiopians,” said Maryam Salim, World Bank Country Director for Eritrea, Ethiopia, South Sudan, and Sudan.


ንግድ ባንኮች ከተለመደው ባለፈ መልኩ የጥሬ ገንዘብ እጥረት ገጥሟቸዋል! በባንኮች ውስጥ የጥሬ ገንዘብ እጥረት የሚፈጠርበት ምክንያቶች!

የንግድ ባንኮች በጥሬ ገንዘብ እጥረት ምክንያት እየተፈጠሩባቸው ያሉት ተፅዕኖዎች!

የንግድ ባንኮች የጥሬ ገንዘብ እጥረትን ለመቋቋም የሚወስዷቸው የመፍትሔ እርምጃዎች!

ከላይ የተዘረዘሩ ወሳኝ የኢኮኖሚ ጉዳዮችን በትክክለኛ ምሳሌ እንመለከታለን!https://youtu.be/yAyTk2yLGjk


የኢትዮጲያ ኢኮኖሚ እያደረገ ባለው የፖሊሲ ለውጥ ምክንያት የተለያዩ ሴክተር ሰራተኞች ስራቸውን ሊያጡ ይችላሉ!

ኢኮኖሚው የሃገር ውስጥ የፋይናንስ ድርጅቶች ለውጪ ባለሃብቶች ክፍት እንዲሆኑ መፍቀዱ የባንክ ሴክተሩ ሰራተኞች እንዲቀነሱ የሚያደርግባቸው ምክንያቶች፤ ሰራተኞች ቀድመው ማሰብ ያለባቸው ነጥቦች፤ የኢትዮጲያ ኢኮኖሚ በፖሊሲ ለውጥ ምክንያት የሚፈጠር የሰራተኞች መቀነስን እንዴት ሊመለከተው እንደሚችል እንመልከት....https://youtu.be/mSuwzh1oPe0


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲሱ አዋጅ 5 ዋና ዋና ለውጦች! የውጪ ባንኮች የሚገቡባቸው 4 ዘዴዎች! ለዲያስፖራው የተመለሰው የኢንቨስትመንት እድል....

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ አዲስ አዋጅ ፀድቆለታል! በዚህ አዋጅ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚን መወሰን የሚችሉ ዋና ዋና ማሻሻያዎች ተካተውበታል!

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ተፅዕኖ የሚፈጥሩትን የአዋጁን 5 ዋና ዋና ድንጋጌዎች በዝርዝር እንመልከት...https://youtu.be/vjOrIxpyLPY

የባንኩን ረቂቅ አዋጅ በእንግሊዝኛ እና በአማርኛ እንዲሁም የአዋጁን ማብራሪያ pdf ማንበብ ለምትፈልጉ ከላይ አስቀምጫለሁ።








የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲሱ አዋጅ 5 ዋና ዋና ለውጦች! የውጪ ባንኮች የሚገቡባቸው 4 ዘዴዎች! ለዲያስፖራው የተመለሰው የኢንቨስትመንት እድል....

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ አዲስ አዋጅ ፀድቆለታል! በዚህ አዋጅ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚን መወሰን የሚችሉ ዋና ዋና ማሻሻያዎች ተካተውበታል!

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ተፅዕኖ የሚፈጥሩትን የአዋጁን 5 ዋና ዋና ድንጋጌዎች በዝርዝር እንመልከት...https://youtu.be/vjOrIxpyLPY


#በጣም_ጥሩ_መረጃ፡ የኢትዮጲያ ሰነደመዋለንዋይ ገበያ #ዲጂታል_አካዳሚ መጀመሩን በይፋ አብስሯል።

የኢትዮጲያ ሰነደመዋለንዋይ ገበያ "ESX Academy" የተሰኘውን የመማሪያ ፕላትፎርም ያስተዋወቀ ሲሆን ይህም ከFSD Ethiopia ጋር በመተባበር የተሰራ ፕሮጀክት ነው።

ፕላትፎርሙ የተለያዩ ኮርሶችን አንድ ላይ የያዘ ሲሆን ከነዚህም፡
1. ካፒታል ገበያ እንዴት ነው የሚሰራው?
2. ኢንቨስትመንት ስትራቴጂ
3. ሻሪያን ስላገናዘቡ ምርቶች
4. የኢትዮጲያ ሰነደመዋለንዋይ ገበያ በኢትዮጲያ ኢኮኖሚ ላይ ስላለው ሚናና ያካትታል።

ኮርሶቹን esxacademy.com ላይ ገብተው መውሰድ ይችላሉ።
ኮርሱን ያጠናቀቁ ሰዎች በስራ አስፈጻሚው የተፈረመ ሰርተፊኬት በኢሜላቸው ይደርሳቸዋል!


የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ገቢ ለማመንጨት ሲል እየተጨነቀ ነው!

የኢትዮጵያ መንግስት በ2017 የ1.5 ትሪሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ አቅዷል! ይህንን የገቢ እቅድ ለማሳካት ሲባል በፌደራል እና በክልል ደረጃ የሚወሰዱ እርምጃዎች ኢኮኖሚውን እያስጨነቁት ነው።

የሚወሰዱ እርምጃዎች እየፈጠሩ ያሉት ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግር "The Cobra Effect" እንዳያመጣ ያሰጋል!

በዝርዝር እንመልከተው https://youtu.be/UiaO3c58NtQ


የአጠቃላይ ትምህርት ረቂቅ አዋጅ .pdf
498.2Кб
አጠቃላይ ትምህርት ረቂቅ አዋጅ።


#ለመረጃ (የሚገርም!) ለህዝብ ተወካዮች የቀረበው አጠቃላይ የትምህርት ረቂቅ አዋጅ

አንድ የግል ትምህርት ቤት በገበያው ለመቆየት "የትምህርት ቤቱን መምህራንና ሌሎች ሰራተኞች የ6 ወር ደመወዝ ክፍያ ለመሸፈን የሚችል በዝግ የባንክ ሂሳብ የተቀመጠ እና በባንኩ የተረጋገጠ ሂሳብ" ያስፈልጋል ይላል።

ለተቃራኒ ውጤት የተጋለጠ ረቂቅ!


በዋና መንገዶች ላይ የንግድ ተቋማት እስከ ምሽቱ 3:30 አገልግሎት እንዲሰጡ ተወስኗል!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 4ኛ ዓመት 4ኛ መደበኛ ስብሰባ ባካሄደበት ቀን "በሁሉም የከተማዋ ዋና ዋና መንገዶች ያሉ የንግድ እና የአገልግሎት መስጫ ተቋማት እስከ ምሽቱ 3፡30 ለህብረተሰቡ የተሟላ አገልግሎት እንዲሰጡ" የሚል ውሳኔ አስተላልፏል!

ውሳኔው ሰው ሰራሽ የአካባቢ ዋጋ ሊፈጥር ይችላል!

የዚህ ውሳኔ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ምክንያታዊነት የተመጣጠነ ስለመሆኑ እንመልከት!https://youtu.be/AV5QYFpjj1w


ገቢዎች ቢሮ ድርጅቶች ሊኖራቸው የሚገባውን የሰራተኞችን ቁጥር እና ሊከፈል የሚገባውን ዝቅተኛ ደመወዝ ወለል ወሰነ!

በዚህ ውሳኔ በሆቴሎች እና ሌሎች የንግድ ዘርፎች ላይ አሰሪዎች ለሰራተኞቻቸው የደሞዝ ጭማሪ እንዲያደርጉ የሚያስገድድ ተመን ይሆናል።

ከአስተናጋጅ፣ ጥበቃና የፅዳት ሙያ ውጭ ላሉ ሰራተኞች ትንሹ የሚከፍሉት ደመወዝ 5,000 ብር ሆኖ ተተምኗል።

በዚህም የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በግብር  ሂደት  ውስጥ የሚፈጠሩ ማጭበርበሮችን ለመቀነስ ዓላማው ያደረገ ለሆቴሎች፣ ለስጋ ቤቶች፣ ለመጠጥ ቤቶች እና ለተለያዩ የተመረጡ የንግድ ዘርፎች ለሰራተኞቻቸው አነስተኛ የደመወዝ ወለል እና የሰራተኞችን ብዛት የሚተምን ተመን ይፋ አድርጓል።

በዚህ ውሳኔ ዝቅተኛ የደሞዝ መጠን እና ዝቅተኛ የሰራተኛ ብዛት የተቀመጠውን እና የውሳኔውን ተፅኖ እና ደካማ ምክንያታዊነት እንመልከት....https://youtu.be/6kxo14riypA


በሆቴሎች እና ሌሎች የንግድ ዘርፎች ላይ ለሰራተኞቻቸው የደሞዝ ጭማሪ እንዲያደርጉ የሚያስገድድ ተመን ወጣ!

ከአስተናጋጅ፣ ጥበቃና የፅዳት ሙያ ውጭ ላሉ ሰራተኞች ትንሹ የሚከፍሉት ደመወዝ 5,000 ብር ሆኖ ተተምኗል።

በዚህም የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በግብር  ሂደት  ውስጥ የሚፈጠሩ ማጭበርበሮችን ለመቀነስ ዓላማው ያደረገ ለሆቴሎች፣ ለስጋ ቤቶች፣ ለመጠጥ ቤቶች እና ለተለያዩ የተመረጡ የንግድ ዘርፎች ለሰራተኞቻቸው አነስተኛ የደመወዝ ወለል እና የሰራተኞችን ብዛት የሚተምን ተመን ይፋ አድርጓል።

በዚህ ውሳኔ ዝቅተኛ የደሞዝ መጠን እና ዝቅተኛ የሰራተኛ ብዛት የተቀመጠውን እና የውሳኔውን ተፅኖ እና ደካማ ምክንያታዊነት እንመልከት....https://youtu.be/6kxo14riypA


የዓለማችን 10 ሃብታሞች! The 10 Richest People in the World (Forbes 2024)!

ፎርብስ በ2024 የቢሊየነሮች ቁጥር 2,781 መድረሱን አሳውቋል፡፡ የባለሃብቶቹ ድርጅቶች 1% ድርሻ የብዙ ሀገራትን ጠቅላላ የምርት መጠን (GDP) በብዙ እጥፍ ይበልጣል.....

ለምሳሌ….

1. የኢለን መስክ ሃብት የኢትዮጲያ GDP እጥፍ ነው!

2. የAmazon ካምፓኒ 10% ድርሻ ከኢትዮጲያ ጠቅላላ (GDP) ይበልጣል!

ሃብታሞች የዓለምን የኢኮኖሚ፤ የፖለቲካ እና የማህበራዊ ድጋፍ አቅጣጫ የመወሰን አቅም አላቸው፡፡

የሃብት መጠናቸውን እና የቢዝነስ ዘርፍ እና ስልት በዝርዝር እንመልከት! https://youtu.be/4_1T1A1xcDU


#ለመረጃ፡ የኢትዮጵያ የቀረጥና ታክስ ሕጎች በቀላሉ የሚገኙበት የኦንላይን ድረ ገጽ ይፋ ሆኗል፡፡ የገንዘብ ሚኒስቴር ያዘጋጀው ድረ ገጽ፡ ከ300 በላይ የታክስ ሕጎች በአማርኛ እና እንግሊዝኛ ቋንቋዎች የተቀመጡበት ነው።

ድህረገጹን ለምትፈልጉ https://ethiopia.mylexisnexis.co.za/#/navigation-view;listCode=LNSA

ድረገፁ የገንዘብ ሚኒስቴር “ከሌክሲስ ኔክሲስ ሩል ኦፍ ሎው ፋዌንዴሽን” ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ነው።

Показано 20 последних публикаций.