Репост из: [ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]
መጅሊሱ የማን ተወካይ ነው???
። ። ።
በሀገራችን ውስጥ በተለያዩ አጋጣሚዎች በተለያየ መንገድ የተለያዩ ችግሮች ሲፈጠሩ ይስተዋላል። አንዳንዴ የብሔር ግጭት፣ ሌላ ጊዜ የሀይማኖት፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ከዜጎች የመብት ጥያቄ ጋር በተያያዘ ህዝብ ከመንግስት ጋር ግጭት ሲፈጥር ይስተዋላል።
ታዲያ ሁሉም ለተለያዩ የፖለቲካ አጀንዳዎች በየ አቅጣጫው ግጭቶችን በመቀስቀስም ይሆን በሌላ መንገድ የሚፈልገውን የህዝቡን ክፍል ለማሳመን ሲፍጨረጨር ይስተዋላል።
በዚህ አጋጣሚ ደግሞ የሚጎዳው መሃል ላይ ያለው ሚስኪኑ ህዝባችን ነው። "ሁለቱ በሬዎች ሲፋለሙ የሚቸግረው ሳሩ ነውና" በእንዲህ ያሉ አጋጣሚዎች ችግሩ የሚደርስበት ከታች ያለው አካል ነው። አንዳንዴ በብሔር ሌላ ጊዜ ደግሞ በሃይማኖት የከፋ ችግር ውስጥ ይወድቃል።
በእንዲህ ያሉ አጋጣሚዎች ደግሞ ለፖለቲካውም ይሁን ለጥቅሙ አለያም እውነተኛ ተቆርቋሪም ይሁን በሀይማኖትም ሆነ በብሔር ለተጎዳው አካል የሚከራከርለትና ችግር እንደ ደረሰበት የሚያሳውቅለት፣ ተገቢውን ካሳ እንዲያገኝና ዳግም የችግሩ ሰለባ እንዳይሆን አስፈላጊውን ጥረት የሚያደርግለት ተወካዩ የዚያ ሀይማኖት ወይም ብሔር ተጠሪ የሆነው አካል ነው።
ከላይ እንደጠቀስኩት ሀገራችን የተለያዩ ችግሮች እየገጠሟት ቆይታለች፣ በቅርብ ጊዜ ደግሞ የፖለቲካ አለመግባባቶች ጎልተው እየወጡ በመሄዱ የተለያዩ ፖለቲከኞች መታሰራቸውን ተከትሎ ሙስሊሞች የሚበዙባት ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ከፍተኛ ቀውስ ተከስቷል።
ይህን ተከትሎ በክልሉ የሰው ህይወት እንደ ቅጠል መርገፉን እና ንብረትም መውደሙን በተለያየ አቅጣጫ ሰምተናል። ሁላችንም እንደታዘብነው "የጋራ ነው" የሚባለው የመንግስት ሚዲያ እንደ ልማዱ የአንዱን ወገን ጩሀት ብቻ ሲያስተጋባ ቆይቷል። ተወካዮችም እንደ ሀይማኖትም እንደ ብሔርም (የሙስሊሙ ተወካይ ነው ሚባለው መጅሊስ ሲቀር።) ሁሉም የኔ ነው ብለው ለተወከሉለት አካል ጩሀቱን ሲያስተጋቡና አልፎ ተርፎ ለበቀል ሲያነሳሱ ቆይቷል።
ሙስሊሙ ማህበረሰብ ግን ሁሌም የቲም ነው። ኢኽዋኑም፣ ሱፊይና አሽዓሪውም እንደ አመችነቱ በደሙ ይነግዱበታል። ኢኽዋኑም ወንበሩ ስትነቃነቅበት ህዝቡን ምንም ላይፈይደው ቁስሉን ነካክቶ በማነሳሳት ይጠቀምበታል፣ ወንበሩ ስትረጋጋ ደግሞ ህዝቡን ያነሳሱበት ነጥብ እንኳን ያስነቃብናል ብለው ሳይሸማቀቁ "በጥቃቅን ነገር አትከፋፍሉን፣ ሁላችንም አንድ ነን፣ እጅ ለእጅ ተያይዘናል" ብለው ፍጥጥ ይላሉ። ያው "የሌባ ዐይነ ደረቅ…" እንደሚባለው ነው።
ሙስሊሙን አሽዓሪያውና ሱፊዩም (አህባሹ) ከከሀዲዎች ጋር ሆኖ ለወንበሩ ፊዳ ያደርገዋል። ይወክለኛል የሚለው መጅሊስ ዋና ፀሃፊ አሽዓሪያው አቶ ቃሲም ታጁ በሰሞኑ ኦሮሚያ ክልል ውስጥ የተከሰተውን የኢማሞችን ግድያ አስመልክቶ ከመጅሊሱ የስራ ቦርድ ጽ/ቤት የተሰጠውን መግለጫ "ህገ ወጥ ነው፣ ተገደሉ የተባለውም ያልተጣራ ወሬ ነው።" ብሎ በማጣጣል ለአሜርካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያ (VOA) ሲናገር ሰምቼው በጣም ተገረምኩ። (ያልተጣራ ነው ብሎ ካመነበትም ህዝበ–ሙስሊሙን ወክሎ ከተቀመጠ ከማንም በፊት ፈጥኖ ደርሶ በማጣራት ትክክለኛውን መፍትሄ መፈለግ የነበረበት ራሱ የፌዴራል መጅሊስ አመራር ነበር፣ ቢያንስ ደግሞ አብዘሃኛው ሙስሊም የሆነበት ክልል የሟቹ ቁጥር ከፍ ሲል ከፍተኛው የሟች ቁጥር ሙስሊሙ እንደሆነ ጥርጥር የለውም!።)
ይህን መናገር ከነሱ የማይጠበቅ ስለሆነ ሳይሆን፣ መንግስት እንኳን ክስተቱን አምኖ የኦሮሚያ የፀጥታ ዘርፍ ኀላፊው አቶ ጂብሪል መሀመድ "በስህተት የተፈጠረ ክስተት ነው" በማለት የተናገሩትን ተጨባጭ ይነቃብኛል ሳይል ለሙስሊሙ ያለውን ንቀት ማሳየቱ ነው።
"ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአንድ ሙስሊም ደም ከሚፈስ ከዕባ ቢወድም ይሻላል" በማለት የሙስሊምን ደም ክብደት የገለፁትን፣ እሱ ግን የከሃዲዎችን ፊት ፍለጋ በሙስሊሙ ደም ይቀልዳል።
ታዲያ ይህ መጅሊስ ውክልናው ለማን ነው?! ለህዝበ–ሙስሊሙ እንዳልሆነ እንዲህ ያሉ በርካታ ተግባሮቻቸው እየገለፁልን ነው። ከሀዲዎች ተገደለብን እያሉ ሲያስተጋቡ ተቀብሎ እንደ ገደል ማሚቱ የሚያስተጋባላቸው መጅሊስ፣ ሙስሊሙ የመስጂድ ኢማሜ ተገደለብኝ ሲል ደግሞ ለገዳዩ ወግኖ "ያልተጣራ ወሬ" እያለ የሚያጣጥልና ከቻለም ሰምቶ እንዳልሰማ የሚሆን መጅሊስ ማንን ነው የሚወክለው?!
አላህ በእዝነቱ ሙስሊሙን ከሸረኞች ሴራ ይጠብቅ!! ሀገራችንም አላህ ሰላም ያድርጋት!!
✍🏻ኢብን ሽፋ: ሙሀረም 12/1442 ዓ. ሂ
ነሀሴ 25/2012 ኢትዮ
#Join ⤵️
https://telegram.me/IbnShifa