Фильтр публикаций






የሕጻናት ቆረቆር በሽታ ስርጭትን ለመግታት የሚያስችል የምርምር ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ

የዩኒቨርሲቲው የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የሕጻናት ቆረቆር በሽታ ስርጭትን ለመግታት የሚያስችል የተቀናጀ የማኅበረሰብ አቀፍ የምርምር ፕሮጀክት ሥራ ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር ሚያዝያ 16/2017 ዓ.ም አካሂዷል፡፡

የምርምር ጉዳዮች ዳይሬክተር ዶ/ር ተስፋዬ ሀብተማርያም ፕሮጀክቱ 1.75 ሚሊየን ብር የተበጀተለት የግራንድ ምርምር ፕሮጀክት መሆኑን ገልጸው ለፕሮጀክቱ መሳካትና ትግበራ ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡና ትብብራቸው እንዳይለይ አሳስበዋል፡፡

የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጥናትና ምርምር ኮርፖሬት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ዘሪሁን ዘርዶ የቆሮቆር በሽታን አስመልክቶ ማኅበረሰቡ ዘንድ የግንዛቤ ችግር ያለ መሆኑን ጠቁመው ይፋ የተደረገው ፕሮጀክት ከዚህ ጋር የተገናኙና ሌሎች ችግሮችን ለመቅረፍ ጠቃሚ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ የምርምር ፕሮጀክቱ ሲካሄድ ማኅበረሰቡን ያሳተፈና ያማከለ መሆን ይገባዋል ያሉት ዶ/ር ዘሪሁን በተለይ በፀጉር ቤቶች ዘንድ የሚታዩ ችግሮች ላይ ማተኮር ይገባል ብለዋል፡፡

በሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የቆዳና አባላዘር ሕክምና ትምህርት ክፍል ኃላፊ፣ የቆዳና አባላዘር በሽታ ስፔሻሊስት ሐኪምና የፕሮጀክቱ ዋና ተመራማሪ ዶ/ር ምህረት ተጫኔ የሕጻናት ቆረቆር በሽታ የሕጻናትን ጭንቅላት የሚያጠቃ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ፕሮጀክቱ የ3 ዓመት ቆይታ ያለው መሆኑን የገለጹት ዶ/ር ምሕረት ከጥናት ባሻገር በጥናቱ ውጤት ላይ የተመሠረተ ማኅበረሰብ አቀፍ ትግበራ በት/ቤቶች፣ በፀጉር ቤቶችና በጤና ተቋማት የሚደረግ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የመድረኩ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት በበሽታው ዙሪያ ከቀረበው መግለጫ ብዙ ግንዛቤ ያገኙ መሆናቸውን ገልጸው ለፕሮጀክቱ መሳካት የበኩላቸውን እንደሚወጡና የማኅበረሰቡን ግንዛቤ ለማዳበር እና የበሽታው ተጠቂ የሆኑ ሕጻናት ተገቢውን ሕክምና እንዲያገኙ ለማድረግ ጥረታቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ቃል ገብተዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ ከዞንና ከከተማ ጤና መዋቅሮች የተወጣጡ የበሽታ መከላከል የሥራ ኃላፊዎች፣ የጤና ኤክስቴንሽን አስተባባሪዎች፣ በአርባ ምንጭ ከተማ የሚገኙ ጤና ተቋማት ኃላፊዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት


ማስታወቂያ

ትምህርት ሚኒስቴር ከሰኔ 2/2017 ጀምሮ የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ለሚወስዱ መደበኛ እና ኢ-መደበኛ ፕሮግራም ዕጩ ተመራቂዎች እና ዳግም ተፈታኞች ፈተናውን ለመውሰድ የብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) እንደቅድመ ሁኔታ ማስቀመጡ ይታወቃል።

በመሆኑም በዩኒቨርሲቲያችን ትምህርት ላይ ያላችሁ እና ከዚህ ቀደም ተፈትናችሁ ማለፊያ ውጤት ሳታሟሉ የቀራችሁ ዳግም ተፈታኞች ከወዲሁ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ምዝገባ እንድታካሂዱ አጥብቀን እናስታውቃለን።

በዚህ መሰረት:-

የመጀመሪያ ዙር ተፈታኞች የመታወቂያውን FAYDA FIN ቁጥር እስከ ረቡዕ ሜያዚያ 22/2017 ዓ/ም ድረስ በአካዳሚክ ፕሮፋይላችሁ /SMiS) እንድታስገቡ፣

ዳግም ተፈታኝ አመልካቾች የአገልግሎት ክፍያ በቴሌ ብር በኩል ብቻ ከፍላችሁ ከሚያዝያ 14/2017 ዓ.ም እስከ ግንቦት 05/2017 ዓ.ም ድረስ ከላይ የተጠቀሱትን ቅድመ ሁኔታዎች በማሟላት በhttps://exam.ethernet.edu.et በኩል መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ማሳወቁን እንገልጻለን፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጂስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት




በፕሬዝደንት ጽ/ቤት ሥር የሚገኙ የሥራ ክፍሎች የ3ኛ ሩብ ዓመት ሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ተገመገመ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ጽ/ቤት በሥሩ የሚገኙ ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤቶችን የ2017 በጀት ዓመት የ3ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን ዛሬ ሚያዝያ 16/2017 ዓ.ም ገምግሟል፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ከአምላክነሽ ደሳለኝ በመድረኩ በሥራ ክፍሎቹ በሩብ ዓመት በቁልፍና ዝርዝር ተግባራት ታቅደው የተሠሩ ሥራዎች ፣ ጠንካራ አፈጻጸሞች፣ መሻሻል ያለባቸው ጉዳዮች፣ ያጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ የመፍትሔ እርምጃዎች በዝርዝር ቀርበው መገምገማቸውን ገልጸው ድክመት የታየባቸው ጉዳዮች ደግሞ በቀጣይ ትኩረት ተሰጥቶባቸው እንዲሠሩና ተሻሽለው እንዲቀርቡ አቅጣጫ መቀመጡን ጠቁመዋል።

ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት ግምገማው ሥራዎችን ትኩረት ሰጥቶ በጥራት ለመሥራትና ከትምህርት ሚኒስቴር የተሰጡንን ቁልፍ ተግባራት በወቅቱ ለመፈጸም የሚረዳ መሆኑን ገልፀዋል።

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት



Показано 7 последних публикаций.