የትምህርት ቤት ምገባ መርሃ-ግብር የትምህርት ተሳትፎና ጥራት ለማረጋገጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ተገለጸ፡፡
------------------------------------------------
የካቲት 26 /2017 ዓ.ም 10ኛው የአፍሪካ የትምህርት ቤት ምገባ ቀን በሐረሪ ብሔራዊ ክልል መንግስት በሐረር ከተማ በሚገኘው ሞዴል አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከብሯል።
በክብረበዓሉ ላይ የተገኙት የሐረሪ ብሔራዊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ኦርዲን በድሪ የትምህርት ቤት ምገባ መርሃ-ግብር ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገትን ለማረጋገጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸዋል፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ አክለውም መርሃ-ግብሩ የመማር ማስተማር ሂደቱን ይበልጥ ውጤታማ በማድረግና የትምህርት ተሳትፎ እና ጥራትን ከማሳደግ ባለፈ የትምህርት ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ እንደሚያግዝም ጠቁመው መርሃ-ግብሩ ከሚሰጠው ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አንጻር ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት መሆኑን ጠቅሰዋል። ከመርሃ-ግብሩ አንጻር በክልሉ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።
በትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ የትምህርት ቤት ምገባ መርሃ-ግብር በለውጡ መንግስት ትኩረት ተሰጥቶት ቀጣይነት ባለው መልኩ በስፋት ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኝና ውጤት እያስመዘገበ ያለ መርሃ-ግብር መሆኑን ገልጸዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤
https://www.facebook.com/share/p/1CNAcDWr4w/