በደቡብ ምዕራብ ቀጣና የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ስፖርት ውድድር ተጠናቀቀ።
--------------------------------
(የካቲት 24/2017 ዓ.ም) በጅማ ከተማ አስተናጋጅነት ሲካሄድ የቆየው በደቡብ ምዕራብ ቀጣና ስር የተደለደሉ የጅማ ዞን ት/ቤቶች ስፖርት ሊግ ውድድር ተጠናቀቀ፡፡
በጅማ ዞን ስር የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ውድድር ፍጻሜውን ሲያገኝ በወንደች እግር ኳስ ሰቃ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ናዳ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን 5 ለ 1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የዋንጫ ተሸላሚ ሲሆን በወንዶች ቮሊ ቦል ደግሞ ቀርሱ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ስግሞ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን 3 ለ1 በማሸነፍ የዋንጫ ባለቤት ሆኗል፡፡
በሴቶች ቮሊ ቦል ዶዮ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት አሌ ትምህርት ቤትን 3 ለ 0 በማሸነፍ የዋንጫ አሸናፊ ሆኗል፡፡
በአትሌትክስ ስፖርት ብዙ ሜዳሊያዎችን የሰበሰበው ማና ወረዳ ትምህርት ቤቶች የአጠቃላይ አሸናፊ በመሆን የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል፡፡
ውድድሩም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳዎች ጎልተው የወጡበትና በየስፖርት ዓይነቱ ጥሩ ስፖርታዊ ክህሎት ያላቸው ተማሪዎች የታዩበት የውድድር መድረክ ሆኖ መጠናቀቁ ተገልጿል፡