ስለምን ልናገር?
👉ስለ እኔ የጨለማ ኃጢአት፤ወይንስ ስለ እመብርሃን ርኅርኅተ ልብነት?
👉ስለኔ ደካማነት፤ወይንስ ስለ አዛኝቷ አማላጅነት ስለ ልጇ ብርታት ሰጪነት?
👉ስለ እኔ የኃጢአት በሽተኝነት፤ወይንስ ስለ ማርያም መድኃኒትነት ስለ ልጇ ቤዛነት?
👉ስለ እኔ አለመቻል፤ወይንስ ስለ አንድያ ልጇ ኤልሻዳይነት?
👉ስለኔ ቃል ዓባይነት፤ወይንስ ስለ እሷ የቃል ኪዳን ምሕረት?
👉ስለኔ ድብቅ ኃጢአት፤ወይንስ ስለ ልጇ ከባቴ አበሳነት?
ስለምን መናገር እንዳለብኝ እና እንዴት መጸለይ እንዳለብኝ ግራ ሲገባኝ ከነ ጉድፍ ማንነቴ ከነ ርኩሰቴ ከመቅደሱ እገባና
እመ ብርሃንን አያታለሁ። ኃጢአቴ በመላ እፊቴ ይከመርና አንገት እደፋለሁ፤ አቀረቅራለሁ፤ከልቦናዬ ጋ እነታረካለሁ፤
ምን ጊዜ እንደጀመረ ያላወቅኩት የ ዕንባዬ ጅረት ይበልጡኑ ይጨምራል፤ጉንጮቼ ይርሳሉ፤ልቤ ይንሰቀሰቃል፤የምለው ይጠፋኛል፤የምገባበት አጣለሁ፤
አንዳች የምለውን ቢያቀብለኝ ብዬ ቅዱሱ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫን እማጸነዋለሁ፤
ከሱ ጋር በመሆን በአርጋኖን እንዲህ እላታለሁ
" የሰራሁትን ኃጢአት ባስበው ልቡናዬ እጅግ ደነገጠብኝ አእምሮ ሳለኝ አለል ዘለል እያልኩ በጽርዓት መኖሬን ባሰብሁት ጊዜ ልቡናዬ እጅግ ደነገጠ
የኃጢአቴን ብዛት በተቆጣጠርሁ ጊዜ ልቡናዬ እጅግ ደነገጠ አንድ ሰዓት ስንኳን አላቋረጥኩም
በሰውና መላእክት ጉባኤ መሐከል ራቁቴን መቆሜን አሰብሁ
በዓይነ ልቡናዬ እመለከት ዘንድ ወዲህና ወዲያ ተመላለስሁ
ምናልባት የሚረዳኝ ባገኝ ከዚህ እጅግ የሚያስፈራው ከሠራሁት ኃጢአት ፍዳ የተነሳ ምናልባት የሚዋሰኝ ባገኝ ብዬ
ነገር ግን በማማለድ እኔን ለማዳን የምትችይውን አንቺን አማላጅ አገኘሁ ዘወትርም ከጎኔ እንዳትርቂ ዐወቅሁ
እንዲህ በፍቅር ያዝሁሽ በጣቶቼ አይደለም
በሃይማኖት ያዝሁሽ በመዳሰስ አይደለም በእደ ሕሊና ያዝሁሽ በእደ ሥጋ አይደለም" አርጋኖን ዘሠሉስ
👉ስለምን ልናገር ስለኔ አለል ዘለል ማለት፤ ወይንስ ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ትህትና?
👉ስለ ሀዘኔ፤ ወይንስ የደስታ መፍሰሻ ስለሆነችኝ ስለ እመ ብርሃን፤ወይንስ ደስታ ስለሆነኝ መድኃኔዓለም?
ስለምን ልናገር?
❤እመቤቴ ሆይ የምናገረውን አላውቅምና አንደበት ሁኚኝ፤
ርግማን ከቦኛልና በበረከትሽ ጎብኚኝ፤
አንድ ጊዜ እዪኝ...
https://t.me/felege_tibeb