አውደ Tibeb


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Религия


❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️♥♥♥♥♥♥♥♥♥
ከጥበብ ምንጭ
አብረን እንጎንጭ!!!
መንፈሳዊ፣ሀገራዊና፣ፍቅር ነክ ግጥሞች፤
ትረካ፣መነባንብ እና ለድራማ የሚሆኑ ጽሁፍች ከዚ ቻናል ያገኛሉ!!!
በሚመቾት መንገድ
የሚፈልጉትን ጽሁፍ እንጽፋለን ለትዕዛዞትና
ለአስተያትዎ @zemeden_bot
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️♥♥♥♥♥♥♥♥♥

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Религия
Статистика
Фильтр публикаций


ትንሽ የመከፋት ስሜት ውስጥ ነበር በጣም የመደበር እናም ወንድሜ Dani Terefe  ውድድር ሞክር ብሎ ማስፈንጠሪያ ላከልኝ ብቸኝነት ወሮኝ በነበረ ሰዓት መልዕክቱን ሳነበው ለምን ስሜቴን አልጽፍም ብዬ አሰብኩ እናም ስሜቴን እንደወረደ ጻፍኩት በመሰረቱ ውድድር አይመቸኝም ነገር ግን ምን አልባትም ውስጤ ደስ ሊሰኝበት የሚችለውን አሳብ ባጋራ ብዬ ወደድኩ
ከሰዎች ሳንጠብቅ ለምናደርገው ነገር ሁሉ ብድራቱን ፈጣሪ እንደሚከፍል ከቃል በላይ በተግባር ስላየሁት ቸኩዬ ይሕንን ግጥም ለጠፍኩ እግዚአብሔር ይመስገን እናም ምናልባት ከተመቻችሁ Bejai Nerash Naiker  ቤት ሂዱና አሳባችሁን አጋሩኝ አመሰግናለሁ

ሰው የለኝም እያልኩ፣እየተመቸኝም፣የምተክዝ ዛሬ፤
ውዬ አውቅ ይሆን መልካም፣ለሰዎች ኑባሬ?
ነገዬን አላውቅም፣በመቄዶንያ፣ትናንቴን ላድሰው፤
ትቢያ ከመሆኔ፣እንዳልዘነጋ፣እስቲ ላንሳ አንድ ሰው።
ሄኖክ ክበበው
አውደ Tibeb
እስቲ Fb ግቡና ለይኩልኝ ማስፈንጠሪያውን አስቀምጫለሁ

https://www.facebook.com/share/p/1BTPvkeDV4/


ትንሽ የመከፋት ስሜት ውስጥ ነበር በጣም የመደበር እናም ወንድሜ Dani Terefe ውድድር ሞክር ብሎ ማስፈንጠሪያ ላከልኝ ብቸኝነት ወሮኝ በነበረ ሰዓት መልዕክቱን ሳነበው ለምን ስሜቴን አልጽፍም ብዬ አሰብኩ እናም ስሜቴን እንደወረደ ጻፍኩት በመሰረቱ ውድድር አይመቸኝም ነገር ግን ምን አልባትም ውስጤ ደስ ሊሰኝበት የሚችለውን አሳብ ባጋራ ብዬ ወደድኩ
ከሰዎች ሳንጠብቅ ለምናደርገው ነገር ሁሉ ብድራቱን ፈጣሪ እንደሚከፍል ከቃል በላይ በተግባር ስላየሁት ቸኩዬ ይሕንን ግጥም ለጠፍኩ እግዚአብሔር ይመስገን እናም ምናልባት ከተመቻችሁ Bejai Nerash Naiker ቤት ሂዱና አሳባችሁን አጋሩኝ አመሰግናለሁ

ሰው የለኝም እያልኩ፣እየተመቸኝም፣የምተክዝ ዛሬ፤
ውዬ አውቅ ይሆን መልካም፣ለሰዎች ኑባሬ?
ነገዬን አላውቅም፣በመቄዶንያ፣ትናንቴን ላድሰው፤
ትቢያ ከመሆኔ፣እንዳልዘነጋ፣እስቲ ላንሳ አንድ ሰው።
ሄኖክ ክበበው
አውደ Tibeb


https://www.facebook.com/share/p/1BTPvkeDV4/










Репост из: አውደ Tibeb
በተስፋ ይሆናል
✍ሄኖክ ክበበው
በህልም ዓለም ቅዠት በቀን ድንዛዜ፤
ደስታን እየሻቱ በመኖር አባዜ..
መዳኅ መራመድ መሯሯጥ ሁልጊዜ፤
ለነገ ብርሃን ነው ለህይወት አዋዜ።
❤በተስፋ ይሆናል❤
መፈራረቃቸው ብርድና ሀሩሩ፣
ማኀለቅት አልባው ጉዞ መራዘም ማጠሩ፣
አዕምሯችን ከንፎ ያለ ልክ መብረሩ፣
ሁሉንም ለማግኘት መቸኮል መጣሩ፣
የዚ ሁሉ ክሥተት የሁነት ምሥጢሩ፣
መጓዝ ሆነና ነው የህይወት ቀመሩ።
❤በተስፋ ይሆናል❤
ርቀት ይመስላል መድረሻ መንገዱ፤
ያደክምም ይሆናል ዓልመው ሲነጉዱ፤
ግና ....
ህልምን አሻግሮ አይቶ፣
በተስፋ ተመልቶ፣
ተግባርን አጉልቶ፣
በአምላክ ተመክቶ፤
መኳተን መፈለግ መመኘት መቋመጥ፣
ጥቂቱን ህልም አሳድጎ ሌተ ቀን መሯሯጥ፣
በሰዎች ህይወት ያመጣል ትልቅ ለውጥ።
❤በተስፋ ይሆናል❤
የህይወት ጥጓ ሞት የሞት ጥግ ዘላለም፤
በዘላለም ኑሮ ...
በዕረፍት በፍስሃ አለያም በሀዘን ማዝገም፤
ቢሆንም እንኳ የመጨረሻው መጨረሻ፤
ማለሙ አይከፋም ቀድሞ ከመነሻ።
❤በተስፋ ይሆናል❤
መልካም ነገር ሁሉ...
በአዕምሮ ታስቦ በልብ ይሰነቃል፤
በተስፋ ይሆናል በእምነት ይፀናል፤
በፈጣሪ ፈቃድ ሁሉም ይከወናል።
✍ሄኖክ ክበበው መጋቢት 8 2013
https://telegram.me/felege_tibeb
ፈለገ ጥበብ Felege tibeb በሄኖክ ክበበው




#ልደታ
#እንኳን_አደረሳችሁ
https://t.me/felege_tibeb




#በመጠን_የማንገልጠው_ፍቅር
#ከዘወረደ_እስከ_ሆሣዕና
#ሕማማት
መድኃኔዓለም አባቴ ሆይ የፍቅርህን ልኬት፣የመውደድህን መዳረሻ፣የርኅራኄህን ጥግ፣የችሮታህን መጠን እኔን ያለ ምክንያት የመቤዠትህን ምሥጢር ዘመኔን በሙሉ ባጤንና ብመራመር እንዳልደርስበት ሳውቅ በድንቅ ሥራህ እደነቃለሁ፤ መውደድህን ተመልክቼ ዕፁብ እላለሁ፤ ፍቅርህን ዐይቼ በዕንባዬ እታጠባለሁ፤ በዝምታ እገረማለሁ በአንደበቴም ተመስገን እልሃለሁ፤ ፍቅሬን አንተ በገለጥክልኝ መጠን መግለጥ እንዳልችል ሳውቅ እጅጉን በራሴ አዝናለሁ፤ አንተ ታላቁን ዕቅድ በሕይወቴ ስታቅድ እኔ በዛሬ እፈትንኃለሁ፤
አንተ መንገዴን ስታቀና እኔ በአቋራጭ እፈትንኃለሁ፤
እንዲያም እያሳዘንኩህ አንተ ግን ለኔ ዋጋ ከፍለህ ከማዳን ቸል አላልክም፤የረከስኩት እኔን ለመቀደስ ከሰማያት ወርደህ፤
መጻጉእ ውስጠቴን ልታክም ከምኩራብ ልቤ ገብተህ፤
ስለ ዳግም መምጣትህ በደብረዘይት ልትነግረኝ፣ገብርኄር(ቸር አገልጋይ) እንድሆን መክሊትን ልትሰጠኝ፤ ዳግም እንደምትወልደኝ በኒቆዲሞስ ነግረኸኝ፣በኃጢኣት ብዛት የታሰርኩትን የተናቅኩትን እኔን ልትፈታ በተናቀች አህያ ጀርባ ሆነህ በእግዚአብሔር ስም የመጣኸው ቡሩክ የእግዚአብሔር ልጅ እግዚአብሔር ሆይ በዚያ የተከተለህ ሕዝብ ሆሣዕና እያለ ልብሱን አውልቆ እንዳነጠፈልህ እኔም ልቤን ከአምላክነትህ እንዳነጥፍ ርዳኝ፤ ጠዋት አክብሬህ ከሰዓት አንተን ስለመስቀል ስለኃጢኣት ከመምከር ጠብቀኝ፤ለቤዛነት የመጣኸው ሆሣዕና ክርስቶስ ሆይ ስለኔ የከፈልከው ዋጋ እጅግ የከበደ ነውና ተመስገን።
ጌታ ሆይ ስለኔ የከፈልከውን ዋጋ እንዳልረሳ ውሳጣዊ ዐይኖቼን አብራልኝ አሜን
ተመስገን
እንኳን አደረሳችሁ
https://t.me/felege_tibeb












ስለምን ልናገር?
👉ስለ እኔ የጨለማ ኃጢአት፤ወይንስ ስለ እመብርሃን ርኅርኅተ ልብነት?
👉ስለኔ ደካማነት፤ወይንስ ስለ አዛኝቷ አማላጅነት ስለ ልጇ ብርታት ሰጪነት?
👉ስለ እኔ የኃጢአት በሽተኝነት፤ወይንስ ስለ ማርያም መድኃኒትነት ስለ ልጇ ቤዛነት?
👉ስለ እኔ አለመቻል፤ወይንስ ስለ አንድያ ልጇ ኤልሻዳይነት?
👉ስለኔ ቃል ዓባይነት፤ወይንስ ስለ እሷ የቃል ኪዳን ምሕረት?
👉ስለኔ ድብቅ ኃጢአት፤ወይንስ ስለ ልጇ ከባቴ አበሳነት?
ስለምን መናገር እንዳለብኝ እና እንዴት መጸለይ እንዳለብኝ ግራ ሲገባኝ ከነ ጉድፍ ማንነቴ ከነ ርኩሰቴ ከመቅደሱ እገባና
እመ ብርሃንን አያታለሁ። ኃጢአቴ በመላ እፊቴ ይከመርና አንገት እደፋለሁ፤ አቀረቅራለሁ፤ከልቦናዬ ጋ እነታረካለሁ፤
ምን ጊዜ እንደጀመረ ያላወቅኩት የ ዕንባዬ ጅረት ይበልጡኑ ይጨምራል፤ጉንጮቼ ይርሳሉ፤ልቤ ይንሰቀሰቃል፤የምለው ይጠፋኛል፤የምገባበት አጣለሁ፤
አንዳች የምለውን ቢያቀብለኝ ብዬ ቅዱሱ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫን እማጸነዋለሁ፤
ከሱ  ጋር በመሆን  በአርጋኖን እንዲህ እላታለሁ
" የሰራሁትን ኃጢአት ባስበው ልቡናዬ እጅግ ደነገጠብኝ አእምሮ ሳለኝ አለል ዘለል እያልኩ በጽርዓት መኖሬን ባሰብሁት ጊዜ ልቡናዬ እጅግ ደነገጠ
የኃጢአቴን ብዛት በተቆጣጠርሁ ጊዜ ልቡናዬ እጅግ ደነገጠ አንድ ሰዓት ስንኳን አላቋረጥኩም
በሰውና መላእክት ጉባኤ መሐከል ራቁቴን መቆሜን አሰብሁ
በዓይነ ልቡናዬ እመለከት ዘንድ ወዲህና ወዲያ ተመላለስሁ
ምናልባት የሚረዳኝ ባገኝ ከዚህ እጅግ የሚያስፈራው ከሠራሁት ኃጢአት ፍዳ የተነሳ ምናልባት የሚዋሰኝ ባገኝ ብዬ
ነገር ግን በማማለድ እኔን ለማዳን የምትችይውን አንቺን አማላጅ አገኘሁ ዘወትርም ከጎኔ እንዳትርቂ ዐወቅሁ
እንዲህ በፍቅር ያዝሁሽ በጣቶቼ አይደለም
በሃይማኖት ያዝሁሽ በመዳሰስ አይደለም በእደ ሕሊና ያዝሁሽ በእደ ሥጋ አይደለም"  አርጋኖን ዘሠሉስ
👉ስለምን ልናገር ስለኔ አለል ዘለል ማለት፤ ወይንስ ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ትህትና?
👉ስለ ሀዘኔ፤ ወይንስ የደስታ መፍሰሻ ስለሆነችኝ ስለ እመ ብርሃን፤ወይንስ ደስታ ስለሆነኝ መድኃኔዓለም?
ስለምን ልናገር?
❤እመቤቴ ሆይ የምናገረውን አላውቅምና አንደበት ሁኚኝ፤
ርግማን ከቦኛልና በበረከትሽ ጎብኚኝ፤
አንድ ጊዜ እዪኝ...
https://t.me/felege_tibeb




Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram



Показано 20 последних публикаций.