#በመጠን_የማንገልጠው_ፍቅር
#ከዘወረደ_እስከ_ሆሣዕና
#ሕማማት
መድኃኔዓለም አባቴ ሆይ የፍቅርህን ልኬት፣የመውደድህን መዳረሻ፣የርኅራኄህን ጥግ፣የችሮታህን መጠን እኔን ያለ ምክንያት የመቤዠትህን ምሥጢር ዘመኔን በሙሉ ባጤንና ብመራመር እንዳልደርስበት ሳውቅ በድንቅ ሥራህ እደነቃለሁ፤ መውደድህን ተመልክቼ ዕፁብ እላለሁ፤ ፍቅርህን ዐይቼ በዕንባዬ እታጠባለሁ፤ በዝምታ እገረማለሁ በአንደበቴም ተመስገን እልሃለሁ፤ ፍቅሬን አንተ በገለጥክልኝ መጠን መግለጥ እንዳልችል ሳውቅ እጅጉን በራሴ አዝናለሁ፤ አንተ ታላቁን ዕቅድ በሕይወቴ ስታቅድ እኔ በዛሬ እፈትንኃለሁ፤
አንተ መንገዴን ስታቀና እኔ በአቋራጭ እፈትንኃለሁ፤
እንዲያም እያሳዘንኩህ አንተ ግን ለኔ ዋጋ ከፍለህ ከማዳን ቸል አላልክም፤የረከስኩት እኔን ለመቀደስ ከሰማያት ወርደህ፤
መጻጉእ ውስጠቴን ልታክም ከምኩራብ ልቤ ገብተህ፤
ስለ ዳግም መምጣትህ በደብረዘይት ልትነግረኝ፣ገብርኄር(ቸር አገልጋይ) እንድሆን መክሊትን ልትሰጠኝ፤ ዳግም እንደምትወልደኝ በኒቆዲሞስ ነግረኸኝ፣በኃጢኣት ብዛት የታሰርኩትን የተናቅኩትን እኔን ልትፈታ በተናቀች አህያ ጀርባ ሆነህ በእግዚአብሔር ስም የመጣኸው ቡሩክ የእግዚአብሔር ልጅ እግዚአብሔር ሆይ በዚያ የተከተለህ ሕዝብ ሆሣዕና እያለ ልብሱን አውልቆ እንዳነጠፈልህ እኔም ልቤን ከአምላክነትህ እንዳነጥፍ ርዳኝ፤ ጠዋት አክብሬህ ከሰዓት አንተን ስለመስቀል ስለኃጢኣት ከመምከር ጠብቀኝ፤ለቤዛነት የመጣኸው ሆሣዕና ክርስቶስ ሆይ ስለኔ የከፈልከው ዋጋ እጅግ የከበደ ነውና ተመስገን።
ጌታ ሆይ ስለኔ የከፈልከውን ዋጋ እንዳልረሳ ውሳጣዊ ዐይኖቼን አብራልኝ አሜን
ተመስገን
እንኳን አደረሳችሁ
https://t.me/felege_tibeb