................
ዛሬም እንደትናትና
ናፈቅሺኝ ከንደገና
ተገዝ የበዛበት የቀናው ጎዳና
ውብ መልክሽን ሳለ
ከመንገዱ መሀል ላመል የበቀለው
ዘንባባና ጥዱ ሳቅሽን የመሰለው
ፈገግታሽን ኳለ!
የለማኝ የተሽከርካሪው የማቲው
ጫጫታ እራቀኝ
ከመንገድ መሀል ገትሮ
በህላዌ አመጠቀኝ
አካልሽ ከኔ ባያርፍም፤ጥላሽን ዳብሼ ጸናሁ
ዳናሽ ከከተበበት፤በጽናት ልቤን መራሁ
ደረስኩብሽ ስል ስትርቂኝ
ቀሚሽን ያዝኩ ስል ስትነጥቂኝ
ማፍቀር ሲያደናቅፈኝ
ተስፈ ሆኖኝ እንቅፋት
በበቀል እንዲሽርልኝ
የነፍሴን ስብር እጥፈት
ትናንት እንዳልነበረ
መዳፍሽ እንዳልዳበሰው
አላውቅም በሚል ቃል ክጄ
ፍቅርሽን እንዳላረክሰው
ትዝታሽ መግል ሆነብኝ ናፍቆትሽ የጊዜ ቁስል
ጎዳናው ይፈካልኛል ጫጫታው መልክሽን ሲስል
መከተል
መሄድ
መጓዝ ነው
ጥላዋን ያፈቀረ ሰው
መንገዱ የቀናለትን ልመና እንዳይመልሰው
ቃላት አይከጅሉትም ገላ ያልበቃውን ሰው
ጠልቼሽ እንደዲድንልኝ
የፍቅርሽ የነፍሴ ቁስል
ሸሽቼሽ እንዲሰምርልኝ
ህይወቴ ህልም እንዲመስል
ሀሞቴን አምርሬ
ሀጥያትሽን ደርድሬ
እረሳሁሽ ብዬ መንፈሴን ሳጽናና
ትናፍቂኝ ጀመር ዛሬም እንደገና
By
@mad12titan@getem@getem@getem