............
በስሜት ተናንቀን
በስጋ ተዋውቀን
ገላሽን ስሞቀው
ወዝሽን ስጠምቀው
ጠረንሽ ሰንፍጦኝ
ጥፍርሽ ላመል ልጦኝ
የስሜት ጣረ ሞት
ውስጥሽን አፍሞት
ፍቅርን ስንሰራ
.....
........
............
ውል ከሌለው ስፍራ
ደከም ስትይ አርፈሽ
ክንዴን ተደግፈሽ
ፍቅርን ስታወጊኝ
በአሽሙር ስትወጊኝ
በህጻን ፈገግታ
ያዋቂ ጨዋታ
ብ........ዙ ስናወጋ
....
......
.........
እንደ ድንገት ነጋ
አይኔን አጨፍግጌ
ገላሽን ፈልጌ
ላቅፈው ብንጠራራ
ላወራሽ ብጠራ
ህልም ነው የለሽም
ያወጋሁሽ ሁሉ
ያደረግነው ሁሉ
ፍሬው አልደረሰሽም ?
By @Mad12titan
@getem
@getem
@getem
በስሜት ተናንቀን
በስጋ ተዋውቀን
ገላሽን ስሞቀው
ወዝሽን ስጠምቀው
ጠረንሽ ሰንፍጦኝ
ጥፍርሽ ላመል ልጦኝ
የስሜት ጣረ ሞት
ውስጥሽን አፍሞት
ፍቅርን ስንሰራ
.....
........
............
ውል ከሌለው ስፍራ
ደከም ስትይ አርፈሽ
ክንዴን ተደግፈሽ
ፍቅርን ስታወጊኝ
በአሽሙር ስትወጊኝ
በህጻን ፈገግታ
ያዋቂ ጨዋታ
ብ........ዙ ስናወጋ
....
......
.........
እንደ ድንገት ነጋ
አይኔን አጨፍግጌ
ገላሽን ፈልጌ
ላቅፈው ብንጠራራ
ላወራሽ ብጠራ
ህልም ነው የለሽም
ያወጋሁሽ ሁሉ
ያደረግነው ሁሉ
ፍሬው አልደረሰሽም ?
By @Mad12titan
@getem
@getem
@getem