“ በአጠቃላይ አቃቢ ህግ በእኔ ላይ መስርቶ ባቀረበው ክስ ላይ የተገለጸውን ወንጀል አልፈጸምኩም” - አቶ ክርስቲያን ታደለ
እነአቶ ክርስቲያን ታደለ ዛሬ ችሎት ቀርበው የእምነት ክህደት ቃል መስጠታቸውን ጉዳዩን ከሚከታተሉ ሰዎችና ቃላቸውን ካቀረበበት ሰነድ መረዳት ትችሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው አቶ ክርስቲያን የእምነት ክህደት ቃል የሰጡበት ሰነድ፣ “በአጠቃላይ አቃቢ ህግ በእኔ ላይ መስርቶ ባቀረበው ክስ ላይ የተገለጸውን ወንጀል አልፈጸምኩም። ጥፋተኛም አይደለሁም” ይላል።
አቶ ክርስቲያን በሰጡት የእምነት ክህደት ቃል ምን አሉ?
“ለ550 ቀናትም በግፍና ጭካኔ እገታ ውስጥ የምገኘው ለአንዲት ደቂቃ እንኳን በጥፋተኝነት የሚያስቀጣ አንዳችም የወንጀል ድርጊት የሚያቋቁም የህግ መተላለፍ ስለፈጸምኩ አይደለም። የአማራ ሕዝብ የሚያነሳቸውን የህልውና ጥያቄዎች በይፋ በማቅረቤ፣ በሕዝቤ የሚደርሰውን ግፍ፣ በደል በማስረጃ በመሞገቴ፣ የገዢውን ፓርቲ አፈናና የመንግስት አሰራሮችንና አመራሮችን ብልሹነትና ዘረፋ በመታገሌ ነው ” ብለዋል።
“ ተደጋጋሚ የአመራር ብልሹነት ባሳዩ አካላትም የወንጀልና የፍትሃብሔር ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ ክስ እንዲመሰረት ፍትህ ሚኒስቴር አዝዥለው ” የሚሉና ሌሎች ድርጊቶችን በአደባባይ እንደታገሉ ገልጸዋል።
“ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ሌሎች የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች በአሰራራቸው የፋይናንስ ገልጸኝነትና ህጋዊነት እንዲከተሉና እንዲረጋገጡ እንዲሁም ኦዲት ለመደረግ ፈቃደኝነታቸውን እንዲያረጋግጡ ጠይቄከለሁ ” ነው ያሉት።
እነዚህን ጥያቄዎች እንዳልጠይቅ አንዳንድ አመራሮች ለማግባባት እንደሞከሩ ገልጸው፣ “ አንዳንዶቹም ሊገድሉኝ፣ ሊያስሩኝና አንዳች ነገር ሊያደርሱብኝ እንደሚችሉ ጭምር ነግረውኛል፤ መልዕክትም አድርሰውኛል ” ብለዋል።
“ አንዳች ወንጀል አልፈጸምኩም ” ያሉት ክርስቲያን፣ “ ይህን በተመለከተ ከክሱ ይዘት ብቻ ሳይሆን በራሴ መንገድ ይህን ክስ ተዘጋጅቶ እንዲቀርብብኝ ካደረገው አካል ዘንድም አረጋግጫለሁ ” ሲሉ አስረድተዋል።
“ እኔ አማራ የሆንኩት አማራ ሆኘ ስለተወለድኩ ነው። የከማራ ብሔርተኝነት አቀንቃኝ የሆንኩትም ፈቅጄ፣ መርጨና ወድጄ ነው። በየትኛውም ቦታና ሁኔታ ለአማራነቴ ጥብቅና መቆምም ተፈጥሯዊ ግዴታዬ ነው ” ብለዋል።
“ አማራዊ እሴቶታችን ለኛ ቅዱስ ነው ” ብለው፣ “ ይሁንና አቃቢ ህግ ባቀረበው የፓለቲካ ውንጀላ ሰነድ ላይ፣ ‘አማራ ርስቱን ተቀምቷል፤ አገሪቱ በአማራ እሴት መመራት አለባት’ የሚል የርዕዮተዓለማዊ አቋም መያዛችን ክስ ሆኖ ቀርቧል” ብለዋል።
“ ይህ የአቃቢ ህግ ክስ ግን መንግስት ከአማራና ከአማራነት የጸዳች ኢትዮጵያ ነው ወይ የሚፈልገው ? የሚል ሙግት ያስነሳል። ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ከአማራና ከአማራነት በስተቀር እንዲሆኑ የሚደነግግ ህግስ አለ ወይ? ” ሲሉ ጠይቀዋል።
በሌላ በኩል “ በአቃቢ ህግ ክስ ላይ ‘ቋሪትና ደጋ ዳሞት ላሉ የሽብር ቡድን አስተባባዎች በስልክ ሐምሌ 25/2015 ዓ/ም በመደወል መከላከያን ማጥቃት ህገ መንግስታዊ መብት መሆኑን በማሳወቅ እንዲመቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል’ ” ማለቱን ጠቅሰል።
“ አቃቢ ህግ ለዚህ ክስ አስረጅ የሆነ አንዳችም ማስረጃ አላቀረበም ” ብለዋል።
(ሙሉ የእምነት ቃላቸውን የሰጡበት ሰነድ ከላይ ተያይዟል) @tikvahethiopia