🟢ኢስላማዊ ፎቶግራፍ መደድ /islamic photograpy


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана



Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


አንዳንዱን ዒልም ይቸረውና ነቢን ማሞገኣ ይነፍገዋል- በእርግጥ አላወቀም። መደሁን የወፈቀው ተውፊቁን አወቀው- ቢያንስም አተለቀው ወዳጁ ነውና ሙሐመዲል ሃዴ ኑሩል ዐለሚና።


አሏሁመ ሶሊ አላ ሰይዲና
አሏሁመ ሶሊ አላ ሰይዲና
ሙሐመዲል ሃዴ ኑሪል ዐለሚና
💚💜
ልጥራሁ ከዳና መስዬ ተደህና
አርሂብ ልትሉኝ ና ኸይሩል ዐለሚና ሙሐመዲል ሃዴ ኑሪል ዐለሚና
💚💜
ሶላት በስዎም አህሉ በሷህብም ኩመሉ
ሳይሆን በከፊሉ በሙላውም ጀግና ሙሐመዲል ሃዴ ኑሪል ዐለሚና
💚💜
መድሁን ያጣፈጡ በመደድ ሰመጡ
አምሳሉን እያጡ ሰርኩን ዋለሉና ሙሐመዲል ሃዴ ኑሪል ዐለሚና
💚💜
የጀነት ወራሽ ነው ውዱ ያባዘነው
መድሁ ያባከነው በአናም በዳና ሙሐመዲል ሃዴ ኑሪል ዐለሚና
💚💜
አለ ጎበዝ አልፎ የከተበ ጎርፎ
ያልጠገበው ጥፎ የጫሌው መውላና ሙሐመዲል ሃዴ ኑሪል ዐለሚና
💚💜
እንዳመዴው ባካኝ የኮረሜው ሰካኝ
ነፍሃቱ በነካኝ የዋሪዱ ጣና ሙሐመዲል ሃዴ ኑሪል ዐለሚና
💚💜
ገባ ተንደርድሮ መች ቀረ ሸምሮ
ጨረሰው ዘምሮ የዱንያን ጎዳና ሙሐመዲል ሃዴ ኑሪል ዐለሚና
💚💜
ያ ሷሂበል ቡራቅ ቡሲይሪና ወራቅ
ጀማልሁን ባውራቅ ሲያፈሱት ኖሩና ሙሐመዲል ሃዴ ኑሪል ዐለሚና
💚💜
ኺታማቸው አምሮ ሸረፉን ጨማምሮ
ከውኑ ላይ ተነክሮ የነዝማቸው ፋና ሙሐመዲል ሃዴ ኑሪል ዐለሚና
💚💜

ሲባል ሰማን ወዷል ወዳጁን አጋዷል
ይኸው እጄም ሰዷል ከወስፉ ቀጠና ሙሐመዲል ሃዴ ኑሪል ዐለሚና
💚💜
ሐበሽ ስንቱ አብዷል ሆዱን ዘልቆት ነዷል
ጅስሙ ተመርዷል ፊትኩን አጣውና ሙሐመዲል ሃዴ ኑሪል ዐለሚና
💚💜
ለኛስ ምነው ልከው ጦይፉን አፈትልከው
ስንተሓረከው ሌቱን ባልተኛና ሙሐመዲል ሃዴ ኑሪል ዐለሚና
💚💜
ዚክሩ ሆኖን ቀለብ ለቀልብና ቃለብ
ፈትራ ባንል ሸለብ በጦይበቷ ቃና ሙሐመዲል ሃዴ ኑሪል ዐለሚና
💚💜
ይልካል የኑር ጀት ከድልበቱ ማጀት
ከቶ አያውቅም ማርጀት ከውናቱን'ሲያቀና ሙሐመዲል ሃዴ ኑሪል ዐለሚና
💚💜
አውሬው ሁላ ሳቀ ካሂን ፈርቶ ራቀ
ኢብሊስ ተንፏቀቀ ስትወልደው አሚና ሙሐመዲል ሃዴ ኑሪል ዐለሚና
💚💜
በረጀብ ጁምዐ ለይል ተረግዞ የኑር ሰይል
አልፎ'አያሌውን ጀይል ባሚነት ላይ ጠና ሙሐመዲል ሃዴ ኑሪል ዐለሚና
💚💜
ተኩላው ጅብ የጫካው ቢሻራው ያውካካው
ደስታው አፈትልካው ምዕራቡን ተቃና ሙሐመዲል ሃዴ ኑሪል ዐለሚና
💚💜
እልል በይ ካኢናት አልፏል ያሳር ቀናት
ሹክር ሁላ ላሚናት ወላጁህ ናትና ሙሐመዲል ሃዴ ኑሪል ዐለሚና
💚💜
ደግሞም ለአብደሏህ ያ መዕዲነል ፈላህ
ዘይኑ ሪጃሊላህ የወንዶቹ ጀግና ሙሐመዲል ሃዴ ኑሪል ዐለሚና
💜💚
ሓሊመቷም ትመር የሰዕዲቷ ቀመር
ያንን ወጅሃል አህመር አቅፋ ስታጽናና ሙሐመዲል ሃዴ ኑሪል ዐለሚና
💜💚
ያጸናል እንጂማ ጉዱን ብታውቅማ
የኑቡዋው ሸማ የተውሂድ በገና

جاء بالبشارات لأهل العبارات
فاتق المسرات لصب تغنى ሙሐመዲል ሃዴ ኑሪል ዐለሚና
💜💚
قد أفرح الوحوش وجهكم البشوس
وقتكم المنقوش بكمال الهناء
💜💚
هبت من القبا روائح الصبا
نعم تلك الربى تذهب بالعناء
💜💚
كريم الأيادي مجيب المنادي
يا ليت إعراضي قولوا'التجئ بنا
💜💚
قاسم الدرجات حدائق الجنات
سقف بيت المنات ملجأ الفطنا
💜💚
هذا الطفل يقول ما دريت النقول
بالأوهام أقول ارأف سيدنا
💜💚
ما اختلط الأحباب يعيش كالذئاب
لامسا كاذباب كل سخف دنا
💜💚
بماء التوبة طهر سريرتي
بطيوب النعت كي أبلغ المنى
💜💚
ألم تكن غدا شافع للفسدى
أنت جود بدى وحاط أزمانا
💜
حبذا الطبيب منه كل طابو
بذكره غابو عن العلمينا
💜💚
معنى المعية من ذاتك آت
جدول فرات معاني القرأنا
💜💚
في الطيبة الغراء وفيحاء العذراء
كم قصص جرى وكم فات عنا ሙሐመዲል ሃዴ ኑሪል ዐለሚና
💜💚
خدام المجتبى بوابات الطيبة
هم جيران قباء بالحس والمعنى
💜💚
وا حسرة زادت من وقت أتلفت
بالجهد ما فازت نفسي هل لي عونا
💜💚
يا ربيع الجدوب مصقلة القلوب
رجاك ذا المعيوب ببريق السنا
💜💚
ظفر من دنا جنابه الأهنى
خسر من جنى ثمار الضالينا ሙሐመዲል ሃዴ ኑሪል ዐለሚና
💜💚
عطوف شفوق بعده حراق
إليه تساق ساق السائرينا
💜💚
وصلاة الباري الهادي الغفار
على طه النور صومع الأمناء
💚💜
وسلام السلام على ذات السلام
وآله الأعلام وصحب الأعوانا
💜💚
لحقا بالأتباع فرسان الخشع
فروا من الشبع وأخلصو الإناء
💜💚
يا عمود التوحيد يا مركب التفريد
في قصرك المشيد بالود أكرمنا
💜💚
አሏሁመ ሶሊ አላ ሰይዲና
አሏሁመ ሶሊ አላ ሰይዲና
ሙሐመዲል ሃዴ ኑሪል ዐለሚና

ረቢዕ 1 ዳና
ሰላም ይድረሶት ሆዴ




የቲኬት ብር ተመላሽ ስለማድረግ
•••••••••••••••••••••••
ለመስከረም 15/2015 ዓ/ል "በነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ፍቅር እና በዑለሞቻችን መንገድ ሕያው ነን" በሚል መሪ ቃል 3ኛ ዙር ታላቅ ሀገር አቀፍ መውሊድ ለማዘጋጀት አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታዎች አሟልተን ከከንቲባ ፅህፈት ቤት በደብዳቤ ቁጥር አአከፅ17/30.4/89 ህጋዊ ፍቃድ ከተሰጠን በኋላ፣ ከህገ ወጡ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት የተፃፈ ደብዳቤን መነሻ በማድረግ፣ የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ በመስከረም 12/2015 ፕሮግራሙ የፀጥታ ችግር ያጋጥመዋል በሚል ፈቃዱን መሰረዙ ይታወቃል።

ማህበራችንም ህጋዊ አካሄዶችን ተከትሎ ከጨረሰ በኋላ ከአዲስ ፓርክ/ሚሊኒየም አዳራሽ አስተዳደር ጋር እንዲሁም ከሌሎች ባለድርሻ አካላቶች ጋር የውል ስምምነት በመግባት አስፈላጊውን ክፍያ በመፈፀም ለማህበረሰባችን በማሳወቅ የቲኬት ሺያጭ ከጀመርን በኋላ ታላላቅ የሀገራችን ዓሊሞች/የእምነቱ አስተምህሮ አዋቂዎች ጠርተን ወደ ከተማችን ከገቡ በኋላ በቀን መስከረም 12/2015 ከአዲስ አበባ አስተዳደር ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ከሰዓት በኋላ በተደረገልን ጥሪ መሰረት ፕሮግራሙን ማካሄድ እንደማንችል በቃል የተነገረን ሲሆን ክልከላው በደብዳቤ እንዲገለፅልን እና ህዝባችንን እንድናሳምን አጥበቀን የጠየቅን ቢሆንም ክልከላው ከቃል በዘለለ በደብዳቤ ሳይገለፅን አልፏል።

በወቅቱ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ፅህፈት ቤት ኃላፊ :_ ጊዜው የደመራ እና የእሬቻ በአል የሚከበርበት በመሆኑ የፀጥታ ሃይል ልንመድብላቹህ አንችልም። ከመስከረም በኋላ ባለው ጊዜ በምትፈልጉት ቀን ጠይቁን እንተባበራችኋለን ብለው ቃል ገብተውልን የነበረ ቢሆንም ቀኑ ካለፈ በኋላ ቃሉ በተግባር ሊፈፀም አልቻለም። ለአዲስ አበባ ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ለጥቅምት 6፣ 13 እና 27 መውሊዱ እንዲፈቀድልን አበክረን በየእለቱ ደጅ እየጠናን የጠየቅን ቢሆንም ከበላይ ኃላፊዎች ጋር ተነጋግረን እናሳውቃችኋለን እያሉ ለጥቅምት 6 እና 13 ያቀረብነውን ጥያቄ ምላሽ ሳይሰጡን ወደ ጥቅምት 27 ለማዞር ተገደድን። ከጥቅምት 15 በኋላ ባለው ጊዜ በየትኛውም ቀን አንድ ቀን እንፈቅድላችኋለን ብለው የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ቃል የገቡልን ቢሆንም ደብዳቤ አስገብተን ለጥቅምት 27 እንዲፈቅዱልን ስንጠይቅ ግን ቃላቸውን አጥፈው መልሰው እንደማይፈቅዱ ገለፁልን።

የመስከረም 15 መውሊድ ሲሰርዙ መስቀልና እሬቻን አሳበው የፀጥታ ችግር ስላለ ነው ብለው ሲናገሩ የነበሩ የመንግስት ኃላፊዎች መስከረም 15 ካለፈ በኋላ ግን ጉዳዩ ከፀጥታ ችግር ጋር የተገናኘው ህገወጡ የአዲስ አበባ የወሃቢያ መጅሊስ በፃፈው ደብዳቤ ምክንያት መሆኑን እና ከአዲስ አበባ የወሃቢያ መጅሊስ ደብዳቤ እንድናመጣ ከወሃቢያ መጅሊስ ጋር ተባብረን እንድንሰራ በግልፅ መናገር ጀመሩ። ማህበራችን ቀድሞውንም ቢሆን የጸጥታ ችግር የሚባለው ለሽፋን እንጂ ዋናው ሰበብ ለወሀቢያ መጅሊስ እውቅና እንድንሰጥ ለማስገደድ እንደነበር ግዛቤ ወስዶ ነበር።

የሚሊኒየሙ አዳራሽ መውሊድ ከጥቅምት 27 በኋላ እንደማይሳካ ስናውቅ ቲኬት ለገዙ 2ሺ ለሚደርሱ ሰዎች የአዳራሽ ፕሮግራም ለማዘጋጀት አስበን የነበረ ቢሆንም በአንዳንድ ምክንያቶች እስካሁን ማሳካት ባለመቻሉ በቲኬት ሽያጭ የተሰበሰበው ገንዘብ ወደ ህዝብ ተመላሽ መደረግ ስላለበት ይህን ፅሁፍ መልቀቅ አስገዳጅ ሆኗል። በመሆኑም ለመስከረም 15 መውሊድ ቲኬት የገዛችሁ ሙሂቦች ከነገ ማክሰኞ ህዳር 13/2015 ጀምሮ ፒያሳ አትክልት ተራ ከሊፋ ህንፃ አጠገብ የሚገኘው ሴካ ህንፃ 10ኛ ፎቅ የማህበራችን ቢሮ በመምጣት ቲኬት የገዛችሁበትን ብር ተመላሽ እንድትወስዱ እንጠይቃለን። ተመላሽ ለመጠየቅ ሲመጡ የገዙትን ቲኬት ይዘውልን ይምጡ።

ይህ ፕሮግራም እንዲሳካ ለማድረግ በጊዜ በገንዘብ በእውቀትና በጉልበታችሁ ላገዛችሁን እንዲሁም መውሊዱን ለመታደም በጉጉት ስትጠብቁ ለነበራችሁ ለመላው ሙስሊም ማህበረሰብ በተፈጠረው ጊዜያዊ ጫና መውሊዱ ሊካሄድ ባለመቻሉ አጅግ በጣም በትልቁ ይቅርታ እንጠይቃለን።


ህዳር 4 ከ 3:00 ጀምሮ በወረዳ 1 ወጣት ማዕከል  አዳራሽ ለመጀመሪያ ዙር በቦሌ ጃዕፈር የሀድራ ወጣቶች የተዘጋጀ በአይነቱ ለየት ያለ የመውሊድ ድግስ አለ  የሰይዳችን (ሰ ዐ ወ) ወዳጅ የሆናችሁ ሁላችሁንም ጠርተናቹሀል በፕሮግራሙ ትላልቅ ዑለማዎች ማዲሆች ሙነሺዶች ኡስታዞች ታላላቅ እናቶች ይገኛሉ የተለያዩ ፕሮግራሞችን ይዘን እንጠብቃቹሀለን ።
የመግቢያ 100 ብር
ለእናቶቻችን መግቢያ 50 ብር
ቲኬቱን ከአከባቢው ወጣቶች ማግኘት ይቻላል።
0939912624
0930595630


ህዳር 4 ከ 3:00 ጀምሮ በወረዳ 1 ወጣት ማዕከል  አዳራሽ ለመጀመሪያ ዙር በቦሌ ጃዕፈር የሀድራ ወጣቶች የተዘጋጀ በአይነቱ ለየት ያለ የመውሊድ ድግስ አለ  የሰይዳችን (ሰ ዐ ወ) ወዳጅ የሆናችሁ ሁላችሁንም ጠርተናቹሀል በፕሮግራሙ ትላልቅ ዑለማዎች ማዲሆች ሙነሺዶች ኡስታዞች ታላላቅ እናቶች ይገኛሉ የተለያዩ ፕሮግራሞችን ይዘን እንጠብቃቹሀለን ።
የመግቢያ 100 ብር
ለእናቶቻችን መግቢያ 50 ብር
ቲኬቱን ከአከባቢው ወጣቶች ማግኘት ይቻላል።
0939912624
0930595630


ህዳር 4 ከ 3:00 ጀምሮ በወረዳ 1 ወጣት ማዕከል  አዳራሽ ለመጀመሪያ ዙር በቦሌ ጃዕፈር የሀድራ ወጣቶች የተዘጋጀ በአይነቱ ለየት ያለ የመውሊድ ድግስ አለ  የሰይዳችን (ሰ ዐ ወ) ወዳጅ የሆናችሁ ሁላችሁንም ጠርተናቹሀል በፕሮግራሙ ትላልቅ ዑለማዎች ማዲሆች ሙነሺዶች ኡስታዞች ታላላቅ እናቶች ይገኛሉ የተለያዩ ፕሮግራሞችን ይዘን እንጠብቃቹሀለን ።
የመግቢያ 100 ብር
ለእናቶቻችን መግቢያ 50 ብር
ቲኬቱን ከአከባቢው ወጣቶች ማግኘት ይቻላል።
0939912624
0930595630










ሚሊኒየም መውሊድ ከምናያቸው ኩረማዎች ኢንሻአላህ 5 ቀናት ብቻ


ቀድመው ቲኬት ለወሰዱ የተጋበዙት 😂😋


የሚሊኒየም አዳራሹ መውሊድ 9 ቀናት ብቻ ነው የቀሩት ቲኬት በጊዜ በእጃቹ ብታስገቡ ኸይር ነው ለማለት ያህል....

0930595630




ታጥቀህ ተነስ ሚኒልየም ሊደገም ነው


የአዲስአበባ ሙስሊም ወጣቶች ማህበር
ተዘጋጁ እያለን ነው ያ አህባብ ዝግጁ ናችሁ???


የዘንድሮ መውሊድ ቲሸርት ሳትገዙ ሊያይቅ ነው ቶሎ ደውሉ
#ዋጋው 350

0930595630
0932508473




የመውሊድ ቲሸርት በጥራት
ዋጋ 350
0930595630
0932508473


ያረቢ ሁጃጆችን በሰላም ሄደው ተጠቅመው ሚመጡ አርግልን እኛንም ወፍቀን አሚን🙏

Показано 20 последних публикаций.

126

подписчиков
Статистика канала