Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
የኢኽዋንና የአሕባሽ ውዝግብ!!
~~~~~~~~~~~
ሰሞኑን መጅሊስን አስመልክቶ በኢኽዋንና በአሕባሽ ሰዎች መካከል የተከሰተውን ውዝግብ ታዝበዋል? ምን አስተዋሉ? ያ ሁሉ ጮቤ የረገጡበት ‘አንድነት’ ከአህያ ቆዳ የተሰራ ቤት ሲሆን ተመለከቱ አይደል? "ከአህያ ቆዳ የተሰራ ቤት ይበታተናል ጅብ የጮኸ’ለት!!" መሰረታዊ መርሆዎችን በመጨፍለቅ የፈፀሙት ያለ አቻ ጋብቻ ይሄው በውሃ ቀጠነ እየደፈረሰ ነው። ምክንያቱም የተቋም ሽሚያና የጠቅላዩን የመደመር ፍልስፍና እውን ለማድረግ ሲሉ ነበር እጅ ለእጅ የተያያዙት። መሰረታዊ ልዩነቶችን ገሸሽ በማድረግ በእግር ኳስ እየመሰሉ ተራ ቁርቁስ አድርገው ሲያቀርቡት እያስተዋልን ነበር። ይሄው ቀኑን ጠብቆ ፈነዳ። ውሸት እድሜው አጭር ነው። ከባባድ ልዩነቶች ባሉበት "በጥቃቅን ነገሮች ልንለያይ አይገባም" እያሉ ባደባባይ ሲቀጥፉ ነበር። እንዲህ ከሚያለባበሱ እቅጭ እቅጩን ተነጋግረው ግልፅ ውይይት በማድረግ ልዩነቶችን ቢቻል መፍታት፣ ካልሆነ ማጥበብ ነበር የሚገባው። ግና ሲያለባብሱ ነው የኖሩት። "አለባብሰው ቢያርሱ ባ’ረም ይመለሱ" ነው ነገሩ።
አሁንም ችግራቸውን ሳይቀርፉ "ታርቀናል" እያሉ ነው። በርግጠኝነት ዳግም ይጣላሉ። ለምን? የህብረቱ መሰረት ‘ሊላህ’ አይደለም። ይልቁንም ‘ሊአብይ’ ነበር። ለጠቅላዩ መደመር ፍልስፍና። በቃ! ከዚያ ካለፈ መጅሊሱን መቀራመት ነው አላማው። ከኢኽላስና ከኢስላሕ የተኳረፈ ቅንጅት የኋላ ኋላ መናቆርና መባላት ነው ትርፉ። ከዚህ ጋር በተያያዘ ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላ፞ህ እንዲህ ብለዋል: –
"والناس إذا تعاونوا على الإثم والعدوان أبغض بعضهم بعضًا، وإن كانوا فعلوه بتراضيهم ...
فالمُخَالّة إذا كانت على غير مصلحة الاثنين؛ كانت عاقبتها عدواة، وإنما تكون على مصلحتهما إذا كانت فى ذات الله، فكل منهما وإن بذل للآخر إعانة على ما يطلبه واستعان به بإذنه فيما يطلبه، فهذا التراضى لا اعتبار به، بل يعود تباغضًا وتعاديا وتلاعنًا، وكل منهما يقول للآخر : لولا أنت ما فعلت أنا وحدى هذا، فَهَلاكِى كان منى ومنك ... "
“ሰዎች በወንጀልና በበደል ላይ ከተጋገዙ ከፊላቸው ከፊላቸውን ይጠላል። ተስማምተው ቢፈፅሙት እንኳን ማለት ነው።… ስለዚህ ወዳጅነት ለሁለቱም በሚበጅ መልኩ ካልሆነ ፍፃሜው መጠላላት ነው የሚሆነው። ለሁለቱም ጠቃሚ የሚሆነው ደግሞ ለአላህ ዛት ታስቦ ሲፈፀም ነው።
ያለበለዚያ ሁሉም ቢሆን አንዱ ለሌላው በሚያስፈልገው ጉዳይ ላይ ድጋፍ ቢያደርግልትና በፍቃዱ መሰረት በሚያስፈልገው ጉዳይ ላይ ቢታገዝበት እንኳን ይሄ የእርስበርስ ስምምነት ዋጋ የለውም። ይልቁንም ወደ መጠላላት፣ መበዳደልና መረጋገም ይቀየራል። እያንዳንዱ ለሌላው ‘አንተ ባትኖር ኖሮ እኔ ብቻየን ይህን አላደርግም ነበር። የጠፋሁት በኔ ብቻ ሳይሆን ባንተም ሰበብ ነው…’ ይለዋል።"
[መጅሙዑል ፈታዋ: 15/129]
•
ሸይኹል ኢስላምን አላህ ይማራቸው። ምንኛ የሚደንቅ ሐቅ ተናገሩ?! ይሄው የተናገሩትን ነገር በገሃድ አየነው። ነገም በአላህ ፈቃድ እንደምናየው እርግጠኞች ነን።
መፍትሄው ሌላው ቢቀር ቢያንስ ለራስ እውነተኛ መሆን ነው። ልዩነት በተጨባጭ አለ። ያለ ምንም መሸዋወድ ልዩነትን አምኖ መነጋገር። ከተቻለ መፍታት። ካልሆነ በሐቅ መለያየት! እውነት ለመናገር በሐሰት ጊዜያዊ ህብረት ከመፍጠር በእውነት መለያየት ይሻል ነበር። ትላንት ጭራቅ አድርገን ስንስለው የነበረውን አሕባሽ (እውነትም ጭራቅ ነው) ዛሬ "በጥቃቅን ነገር ነው የምንለያየው" ማለት በዲንም፣ በህዝብም ላይ ግፍ መፈፀም ነው። እንደኔ የድራማው ተዋናዮች እውነቱን ይነግሩናል፣ ለሐቅ ቁርጠኛ ይሆናሉ፣ መራራውን እውነት ይጋፈጣሉ ብየ አልገምትም። ስለዚህ ወገኔ ሆይ! የመፍትሄው ቁልፍ ባንተ እጅ ነው። በነዚህ ቀልደኞች ካርጎ እንደ በግ ታጭቀህ አትጓዝ። ከባቡሩ ውረድ። ሲጣሉ "አሕባሽ አይሁድ ነው" ሲታረቁ "ልዩነታችን ጥቃቅን ነው፣ አንድ ነን" እያሉ ዲን ከሚያጨማልቁ ሃላፊነት የማይሰማቸው፣ አኺራን ሚዛን ያላደረጉ አካላት ተከትለህ ዐቂዳህን አታጨማልቅ። ነገ ከአላህ ፊት የምትቆመው ብቻህን እንጂ እነሱ አይቆሙልህም። የምትጠየቀው ብቻህን እንጂ እነሱ አይጠየቁልህም።
https://t.me/IbnuMunewor