"የማዕድን ሀብት ልማት ለሀገራችን የኢኮኖሚ ግንባታ!" በሚል መሪ ቃል ከአጋር አካላት ጋር የውይይት
መድረክ ተካሄደ፡፡
የካቲት 20/2017 ዓ፣ም፤እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የምህድስና እና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ ከማዕድን ልማት ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ጋር ማዕድን
ልማት ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ አካሂዷል፡፡
በውይይቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል
ፕሬዝዳንት እና የፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ተወካይ ክንዴ ብርሃን(ዶ/ር) ዪኒቨርሲቲው የማዕድን ሀብት ዙሪያ
ለመስራት የማዕድን ዘርፍን ለማሳደግ እና በቴክኖሎጂ ለመደገፍ የማዕድንን ትምህርት ክፍል በመክፈት የተማረ የሰው ሀይል በማፍራት፣ ጥናት እና ምርምር በማድረግ፣ ስልጠና በመስጠት እና ማህበረሰቡ
ከዚህ ዘርፍ ተጠቃሚ እንዲሆን እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡
ዶ/ር ክንዴ አያይዘውም የዚህ መድረክ ዓላማ የኒቨርሲቲው ያለውን የተማረ የሰው ሀይል ተጠቅሞ በሀገራችን፣ በክልላችን እና በብሄረሰብ አስተዳደሩ የሚገኙ ጠቃሚ የማዕድን ሀብት ማውጣት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መነጋገር፣ መወያየት እና አቅምን መገንባት አስፈላጊ በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡ ውይይቱ
ያሉንን ሀብት ለመለየት፣ እንዴት መጠቀም እንደሚቻል፣ ለሚያጋጥሙ ችግሮች መፍትሄዎችን ለመፈለግ እና በቀጣይ በማዕድን ልማት ዙሪያ በጋራ መስራት ስለሚቻልበት ሁኔታም ለመምከር የሚያስችል መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል፡፡
https://www.facebook.com/100069178971700/posts/pfbid0cLjmbK8Kf2CRsFPqf7Fj9oSdMKJwEubgiB8sc1cC7NQmGUV1DsBrk3Hnu2HuqNrFl/?app=fbl