የአእላፋት ዝማሬ | Melody of Myriads


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Религия


እንዳልዘምር የሚከለክለኝ ምንድን ነው?

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Религия
Статистика
Фильтр публикаций


በኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ አዘጋጅነት በአዲስ አበባ እና በድሬዳዋ ከተማ በተከናወነው የአእላፋት ዝማሬ ላይ ቀርቦ የነበረው ''አንድ የኢትዮጵያ ሰው'' የተሰኘው የዕጣ ቲኬት ነገ በሰንበተ ክርስቲያን በJanderebaw media YouTube channel በቀጥታ ስርጭት የዕጣ ማውጣት መርሐግብር ይከናወናል።
ነገ ከቀኑ 10:00 ሰዓት ላይ ይጠብቁን።






ይህን ምስል ስቶሪ እና ፕሮፋይል በማድረግ ያጋሩ።

የብዙኃን ደም ልገሳ መርሐግብር   

ጥር 17 እና 18 ፡ በቦሌ መድኃኔዓለም
ከጠዋቱ 3:30 ጀምሮ

ባዮ ላይ ባለው ሊንክ ይመዝገቡ።


በኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ የተዘጋጀ የደም ልገሳ መርሐግብር

በእለቱ ደም በመለገስ በቋሚነት አባል መሆን ከፈለጉ ፎረሙን በመሙላት ይመዝገቡ።
👇👇👇
https://forms.gle/3dK8tm6EKbZHNADy9

"ከበጎ ነገር ጋር ተባበሩ " ሮሜ 12:9


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
- ሉቃ 3:21

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን ።




Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
የብዙኃን ጋብቻ | ዘጋቢ ፊልም






ነገ ማታ በጃንደረባው ሚድያ የዩቲዩብ ገጽ ይጠብቁን ።


በድሬዳዋ የመጀመሪያው የአእላፋት ዝማሬ ተካሔደ

| ጃንደረባው ሚዲያ | ታኅሣሥ 28 2017 ዓ.ም.|
ድሬዳዋ ኢትዮጵያ

ከጥቅምት 5-2017 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ ይፋ የተደረገው የአእላፋት ዝማሬ ከሦስት ወራት የመዝሙር ጥናትና የማኅበራዊ ሚድያ ዘመቻ በኋላ አእላፋት በተገኙበት በእግዚአብሔር ቸርነት በድሬዳዋ የመጀመሪያው ዙር የአእላፋት ዝማሬ በድሬዳዋ ምድር ባቡር ለገሃር አደባባይ በድምቀት ተካሔደ::

ከቀኑ 10:00 ሰዓት ላይ በድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ በርተሎሜዎስ ፣ የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ እና የመምሪያ ኃላፊዎች እንዲሁም በሀገረ ስብከቱ የሚገኙ የሁሉም አድባራት እና ገዳማት አስተዳዳሪዎች እና ሰ/መ/ጉ/ጽ/ቤት አባላ ተገኝተዋል:: በኢጃት ጃን እስጢፋኖስ ሥር በሚያገለግሉ 12 ዲያቆናት ባካሔዱት በመሐረነ አብ እና በምሕላ ጸሎት ጉባኤው የተጀመረ ሲሆን በጸሎቱ ፍጻሜም በብፁዕ አቡነ በርተሎሜዎስ የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ጸሎተ ወንጌልና ኪዳን ደርሶአል::

በዕለቱም ምእመናን 60 ካሬ ስክሪኖች በአራት አቅጣጫ እየተመለከቱ አብረው የዘመሩ ሲሆን ፍጹም በተረጋጋ መንፈሳዊ ድባብ የመድኃኔ ዓለም ክርስቶስን ልደት በአእላፋት ዝማሬ አክብረዋል:: የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ ወጣቶች ለወራት በብዙ ጸሎትና ትጋት የደከሙበት ይህ የዝማሬ ማዕድ በእግዚአብሔር ጥበቃ ባማረ ሁኔታ ተከናውኖአል:: አእላፋት በዕንባና በተመሥጦ ሆነው እየዘመሩ የመድኃኒታቸውን ልደት በመንፈስ አክብረዋል::


የአእላፋት ዝማሬ ለፓሪስ ኦሎምፒክ ጸያፍ ትርዒት ምላሽ ሠጠ
| ጃንደረባው ሚድያ | ታኅሣሥ 2017 |
አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ

የ2017 ዓ.ም. የአእላፋት ዝማሬ ላይ "የገና መልእክት ከኢትዮጵያውያ ሰዎች ወደ ኦሎምፒከኞች" (A Christmas Message from Myriads to Olympiads) በሚል ርእስ የሁለት ደቂቃ አኒሜሽን ታየ:: የዚህ መልእክትም ዋነኛ ሃሳብ ከአራት ወራት በፊት በፓሪስ ኦሎምፒክ መክፈቻ ላይ የጸሎተ ሐሙስ ሥዕል ላይ ጸያፍ መልእክቶችን በማስተላለፍ የተደረገውን ተሳልቆ ለጸሎተ ሐሙስ ሥዕልና ለከበረው የክርስቶስ ደም ክብር የምትሠጠው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን ምን ያህል እንዳስቆጣ ለማሳየት ነው:: "እነርሱ በስሙ ሲዘብቱ ኢትዮጵያ ግን ዳግመኛ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች" (When they mock his name in vain, Ethiopia lifts her hands to God again) የሚል መልእክት ያለው ይህ ቪድዮ የፓሪስ ኦሎምፒክ አዘጋጆችን ድርጊት በክርስቶስ ላይ የጥላቻ ጦር ከሰበቀው ከንጉሥ ሔሮድስ ድርጊት ጋር በማመሳሰል የተሠራ መሆኑን የአኒሜሽኑ ዳይሬክተር ወ/ሪት ቅድስት ፍስሓ ገልጻለች::

"ዓለም አቀፍ መክፈቻ ሥነ ሥርዓቶችና ምርቃቶች በተካሔዱ ቁጥር በክርስትና መቀለድና ሰይጣናዊ ትርዒቶችን ማሳየት እየተለመደ መጥቶአል" ያሉት የአኒሜሽኑ ክሪኤቲቭ ዳይሬክተር ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ በበኩላቸው "ዓለም አቀፍ ሚድያዎች ከፍተኛ ሽፋን እየሠጡት ባለው በአእላፋት ዝማሬ ላይ ለዓለም አቀፉ ተመልካች የሚሆን መልእክት ለማስተላለፍ አጋጣሚውን ተጠቅመንበታል" ብለዋል::



Показано 14 последних публикаций.